☔️ወደ ሗላ ህዳር 8/3/2012 እና እኔ☔️
✍️ቀኑ ሰኞ ነው እንደ አገራችን ሳምንታዊ ቀን አቆጣጠር ሰኞ የመጀመሪያ ቀን የስራ ቀን ነው። እኔም ከሷሒቤ ጋ ከጀመርናት ስራ ላይ ተጥጃለሁ ነገር ግን ብዙ ጊዜ የማያቸው ሕልሞች ውለው ሳያድሩ በዟሒሩ ከች ይላሉና ጁሙዓ ለቅዳሜ ለይል አንድ ሕልም አይቸ ስለነበር በስጋትና በተበታተነ ሐሳብ ውስጥ ነኝ።ለሷሒቤ ሕልሜን ስለነገርኩት እሱም ስጋት ይዞታል ነገር ግን ያ ቀን ሰኞ ድባቡ ደስ ይላል ዝሁር ድረስ ቆየንና ወደየሰፈራችን አመራን።ምሳ በልተን ድጋሜ ወደ ስራ ገብተን ተፍ ተፍ ማለትን ጀመርን አስር ሶላት ደረሰና ሰግጀ ልቤ ጥሩ ስሜት ሲያጣብኝ ወደ እናቴ ደወልኩና ዘለግ ያለ ወሬ አወራ ምነው ድምፅህ አሞሓል እንዴ አለች እናቴ እኔም እረ ደህና ነኝ አልኩ ግራ በተጋባ ስሜት ከዛም በቃ ሰላም አምሹ ተባብለን ስልኩ ተዘጋ።
✍️ከ10ሰዓት ከ30በሗላ ነው የመንግስት ሰራተኛው የሚወጣበት ተማሪውም ከትምህርት የሚለቀቅበት ወቅት ደርሷል ወደ ከተማ ጎራ ብለው አስቤዛ የሚያደርጉ ሰዎች ከተማዋ ላይ የሚርመሰመሱበት ሰዓት ነው።በዚህ ሰዓት ከተማዋ ጭንቅ ጥብብ ብሏታል ፌደራሎች ፣ፖሊሶች ፣ልዩ ሚሽን ፈፃሚ ፖሊሶች ወዘተ አባላት ከተማዋ ዋና ዋና ቦታቸውን ይዘዋል።ከምሰራበት ሕንፃ ፊትለፊት ያለው ሕንፃ ላይ ስናይፐሮች ቦታቸውን ይዘዋል የተሽከርካሪዎች ሐረካ ተቀንሷል ።እኔ ግን ስራ ቦታዬ ውስጥ ነኝና ውጭ ላይ ምን እየተካሄደ እንደሆነ አላወኩም።
✍️ሁኔታውን የሚያዩ ሰዎች ምን አይነት ባለስልጣን ከተማችን መጥቶ ነው ወይስ ምን ምን አይነት ፀጉረ ልውጥ ገብቶ ነው የሚል የስጋት ወሬ ጫጫታ ተያይዟል።
✍️በዚህ ጊዜ ክትትል ክፍሉና የተመረጡ ፌደራሎች ከአጋዥ GPs ጋ በመሆን ከባንክ ባወጡት ፎቶዬ ተመርተው ሱራው ተመሳስሎባቸው አንድ ወንድማችን ሱቅ ጋ በመድረስ ይይዙታል በእርግጥ GpS እሱ አይደለም እያላቸው ነበር እነርሱ ግን መረጋጋት አልቻሉምና
✍️ሱራውን እያሳዩ ይህ አንተ ነህ አሉት ወንድማችንን በድንጋጤ እየተንተባተበ እረ እኔ አይደለሁም ሲላቸው በጣም መደነገጡን እንደ አድቫንቴጅ ተጠቅመው እሽ ይህንን ባለፎቶ ታውቀዋለህ ሲሉት የደነገጠ ሰው ችግር ነውና አወ አውቀዋለሁ አለ።
✍️አወ አውቀዋለሁ ካልክ ጉዳዩ ሲልሲላ አለውና ምራ የሚል ጥያቄ ይከተላል። እናም የት ነው ምራ ሲሉት እሽ በማለት ቀጥታ ወደ እኔ ስራ ቦታ ይዟቸው መጣ።
✍️ልክ ፎቁን ወጥተው ሱቅ በር ላይ ሲደርሱ ወንድማችን ጣቱን ወደ እኔ በመቀሰር 👉ይህ ነው አላቸው። እኔም ምንድን ነው ሸይኽ ፉላን ስል እንባው አይኑን ሲሞላው ተመለከትኩ ኣሓ ያ እጄ በካቴና ውስጥ ሲገባ ያየሁት ሕልም ዛሬም ግልፅ ሆኖ መጣ ማለት ነው ብዬ የያዝኩትን ትልቅ የጨርቅ መቀስ ይዠ ቀጥ ብዬ ቆምኩ።
፨ከተማዋ ውስጥ አይቸው የማላውቀው ሱፉን ደቅ አድርጎ የለበሰ ሰው ወደ ፊት ቀደም ብሎ ፉላን ማለት አንተ ነህ አለኝ ስልኩ ላይ ያለውን ከባንክ የወጣ ፎቶ እያሳየኝ።
እኔን ይመስላል እስኪ ስልኩን አምጣው ብዬ ጠጋ እንደማለት ስል በቅፅበት ረጃጅሞቹ ፌደራሎች ከቀኝም ከግራም እጄን ጠምዘዝ በማድረግ ጠፍንገው ያዙኝና የያዝኩትን መቀስ ቀምተው አስቀመጡ።
✍️ሱቁ ውስጥ ጓደኞቸ ደንግጠው እንደ እንጨት ደርቀዋል እኔ ቀድሞ ኢሻራው ስለመጣ ብዙም አልደነገጥኩም።ያው እጅ ሰጠሁ ማለት ነው ብዬ ለራሴ ነገርኩና ፀጥ አልኩ።
✍️ከሕንፃው በፍጥነት ይዘውኝ ወረዱና የሆነች ቅያስ አለች ወደሷ ገለል አድርገው በከበባ አስቀመጡኝ።በመገናኛ የሚያወሩት ቀውጢ ሆኗል። ሰዎች እንዴ እሱን ለመያዝ ነው ይህ ሁሉ ጋጋታና ወታደር ደህናውን ልጅ ይላሉ......
~ ከአቡ ሃላል… ከፌስቡክ መንደር የተገለበጠ ነው።