☔️ወደ ቀሶሳችን☔️
✍️አንጋፋው ኢማም ሐሰን አልበስሪ رحمه الله እንድህ ይላሉ፦ሙእሚን እኮ በዱኒያ ውስጥ እስረኛ ነው።አንገቱን ከእስር ለማላቀቅ ይጥራል።በምንም ነገር አይተማመንም የተባረከውንና የላቀውን አላህ እስከሚገናኝ ድረስ ።محاسبة النفس لابن أبي الدنيا
👉የአገሪቱ ከፍተኛ ችሎት 1ኛ ፀረሽብር ችሎት በፕላዝማ ለመቅረብ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ያዘጋጀው ፕላዝማ ክፍል አጃቢዎች ጋ ገባን። እኔ ከመግባቱ ተከትሎ በነዛ ጀነራሎች ግድያ በነ ሳእረ ግድያ ተጠርጥሮ የታሰረው 10አለቃ መሳፍንትም በአጃቢዎች ክፍሉ ውስጥ ገባ። የዛሬ የፕላዝማ ቀራቢዎች ሁለታችን ብቻ ነን ማለት ነው። በእርግጥ መሳፍንት መሆኑን አላወኩም ነበር ስም ሲጠራና ክሳችን ሲነበብ ነበር የእሱን ኬዝና ስሙን ያወኩት። ፕላዝማው ተከፈተና ዳኞች ወደ ችሎት ወንበራቸው ተሰየሙ።ዳኞች እንደት አደራችሁ በማለት ነቃ ለማድረግ ከሞከሩ በሗላ ስማችን ተጠራና መቅረባችንን አረጋገጡ።
👉መጀመሪያ የመሳፍንት ችሎት ተጀመረና ክሱ ተነበበ።መሳፍንትም መልሱን ሰጠ ነገር ግን መሳፍንት ዳኞቹን የለለ ነው ከፍ ዝቅ ያደረጋቸው የመሓል ዳኛውን አንተ እከሌ ምናምን እያለ የሌለ ዛተባቸው 😂እንዴ አልኩኝ እኔ ዳኛ ላይ እንድህ ያዙኝ ልቀቁኝ ማለት ይቻላልዴ ብዬ ተገረምኩ። በእርግጥ አንድ አይኑ በዛ ክስተት ነው አሉ ጠፍታበታለችና ዳኞቹም ብዙም አልተቆጡበትም ሊያረጋጉት ሞከሩ። ብዙ ውርክቦችንና ዛቻወችን ካየን በሗላ የእርሱ ችሎት አለቀ።
👉ተከሳሽ ፉላን ተብሎ የእኔ ስም ተጠራና ከተቀመጥኩበት ወንበር ተነስቸ ወደ ማይኩ ጠጋ ብዬ ችሉቱ ቀጠለ።ዳኞቹ አድስ ናቸው ማለትም ከዛ በፊት አይቻቸው አላውቅም።
✍️ፉላን ይሰማል አሉኝ አወ ይሰማል ብዬ መልስ ሰጠሁና ወላጅና ወዳጅ ቢሰማው ራስ የሚያስተው ግብዳው ክስ መነበብ ተጀመረ። በጣም ብዙ ነገር አነበቡ። በቃ አለምን ዙሪያለሁ ኡማውን ለሸሪዓ የቀሰቀስኩት ይመስላል ክሱ።በእርግጥ ከነጮቹ የልዑኩ መሪ 17አመት አፍጋኒስታን ፣ኢራቅ ፣ሊቢያ ፣ሚስር ፣ሳዑድ አረቢያ አሸባሪዎችን መርምሪያለሁ እንደዚህ የራሳቸውን ማንነት ሳይቀር በመካድ ግግም የሚሉት የቡድኑ ግንድ ሆነው አግኝተናቸዋል ስለዚህ እንዳትለቁት የሚል መመሪያ ሰጥቷቸዋል።እኔ እንኳን ግንዱ የቅርንጫፉም ዘላል አይደለሁም።
✍️የፌደራል አቃቤ ሕጉ 3የሰው ምስክር ፣ቤት ሲፈተሽ የተገኙ ዶክሜንት የያዙ 4ፍላሾችና ቪዛ ነክቶት የማያውቀው ፓስፖርቴን እንደማስረጃ ክሱ ላይ አስቀምጧል።የሰው ምስክር የተባሉት አንዱ የፌደራል አባል በተያዝኩ ቀንና ቤት ሲፈተሽ በአካል የነበረ ቢሆንም ሁለቱ ግን የማያውቁኝ የማላውቃቸው የአድስ ከተማ ክፍለከተማ ነዋሪ ሰዎች ነበሩ።
✍️ክሱ ተነቦ ካለቀ በሗላ በቀጣይ መንግስት ከቀጠረልህ ጠበቃ ጋ ተነጋግራችሁ መልስ ትሰጣላችሁ በማለት የ2ወር ቀጠሮ ሰጥተውኝ ችሎቱን ለመቋጨት ተገደዱ ምክኒያቱም ፕላዝማው እየተቆራረጠ አስቸገራቸውና።
👉ከችሎት አጃቢዎች እኔንም መሳፍንትንም አብረው ይዘውን ወጡ።አይዞህ እንዳትፈራቸው አሸባሪው አለኝ በወታደር አነጋገር መሳፍንት። እኔም ፈገግ ለማለት እየሞከርኩ በግንባሬ እሽ አልኩትና እሱም የተመደበበት ዞን 5 እኔም ወደ ዞን 3 ገባሁ።
✍️መሕከማ ቀርበህ ስትመለስ እስረኛው አፉን አሹሎ ይጠብቃል ምን ተባልክ ለመቸ ቀጠሩህ ክስህ ተነበበ ወይ ብላ ብላ
✍️ረመዷን አሽረልአዋኺርም ግማሽ ሆኗል ቀጠሮየም ረጅም ስለሆነ ተረጋግቸ የቀረችውን የረመዷን ቀን መጠቀም አለብኝ በማለት ልብሶቸን አጣጥቤ ራሴን ፍሬሽ አድርጌ ከረመዷኔ ጋ ቁርኝቴን ጠበቅ አደረኩ። ይቀጥላል