☔️ወደ ቀሶሳችን☔️
✍️ምንም እንኳ እስር ቤት ሕመሙ ከባድ ቢሆንም ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ካለፉት ከሌሎቹ የተሻለ ነው።ክላሶቹ ፣ውሓው መብራቱ ወዘተ ከሌላው የተሻለ ነው።
✍️ማታ 11ሰዓት ቆጠራ ተብሎ ወደቤታችን ተቆጥረን ከገባን በሗላ አልጋዬ ላይ ሆኘ ቁርኣን ለመቅራት እሞክራለሁ ከዛም ፉጡር ሲደርስ ከእኔ ጋ ሌሎች በእድሜ ትንሾች በሌላ ኬዝ የታሰሩ ልጆች ጋ ፕላስቲክ ዘርግተን በፍቅር እናፈጥራለን። ክላሱ ሰፊ ነው ቢያንስ 60ታራሚዎችን ይይዛል። ሶላታችንን ወደ አንዱ ጥግ ጠጋ ብለን በጀመዓ በመስገድ ሐዘናችንን ብሶታችንን ቀለል እናደርጋለን።
✍️ቀን ላይ ደግሞ የማረሚያ ቤቱ መፅሓፍት ገብቸ ኢስላማዊ መፅሓፍትና ኪታቦች አገኘሁ። በቃ ራስን ቢዚ ማድረጊያ ነገሮችን በማግኘቴ ደስተኛ ነበርኩ።
✍️የቀን ሶላቶችን ለመስገድ ትንሽ እንቸገር ነበር በፀሓይ ያኔ በድምፃችን ይሰማ ዘመን በ2008 አመፅ ተነስቶ ስለነበር ማረሚያ ቤቱ ሁሉም ዞኖች ያሉ መስገጃዎችን አፍሯሳቸዋል። ድጋሜም አልሰሯቸውም። መስጂዷ የነበረባት ቦታ ሊሾ ስለነበረች ፀሓይዋን ተቋቁመን ዝሁርንና አስርን እዛቹ እንሰግዳለን።
✍️በተለያየ ኬዝ የታሰሩ ወላሂ የሚሉ ታራሚዎችን በገራልኝ መልኩ ነሲሓ በማድረግ ጀመዓችንን ማጠናከሩን ቀጠልኩኝ።
✍️ረመዷንን በተለያዩ ውጣ ውረዶች አሳልፌ ዒደል ፊጥር ደረሰ😥ኣህህ በዚህ ወቅት ስሜቱ ድብልቅልቅ ነው የሚልብን። በእርግጥ ማረሚያ ቤቱ ለበዓላችን የተለያዩ ዝግጅቶችን ያደርግልናል። ለሁሉም ታራሚ ለስላሳ መጠጦች ይመጣሉ ድባቡም አብሽሩ እንኳን አደረሳችሁ በሚሉ የእርስበርስ የደስታ መግለጫዎች የግቢውን ድባብ ጥሩ መልክ ይሰጡታል።
✍️የዒደል ፊጥር ቀን ጧት ሻወር ወስደን ሁሉም ያለችውን ንፁህ ልብስ ለብሶ ቁርሱን በልቶ ኳስ መጫወቻ ሜዳዋ ላይ እንሰባሰባለን።
✍️መጥፎ ስሜት እንዳይሰማኝ ለማድረግ ብሞከርም በእስር ቤት ዒደል ፊጥርን ለመጀመሪያ ጊዜ ላሳልፍ ነውና አይን በእንባ ይሞላል ግን
👉እንባው እንዳይፈስ እከለክለዋለሁ
✍️የሚገርመው በሌላው ቀን የማይሰግዱትም በዒድ ቀን ፏ ብለው ሶፋቸውን ይዘው የዒድን ሶላትን ለመስገድ ይቀመጣሉ።
✍️እንደምንም አላህ ባገራልኝ መልኩ ኹጥባ ተዘጋጅቷል።ትንሽ ረፈድ እስከሚል ጀመዓውን ተክቢር እያስባልኩ እጅግ ሩቅ ስሜት ያለው ሰመመን ይዞን ተጓዘ።
በእርግጥም ጠበብቶች እንደሚሉት ነው
إذا كان الله معك فماذا فقَدت،
وإن فقدتَ الله فماذا وجدت
✍️ነዓም አላህ አንተ ጋ ከሆነ ምን አጣህ
እርሱን አጥተህስ ምን ታገኛለህ 😥
✍️ተክቢራችንን አንዴ ፈገግታ አንዴ ሲቃ እየተናነቀን
አላሁ አክበር አላሁ አክበር ላ ኢላሃ ኢለላህ አላሁ አክበር አላሁ አክበር ወሊላሂል ሓምድ ማለታችንን ቀጥለናል።
✍️የተወሰነ በተክቢራችን ቀልባችንን ካረጠብንና ኢማናችንን ጠንከር ለማድረግ ከሞከርን በሗላ።ለሶላት ቆምን
✍️አላህ ይቅር ይበለኝና እኔው ጃሒሉ የዒደል ፊጥር ሶላትን ለማሰገድ የመጀመሪያዋን ተክቢራ አላሁ አክበር በማለት ጀመርኩኝ😥 ነገር ግን ልቤ ቦታዋን ልትለቅ ትመስላለች ሰውነቴ መቆም እየተሳነው ይንቀጠቀጣል።እንደምንም ሶላቱ አለቀና የአላህን ታላቅነትና አዛኝነት ለዚህ ዐለም እዝነት እጅግ ባማረ አኽላቅ የላካቸውን አሽረፈል ኸልቅ صل الله عليه وسلم በማውሳት ቀኗን በምንም አይነት አሕዋል ላይ ብንሆንም በደስታ እንድናሳልፋት በመናገር የዒዱ ሶላትና ኹጥባን ጨርሰን በዓላችንን በደስታና ተሰብስበን ለማክበር ሁሉም በቻለው ከሱቅ የሚገዛው ይገዛል ፣ከካፌው ቡና ይታዘዛል በቃ ሁሉም እንደ አንድ ቤተሰብ ሁኖ ዒዱን ያከብራል።
ኢንሻ አላህ ይቀጥላል ።