በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው።
የአላህ ባሪያ መሆን እንዴት ይጥማል! እንዴት ደስ ይላል አስቡት ወላህ!
እንደ ሰው ያሰብከው ሲሳካልህም ሆነ ስትደናቀፍ የምንጊዜም መጠጊያህና መሸሻህ አላህ ብቻ ነው።ይሄንን የማያውቅና ዕድሜ ልኩን የርሱ ጉዳይ በእጁ የሆነውን የአላህን ስም አንድ ጊዜ እንኳን «ያ አላህ!» ብሎ ሳይጠራ ዱንያን የሚሰናበተውን እድለ-ቢስ ብዛት አስተውል!።መዓዘሏህ!።
አላህ ነው የነገሮችህ ሁሉ ቁልፍ በእጁ ያለው፣የፈጠረህ፣ሙስሊም ያደረገህ፣በአንተ ላይ ፀጋዎቹ መች ተዘርዝረው ያልቁና።አስተውላቸው፣አመስግነውም።
ሰዎችማ ስኬት ላይ ሆነህ ካዩህ፣ወዳንተ ለመጠጋት ወደ ራሳቸውም ሊያስጠጉህ ብዙ ይጥራሉ።«እርሱ እኮ ዘመዴ ነው፣ጓደኛዬ ነው፣ወዳጄ ነው...ወዘተ» ይሞግታሉ።ለምሳሌ በዱንያ ጉዳዩ ከፍ ያለ የሚመስለን ሀብታምና ባለ-ስልጣን ሆኖ የሁሉም ዘመድ ያልሆነ ማን ኣለ?።
ስትደናቀፍ፣ስትከስር፣በሙከራህ ላይ ስትወድቅ፣ከስልጣንህ ስትባረር...ወዘተ ከአንተ ጋር ዝቅ የሚሉት የቅርብ ቤተ-ሰቦችህና ትክክለኛ ወዳጆችህ ብቻ ናቸው።
አምላክህ አላህ ግን በከፍታህ ጊዜም ሆነ በዝቅታህ ጊዜ ለርሱ ሂክማ(ያንን የፈለገበት ጥበብ) ኣለው።ሁሌም በአንተ ጉዳይ ላይ የርሱ ውሳኔ ነው የሚፈፀመውና አብዝተህ ተጠጋው፣ውደደው፣ተማፀነው፣መቼም ቢሆን ጥሎ አይጥልህምና።ቆንጠጥ ካደረገህም ዱንያ ኣኺራህ እንዲሳካ፣ረስተሀው ከነበረም ታስታውሰው ዘንድ፣በጀነት በስራህ የማትደርሰውን ከፍታ ያጎናፅፍህ ዘንድ...ወዘተ ሂክማዎች ኣሉት ረቡና።
ይሄኔ ነው የርሱ ባሪያ የመሆንን ጣዕም የምታጣጥመው።ይሄንን አይነቱን አማኝ አስመልክተው ነቢዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ሙስሊም በዘገቡት ሀዲስ የሚከተለውን ብለዋል፦ «የሙዕሚን ጉዳይ ምንኛ ያስደስታል ያስደንቃል፣መልካምን ነገር ካገኘ አላህን ያመሰግንና ለርሱ ኸይር ይሆንለታል፣መጥፎ ነገር ከነካውም ይታገስና ኸይር ይሆንለታል።ይሄ ለሙዕሚን እንጂ ለሌላ ሰው የማይገኝ እድል ነው።»
ታድያ የዝህ ሩሕሩህና እጅግ መልካም፣በመውደቅም ሆነ በመነሳት፣በማግኘትም ሆነ በማጣት ውስጥ ደረጃህን ከፍ የሚያደርግልህ አምላክ የአላህ ባሪያ መሆን በጣም አያስደስትምን?።
ዛሬ በዙሪያህ ያሉ፣ቤተ-ሰብ፣ወዳጅ፣ዘመድ ሌሎችም በሞት ይለዩሃል።እድለኞች ከሆንን በጀነት መገናኘት ቢኖርም።አላህ ግን ዱንያም ሆነህ፣በርዘኽ(ጣረሞት ይዞህ ሞተህ ከተቀበርክበት ለሂሳብ እስከምትቀሰቀስበት) ባለውም፣ተቀስቅሰህ በአርደልመሕሸር፣በአረሷቱ የውሚልቂያመህ፣ተሳክቶ ጀነቱን አስወርሶህም፣አያድርገውና በሌላም ሁኔታ ሆነህ ለዘልዓለም ከርሱ የማትብቃቃ፣ሁሌም የሚያስፈልግህ፣ሁሌም ጉዳይህን ፈፃሚ፣ውለታውን ከምንም ልታነፃፅረው የማትችል...በቃ በጥቅሉ አስገኚህና አምላክህ እርሱ ነው።
አልሐምዱሊላህ ዓላ ኒዕመቲልኢስላም!
ያረብ ሙስሊም አድርገህ እንጂ ኣኺራ አትውሰደን።
አቡ አብዲላህ
አልመዲነቱልሙነወረህ
ጁማደልዑላ 1446 ዓ.ሂ።