“ የገና ስጦታ ለልብ ህሙማን ህጻናት “ የገቢ ማሰባሰቢያ ንቅናቄ ይፋ ሆነ
በኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ሕፃናት መርጃ የህብረተሰቡን ድጋፍ እንዲያገኝ እና አገልግሎቱን እንዲቀጥል ማዕከሉ ከሚያከናውናቸው ቋሚ የድጋፍ ማስገኛ መንገዶች በተጨማሪ ልዩ ልዩ የገቢ ማሰባሰቢያ መርኃግብሮችን ማዘጋጀት አስፈላጊ መሆኑ ይታወቃል፡፡
በዚህም መሰረት በሀገራችን ብቻም ሳይሆን በተለያዩ ዓለማት በድምቀት የሚከበረውን የገና በዓል ምክንያት በማድረግ እስከ ገና በዓል የሚቆይ “የገና ስጦታ ለልብ ህሙማን ህጻናት“ የገቢ ማሰባሰቢያ ንቅናቄ ዛሬ አስጀምሯል፡፡
በዚህ “የገና ስጦታ ለልብ ህሙማን ህጻናት“ የገቢ ማሰባሰቢያ ንቅናቄ ፤ የተለያዩ በጎ ፈቃደኛ ግለሰቦች፣ ድርጅቶችና ተቋማት ከወትሮው በተለዬ መንገድ ማዕከሉን በአይነትም ይሁን በገንዘብ እንዲያግዙና የልብ ህክምና ለማግኘት ወረፋ የሚጠብቁ ከስምንት ሺ በላይ ህጻናት ህክምና እንዲያገኙ በማድረግ አጋርነታችውን እንዲያሳዩ ማዕከሉ በልብ ህሙማን ህጻናት ስም መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡
@HakimEthio