"ዋጋ አውጪለት"
(መልአኩ ስብሐት ባይህ)
*
በመንታ መንገድ ላይ መንታ ልቤን ይዤ
አንድዜ ደንዝዤ አንድዜ ፈዝዤ ።
ምግባሬን ከምግባርሽ ሳማታ
ሳላጋ ሳጣልዝ ሳውታታ ።
በውጥንጥን ውጥን ስመትር ስለካ
በጭንቅንቅ ጭንቀት ስጋግር ሳቦካ ።
በፋኖሱ መሀል ጮራውን እያየሁ
ከጮራው መሀከል ያንቺን ወዝ እሻለሁ ።
ደሞ አንድዜ ቆም ዘገም - ዘገም ቆም እላለሁ
አሁንም ከዚያው ነኝ በዛው እነጉዳለሁ ።
የኋሊት መመለስ ቀልቤን ቢከጅለው
እኔ ግና እዛው ነኝ - እዛው ፣ እንደተውሺኝ አለሁ ።
ትንቢታዊ ነገር
ለነፍሴ ሲነገር ።
መንታ መንታን ወልዶ መንታ እየፀነሰ
ለስሜ ማበሻ ምጡ እየቀነሰ ።
በነጸብራቅሽ ውጋጋን
በጭላንጭሉ ትልምሽ ስር
ካንቺነትሽ ስፍር ላንቺነትሽ ክብር ።
እንደ ወፍ ዘራሽ በድንገት
ከሥርሽ ስክመት በቅዬ
ተንጋልዬ ተጋድሜ ተጠቅልዬ ።
በልባምነቴ ቡርቅቅ ውግዝ
በአንጀታምነቴ ሽምቅ ከለል
ሸክፌሽ ስካለል ።
ፍቅሬ ፍቅሬ ምሥጢረ ወክሬ
ፍቅሬ ፍቅሬ ዙፋነ ወክብሬ
ፍቅሬ ፍቅሬ መስዋዕተ ወዝክሬ
እያልሁ አዘግማለሁ
ቃላቶች ስላጣሁ ቃላት እተክላለሁ
ልሳኔ ተዘግቶ እነጋገራለሁ
ሙገሳ ጠፍቶብኝ አሞካሽሻለሁ
ውዴ ውዴ ውዴ
ውዴ እልሻለሁ
ባንቺ ውድ መሆን እርካሽ ሆኛለሁ ።
የስብዕና ልህቀት
@Human_Intelligence
(መልአኩ ስብሐት ባይህ)
*
በመንታ መንገድ ላይ መንታ ልቤን ይዤ
አንድዜ ደንዝዤ አንድዜ ፈዝዤ ።
ምግባሬን ከምግባርሽ ሳማታ
ሳላጋ ሳጣልዝ ሳውታታ ።
በውጥንጥን ውጥን ስመትር ስለካ
በጭንቅንቅ ጭንቀት ስጋግር ሳቦካ ።
በፋኖሱ መሀል ጮራውን እያየሁ
ከጮራው መሀከል ያንቺን ወዝ እሻለሁ ።
ደሞ አንድዜ ቆም ዘገም - ዘገም ቆም እላለሁ
አሁንም ከዚያው ነኝ በዛው እነጉዳለሁ ።
የኋሊት መመለስ ቀልቤን ቢከጅለው
እኔ ግና እዛው ነኝ - እዛው ፣ እንደተውሺኝ አለሁ ።
ትንቢታዊ ነገር
ለነፍሴ ሲነገር ።
መንታ መንታን ወልዶ መንታ እየፀነሰ
ለስሜ ማበሻ ምጡ እየቀነሰ ።
በነጸብራቅሽ ውጋጋን
በጭላንጭሉ ትልምሽ ስር
ካንቺነትሽ ስፍር ላንቺነትሽ ክብር ።
እንደ ወፍ ዘራሽ በድንገት
ከሥርሽ ስክመት በቅዬ
ተንጋልዬ ተጋድሜ ተጠቅልዬ ።
በልባምነቴ ቡርቅቅ ውግዝ
በአንጀታምነቴ ሽምቅ ከለል
ሸክፌሽ ስካለል ።
ፍቅሬ ፍቅሬ ምሥጢረ ወክሬ
ፍቅሬ ፍቅሬ ዙፋነ ወክብሬ
ፍቅሬ ፍቅሬ መስዋዕተ ወዝክሬ
እያልሁ አዘግማለሁ
ቃላቶች ስላጣሁ ቃላት እተክላለሁ
ልሳኔ ተዘግቶ እነጋገራለሁ
ሙገሳ ጠፍቶብኝ አሞካሽሻለሁ
ውዴ ውዴ ውዴ
ውዴ እልሻለሁ
ባንቺ ውድ መሆን እርካሽ ሆኛለሁ ።
የስብዕና ልህቀት
@Human_Intelligence