ዲሲፕሊን!
“በምታልሙት ሕልም እና በእጃችሁ ሊገባ በሚገባው እውነታ መካከል ያለው ርቀት መጠሪያ ስሙ ዲሲፕሊን ይባላል” (Paulo Coelho)
ዲሲፕሊን የሌለው ሕልም፣ በምንም ያህል ተነሳሽነት (motivation) ቢጀመርም ከቅዠት ቀጠና አልፎ የመሄድ አቅም የለው፡፡
ዲሲፕሊን ማለት አንድን ማድረግ ያለብኝን ነገር ስሜቴ ቢፈቅድም ባይፈቅድም መደረግ ስላለበት ብቻ ማድረግ ማለት ነው፡፡ ማንኛውም ችሎታና ብቃት ከዲሲፕሊን ውጪ ከንቱ ነው፡፡ ምክንያቱም ዲሲፕሊን ከሌለኝ ምንም እንኳ የማድረጉ ብቃት ቢኖረኝና በነገሩ ባምንበትም ያንን ነገር ማድረግ ያስቸግረኛል፡፡ በሌላ አባባል ዲሲፕሊን ከሌለኝ መልካም ልማድን ለማዳበር ፈጽሞ አልችልም፡፡
ሕይወቴን በዲሲፕሊን ካልመራሁ የምተገብረውን ነገር የሚወስንልኝ ያመንኩበት መርህ ሳይሆን የእለቱ “ሙድ” ይሆናል፡፡ ይህ እንዳይሆን ራሳችንን ለመምራት ጤናማ የሆነን ዲሲፕሊን ማዳበር የግድ ነው፡፡
የስብዕና ልህቀት