እስቲ ጠይቂለት
ይሄ ጭንቅላቴ
“ዓለም የሚለውጥ፣
ብልህ የሚያታልል፣
ሁሉ የሚመኘው-ሃሣብ አለኝ!” ብሎ -
ኩራት ኩራት ካለው
አትጠራጠሪ!
የሃሣቡ አስኳል አንቺ ነሽ ማለት ነው።
ይሄ ድህነቴ!
“ከዕንቁ የተወደደ፣
ከገበያ የሌለ፣
ገንዘብ የማይገዛው – ንብረት አለኝ!” ብሎ
ኩራት ኩራት ካለው፤
አትጠራጠሪ
ብቸኛ ንብረቱ አንቺ ነሽ ማለት ነው᎓᎓
ይህ ምንም እኔነት!!
ራሱን ፍለጋ ወደነፍሱ ዘምቶ፤
በእርካታ ቢጠመቅ የፈካ ገጽ አይቶ፡፡
ከዚያ
“ራሴን አገኘሁ፣
ስኬቴን ጨበጥኩት፣
አቅሜን መዘንኩት!” በተሰኘ ዜማ -
ፎክር ፎክር ካለው፤
አትጠራጠሪ
የተገኘው ምስል ያንቺ ነው ማለት ነው።
እኔ የምልሽ ግን?
ይሄ ፈጣሪያችን ፣
አካል ነፍስያዬን፣
ክብደቴን፣ ቁመቴን፣
ስፋቴን፣ ጥልቀቴን፣
መለያ ቀለሜን፣
የምናብ ዓለሜን፣
አንስቶ ያስረከበሽ ሕልምና ዕውኔን፤
እስቲ ጠይቂልኝ የት ጥሎኝ ነው እኔን?
ምንጭ -የመንፈስ ከፍታ
ደራሲ-ሩሚ
ገጣሚ በረከት በላይነህ እንደተረጎመው!
ይሄ ጭንቅላቴ
“ዓለም የሚለውጥ፣
ብልህ የሚያታልል፣
ሁሉ የሚመኘው-ሃሣብ አለኝ!” ብሎ -
ኩራት ኩራት ካለው
አትጠራጠሪ!
የሃሣቡ አስኳል አንቺ ነሽ ማለት ነው።
ይሄ ድህነቴ!
“ከዕንቁ የተወደደ፣
ከገበያ የሌለ፣
ገንዘብ የማይገዛው – ንብረት አለኝ!” ብሎ
ኩራት ኩራት ካለው፤
አትጠራጠሪ
ብቸኛ ንብረቱ አንቺ ነሽ ማለት ነው᎓᎓
ይህ ምንም እኔነት!!
ራሱን ፍለጋ ወደነፍሱ ዘምቶ፤
በእርካታ ቢጠመቅ የፈካ ገጽ አይቶ፡፡
ከዚያ
“ራሴን አገኘሁ፣
ስኬቴን ጨበጥኩት፣
አቅሜን መዘንኩት!” በተሰኘ ዜማ -
ፎክር ፎክር ካለው፤
አትጠራጠሪ
የተገኘው ምስል ያንቺ ነው ማለት ነው።
እኔ የምልሽ ግን?
ይሄ ፈጣሪያችን ፣
አካል ነፍስያዬን፣
ክብደቴን፣ ቁመቴን፣
ስፋቴን፣ ጥልቀቴን፣
መለያ ቀለሜን፣
የምናብ ዓለሜን፣
አንስቶ ያስረከበሽ ሕልምና ዕውኔን፤
እስቲ ጠይቂልኝ የት ጥሎኝ ነው እኔን?
ምንጭ -የመንፈስ ከፍታ
ደራሲ-ሩሚ
ገጣሚ በረከት በላይነህ እንደተረጎመው!