እህቴ ሒጃቡን አንቺ እንደምትፈልጊው ሳይሆን ሸሪዓው እንደሚፈልገው ልበሺው!!
—————
⇛ ሒጃብ ለአላህና ለመልእክተኛው መታዘዝ እንጂ የሆነ ሀገር ባህል ተከታይነት አይደለም። አዎ! ይህን ርዕስ ልብ በይው አንዳንድ ሰዎች ልክ እንደ ከሀዲዎች ሚዲያን ሽፋን አድርገው በቦዲ ተወጣጥረው አለያም ካባ ለብሰው ጥምጣም ጠቅልለው አዋቂ መስለው "ይሄማ የእንዲህ ያለ ሀገር ባህል ነው" እያሉ የሚናገሩትን ሰምተሽ አትታለይ!። እነሱን በጭፍን መከተል አደጋው የከፋ ነውና ተጠንቅቀሽ ስለ ሒጃብሽ ጠንካራ ከሆኑ አስተማሪዎች ትክክለኛውን ሒጃብ አውቀሽ ሸሪዓው በሚፈልገው መልኩ ልበሺ!!።
ከላይ ስለ ሰዎች ሁለት አይነት ባህሪ ማስቀመጤንም ልብ በይው!፣ በሁለቱም መልክ ስላሉ ነውና ነቃ በይ!፣ ማንኛውም ሰው በአለባበሱና በአፈ ቀላጤነቱ እውነተኛ ሊባል አይችልም!!። እውነተኛነቱ በቁርኣንና በሀዲስ በሶሃቦች ግንዛቤ ተፈትሾ ሲያልፍ ብቻ ነው።
⇛ ሒጃብ ጥብቅነትና ንፅህና ነው። ሒጃብን የማትለብስና ከሂጃብ የተራቆተች እንስት ሁለት ነገሩዋ ቆሿል፣ አንዱ ንፁህ ቢሆን እንኳን አንዱ ንፁህ አይሆንም፣ አንደኛ ልቧ ቆሿል ሁለተኛ ሰውነቷን በተለያየ ወንጀል አቆሽሸዋለች፣ በተለያየ ሸሪዓው እርም ባደረጋቸው ነገሮች ሰውነቷን አጨማልቃው ሊሆን ይመቻል፣ የሚፀዳው ሒጃቧን ሸሪዓው በሚያዛት መልኩ ለብሳ፣ ክብሩዋን ጠብቃ ጥንቁቅ ሆና ወደ ጌታዋ ቁርጥ ያለን መመለስ ስትመለስ ነው!።
ልቧ ባይቆሽሽ አትራቆትም ነበር፣ ከሂጃብ መራቆቷ ራሱ የወንጀል መብዛት አንዱ ምልክት ነው። ሸይጧን ሴትን ልጅ ወንጀል እንድታበዛና እንድትሰራ ይገፋፋታል፣ ከዛ በኋላ ግን ከሂጃቧ እንድትገፈፍና ክብር እንዳይኖራት፣ በባለጌዎች እንድትደፈርና እንደ ቀላል እንድትታይ በማድረግ ለዝሙት ፈላጊ ባለጌዎች ምቹ ያደርጋታል። ሒጃቧን በአግባቡ የምትለብስ ሴት ግን ሁሉም ዘንድ ክብር አላት፣ ባለጌዎች ዘንድም ክብር አላት፣ እሷን ቀና ብለው እንኳን አያዩዋትም፣ መልካም ሰዎች ዘንድም ልዩ ክብር አላት።
⇛ ሒጃብ ከኢማን ክፍል ነው ኢማን ማለት:- በልብ ማመን በምላስ መናገር በአካል መተግበር ነው። አማኝ የሆነችዋ ሴት በሒጃብ ግዴታነት በልቧ ካመነች በአካሏም ትተገብረዋለች።
አንዳንዶች ካሉበት ሸሪዓን የሚቃረን ተግባር እንዲመለሱ ሲነገራቸው "ኢማን በልብ ነው ልቤን ከፍተህ አይተሃል?" እያሉ በውሸት ሲያስመስሉ ይስተዋላሉ።
ጥያቄ አለኝ ልባቹ ካመነበት ተግባራቹ ሊመሰክር ምን ከለከላችሁ?! ለአላህ ግን መዋሸት አይቻልም!፣ ለማንኛውም ኢማን ሶስት ክፍሎች አሉት ከነዛ ውስጥ ምንም ማጉደል አይቻልም፣ ታዲያ 3ኛው በአካል መተግበር ነውና ተግብሪ!፣ ሒጃብሽን ጠብቂ!! አንቺ ሒጃብ ብለሽ የምትጠሪውን አናትሽ ላይ የምትጠቀልይውን ብጣሽ ሻሽ ብጤ ጨርቅ ሳይሆን ኢስላም (ሸሪዓ) ሒጃብ ብሎ ያስቀመጠልሽን ሒጃብ ነው የምልሽ። አላህ በተቀደሰው ቃሉ እንዲህ በማለት ያዘዘሽን ሒጃብ:-
يَا أَيُّهَا النَّبِيُّ قُل لِّأَزْوَاجِكَ وَبَنَاتِكَ وَنِسَاءِ الْمُؤْمِنِينَ يُدْنِينَ عَلَيْهِنَّ مِن جَلَابِيبِهِنَّ ۚ ذَٰلِكَ أَدْنَىٰ أَن يُعْرَفْنَ فَلَا يُؤْذَيْنَ ۗ
«አንተ ነቢዩ ሆይ! ለሚስቶችህ፣ ለሴቶች ልጆችህም፣ ለምእምናን ሚስቶችም ከመከናነቢያዎቻቸው በላያቸው ላይ እንዲለቁ ንገራቸው፡፡ ይህ (በጨዋነታቸው) እንዲታወቁና (በባለጌዎች) እንዳይደፈሩ ለመሆን በጣም የቀረበ ነው፡፡» አህዛብ 59
⇛ ሒጃብ የሀፍረተ-ገላ መደበቂያ ነው። ሴት ልጅ ደግሞ መላ ሰውነቷ ሀፍረተ-ገላ ነውና መላ ሰውነቷን ልትሸፍነው ይገባታል!! የአላህ መልእክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) በሶሂህ ሀዲስ እንዲህ ብለዋል:- “ሴት ልጅ ሀፈረተገላ ናት፣ ከቤቷ በወጣች ጊዜ ሸይጧን (አሸላልሞ) ብቅ ብቅ ያደርጋታል።”
ሙሉ ፊትን ጨምሮ መሸፈን ኺላፍ አለበት ምናምን…" የሚሉትን ትተሽ ለአላህ ብለሽ ተቃራኒ ፆታዎችን ላለ መፈተንና ራስሽም ፈተናው ላይ እንዳትወድቂ ብለሽ መላ ሰውነትሽን ልትሸፍኚው ይገባል። ልብስሽን ጉልበትሽ ድረስ አሳጥረሽ ሀፍረተገላሽን ከፍተሽ ለሚወጣ ለሚወርደው አታሳይ!! ልብሱን እንዲያሳጥር የታዘዘው ወንዱ እንጂ አንቺ አይደለሽም!! አንቺማ ክንድ ሚያክል አስረዝመሽ ከመሬት እንድትጎትቺው ነው የታዘዝሺው።
⇛ ሒጃብ የአይናፋርነት (ሀያእ) ምልክት ነው። የሴት ልጅ ተፈጥሮ አይናፋርነት ነውና ተፈጥሮን ጥለሽ ሌላን ለመሆን መሞከር አደጋው የከፋ ነው።
የአላህ መልእክተኛ ﷺ "ሴት ሆና በወንድ የምትመሳሰልና ወንድ ሆኖ በሴት የሚመሳሰልን አላህ ረግሟዋቸዋል።" ብለዋል። ልብ በይ! እህቴ የአላህ እርግማን አለበት!፣ አንዳንድ ሴቶች አላህ ይምራቸውና ከአይናፋርነት አልፈው እንደ ወንድ ሱሪ ለብሰው የሚሄዱ አሉ። እነዚህ እጃቸው ላይ የነበረውን ብርቅዬ ኢስላማዊ የሴት ልጅ ስርኣትን አሽቀንጥረው በመጣል የባለጌዎችን ከተመሳሳይ ፆታ ጋር ጋብቻን መስራቾችን የምእራባዊያንን ስርኣት ናፋቂ ናቸው።
⇛ ሒጃብ መልካም የሆነች አማኝ ሴት ባህሪ ነው። አላህ ይጠብቅሽና እህቴ የዚህ ተቃራኒ መሆንሽ ምንኛ የከፋ ነው? መልሱን ቆም ብለሽ እንድትመልሺው ለአንቺው ተውኩት።
⇛ ሒጃብ ተፈጥሮ ነው መገላለጥ ስሜታዊነት ነው። ተፈጥሮሽን አላህንና መልእክተኛውን ትተሽ ስሜትሽን በመከተል የስሜትሽ አምላኪ መሆን የለብሽም!።
አላህ በተቀደሰው ቃሉ ስለ ሰሜት ተከታዮች እንዲህ በማለት ተናግሯል:-
أَفَرَأَيْتَ مَنِ اتَّخَذَ إِلَٰهَهُ هَوَاهُ وَأَضَلَّهُ اللَّهُ عَلَىٰ عِلْمٍ وَخَتَمَ عَلَىٰ سَمْعِهِ وَقَلْبِهِ وَجَعَلَ عَلَىٰ بَصَرِهِ غِشَاوَةً فَمَن يَهْدِيهِ مِن بَعْدِ اللَّهِ ۚ أَفَلَا تَذَكَّرُونَ
«ዝንባሌውን (ስሜቱን) አምላክ አድርጎ የያዘውን፣ አላህ ከእውቀት ጋር ያጠመመውን፣ በጆሮውና በልቡ ላይም ያተመበትን በአይኑም ላይ ሽፋን ያደረገበትን ሰው አየሀን?! ታዲያ ከአላህ በኋላ የሚያቃናው ማነው?። አትገሰፁምን?!።» አል-ጃሲያ 23
⇛ ልብ በይ! እህቴ፣ ስሜት ተከታይነት ምን ያህል የከፋ ተግባር እንደሆነ ቆም ብለሽ አስተውይ!!
ስለ እውነቱ እናውራ ከተባለ በአሁን ጊዜ ስለ ሒጃብ ከሚነገራቸው በላይ የሚያውቁ ሴቶች በዝተዋል። ምክንያቱም ⇛ ከተለያዩ ዳዒዎች የሰበሰቡት እውቀት አለ፣ ነገር ግን አላህ ያዘነላቸው እንጂ ከተግባሩ የሉበትም፣ ምን ከለከላቸው? መልሱም ቀላል ነው፣ ስሜት ተከታይነት ነዋ።
ከአንድ ሰው ጋር ከተገናኘን ቆይቶ በቅርቡ ተገናኝተን በአንዳድ የዲን ጉዳዮች ስናወራ ስለ አክፍሮት ሀይላት እንቅስቃሴ ማውራት ጀመርን እሱም እንዲህ አለኝ:- "እኔ ግን የሚያሳስበኝ ሙስሊሙ ማሐበረሰብ በሌሎች ስብከቶች ሌላ ሃይማኖት ይከተላል የሚለው ጉዳይ ሳይሆን በስሜት ተከታይነት ይጠፋል የሚለው ጉዳይ ነው የሚያሳስበኝ።" አለኝ፣ አዎን! በትክክል ተጨባጩም የሚያስገነዝበው ይህን ነው።