የሰኞ ፆም እና መውሊድ
===============
የመውሊድ አክባሪዎች ለዚህ ቢድዐቸው ከሚያጧቅሷቸው “ማስረጃዎች” ውስጥ አንዱ ነብዩ ﷺ ሰኞን ከሚፆሙባቸው ምክንያቶች አንዱ የተወለዱበት ቀን መሆኑን መግለፃቸው ነው። ይህንን መነሻ በማድረግ “እንዲያውም መውሊድ መከበር የተጀመረው በራሳቸው በነቢዩ ﷺ ነው” ይላሉ። ይሄ ግን ፈፅሞ ማስረጃ ሊሆናቸው አይችልም። ምክንያቱም፦
1. ፆምና ጭፈራን ምን አገናኘው?!!
እናንተኮ በጭፈራ እንጂ በፆም አይደለም የምታከብሩት። ተግባራችሁ ባልተመሳሰለበት በምን ስሌት ነው የሰኞን ፆም ለጭፈራ ማስረጃ የምታደርጉት? የልደት ቀናቸውን በጭፈራና በድግስ ማሳለፍ ከሳቸውም፣ ከሶሐቦችም፣ ከታቢዒዮችም፣ ከአትባዑ ታቢዒንም፣ ከአራቱ ኢማሞችም፣ በዐቂዳ እንከተላቸዋለን ከምትሏቸው እነ አቡል ሐሰን አልአሽዐሪም፣ አቡ መንሱር አልማቱሪዲም ፈፅሞ አልተገኘም። እስቲ ከቻላችሁ አንዲት ስንጥር ማስረጃ ጥቀሱ!
ደግሞም ነብዩ ﷺ ሰኞን የሚፆሙበትን ምክንያት ሲናገሩ “ስራዎች ሰኞና ሐሙስ ቀን (ወደ አላህ) ይቀርባሉ። እናም ፆመኞ ሆኜ ስራዬ እንዲቀርብልኝ እወዳለሁ” ነው ያሉት። [ሶሒሑል ጃሚዕ፡ 2959] የናንተ ተግባር ግን “ጨፋሪ ሆኜ ስራዬ እንዲቀርብልኝ እወዳለሁ” የሚል ነው የሚሰጠው።
2. እናንተኮ ሰኞ ቀን አይደለም የምታከብሩት!!
ረቢዑል አወል 12 ሁሌ ሰኞ ጋር አይገጥምም። ኧረ እንዲያውም እዚሁ ሃገራችን ውስጥ ሆነ ብለው በያመቱ እሁድ ቀን ብቻ የሚያከብሩ አሉ። ሌሎች ደግሞ ህዳር ላይ፣ ሌሎች ጥቅምት ላይ፣ ሌሎች ደግሞ ረጀብ ወር ላይ የሚያከብሩ አሉ። እንኳን ቀኑና ወሩም አይገናኝም። አመት ጠብቆ የልደት ቀናቸውን ማክበር ከሳቸውም፣ ከሶሐቦችም፣ ከታቢዒዮችም፣ ከአትባዑ ታቢዒንም፣ ከአራቱ ኢማሞችም፣ በዐቂዳ እንከተላቸዋለን ከምትሏቸው እነ አቡል ሐሰን አላሽዐሪም፣ አቡ መንሱር አልማቱሪዲም ፈፅሞ አልተገኘም። እስቲ ከቻላችሁ አንዲት ስንጥር ማስረጃ ጥቀሱ!
ስለዚህ እየተፈፀመ ያለው ነገር ሲወርድ ሲዋረድ የመጣን ባህል ማስቀጠል ብቻ ነው። እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ ለሱና የተጨነቃችሁ ይመስል ከናንተ ፀያፍ ተግባር ጋር የማይዛመደውን የነብዩን ﷺ ሳምንታዊ የሰኞ ፆም ማጣቀስ ማጭበርበር ነው።
3. ሰኞን ብትጠብቁም ከጥፋትነት አይወጣም!!
ሌላው ቀርቶ በየሳምንቱ እየጠበቃችሁ ሰኞን ብታከብሩ እንኳ የናንተ ተግባር በሺርክ የታጨቀ፣ በቢድዐ የተወረረ እና ከስነ ምግባር ያፈነገጠ ተግባር ነው። አሁንማ ጭራሽ የብልኛ መፈፀሚያም ሆኗል። ደግሞስ ነብዩ ﷺ ሰኞን በፆም እንጂ በጭፈራ አላከበሩም። ጭፈራ በምን ስሌት ነው ዒባዳ የሚሆነው? በዚህ ላይ ሺርክ ሲጨመርበት ከድጡ ወደ ማጡ ይሆናል።
4. ከሰኞ ፆም ጋር በቂያስም አይገናኝም!
የሰኞን ፆምና የመውሊድን ጭፈራ በቂያስ ማገናኘትም ጭራሽ የሚያዋጣ አይደለም። እስቲ የሐሙስን የሱና ፆም በጭፈራና በውዝዋዜ ማሳለፍ ይቻላል? በደስታ እንድናሳልፍ የታዘዝናቸውን ሁለቱን ዒዶች በፆም ማሳለፍ ይቻላል? የምስጋና ሱጁድን በሩኩዕ መቀየር ይቻላል? ዒባዳኮ በታዘዘው መሰረት እንጂ በመሰለኝና በደሳለኝ አይፈፀምም። እውነት ከመውሊድ የሚፈልጉት አላማ ለአላህ ምስጋና መግለፅ ከሆነ ሊከተሉ የሚገባው ነብዩ ﷺ የተከተሉትን እርምጃ ብቻ ነበር። “ከመመሪያ ሁሉ በላጩ የሙሐመድ መመሪያ ነውና።” [ሙስሊም፡ 2042] እሳቸው ደግሞ የተወለዱበት ሰኞን በፆም እንጂ በጭፈራና በውዝዋዜ ምስጋናቸውን አልገለፁም። እየተፈፀመ ያለው እሳቸው ከሰሩት ተቃራኒ ነው። ታዲያ ለምን ነብዩን ﷺ የበቃቸው አይበቃንም?!! ለምንስ ከሳቸው ፊት እንሽቀዳደማለን? አላህ እንዲህ አላለምን?
{يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ لَا تُقَدِّمُواْ بَيۡنَ يَدَيِ ٱللَّهِ وَرَسُولِهِۦۖ وَٱتَّقُواْ ٱللَّهَۚ إِنَّ ٱللَّهَ سَمِيعٌ عَلِيمٞ} [الحجرات: 1]
{እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በአላህና በመልእክተኛው ፊት (ነፍሶቻችሁን) አታስቀድሙ። አላህንም ፍሩ። አላህ ሰሚ አዋቂ ነው} [አልሑጁራት፡ 1]
ነብዩስ ﷺ “በኔ ላይ መልካም ምሳሌ አይኖርህምን? በአላህ ይሁንብኝ! እኔ ከናንተ ይበልጥ አላህን ፈሪያችሁ ከማናችሁም በበለጠ ድንበሮቹን ጠባቂ ነኝ” አላሉምን? [አሶሒሐህ፡ 1782]
5. ነብዩ ﷺ ስለ ሰኞ ፆም እንጂ ስለ ረቢዑል አወል 12 አልተናገሩም!
ነብዩስ ﷺ ሰኞ ቀን እንደተወለዱ በግልፅ የተናገሩ ሲሆን ረቢዑል አወል 12 መወለዳቸውን በተመለከተ ግን አስተማማኝና ሶሒሕ ማስረጃ የለም። ጠንካራ ማስረጃ አለመምጣቱ በራሱ ቀኑ ያን ያክል አንገብጋቢ እንዳልሆነ ነው የሚያሳየው። መውሊድ ዛሬ የሚሰጠውን ያክል ክብደት ቢሰጠው ኖሮ ከሳምንቱ ቀናት ውስጥ ሰኞ መወልዳቸውን እንደነገሩን ከአመቱ ወራት ውስጥ በየትኛው ቀን እንደተወለዱ በግልፅ ቋንቋ በነገሩን፣ እንድናከብረውም ባስተማሩን ነበር።
6. የሰኞ እንጂ የረቢዑል አወል 12 መውሊድ በሐዲሥ ድርሳናት ውስጥ አይገኝም
በሱና ድርሳናትም ላይ የሰኞ ፆም ትኩረት ተችሮት የተወሳ ሲሆን ረቢዑል አወል 12ን የሚመለከት ግን አንድም የለም። ምክንያቱም ሊቀርብ የሚችል መረጃ የለምና። ቡኻሪ፣ ሙስሊም፣ አራቱ ሱነኖች፣ … ብንፈትሽ ረቢዑል አወል 12ን በደስታ፣ በጭፈራ፣ በተለየ ዒባዳ፣ በሶደቃ እንድናሳልፍ የሚጠቁም አንድም መረጃ አይገኝም። ይህም የሰኞ ፆም ለመውሊድ መረጃ እንደማይሆን ጠቋሚ ነው። ቢሆን ኖሮ ከመውሊድ አጋፋሪዎች በፊት እነ ቡኻሪ ይረዱት ነበርና።
6. ነብዩ ﷺ የተወለዱበት ቀን ዒድ አይደለም!
በኢስላም ዒድ አይፆምም። ነብዩ ﷺ ሰኞን መፆም የሚወደድ እንደሆነ አስተማሩ እንጂ “ቀኑ ዒድ ነው” አላሉም!! እለቱ ዒድ ቢሆን ኖሮ በፆም አያሳልፉትም ነበር። የመውሊድ አክባሪዎች ግን ቀኑን ዒድ አድርገውታል። በሚደንቅ ሁኔታ “ቀኑ ዒድ ስለሆነ መፆም አይቻልም” እስከማለት የደረሱ አሉ። "መዋሂቡል ጀሊል ሸርሑ ሙኽተሶሩል ኸሊል የተሰኘውን ከታብ ገፅ 2/406 ላይ ማየት ትችላላችሁ፡፡ ሙሐመድ ኢብኑ አሕመድ በኒስ፣ ኢብኑ ዐባድና ሌሎችም እንዲሁ እለቱን ዒድ ነው ይላሉ። የሚያሳፈር! ታዲያ እንደዚያ የሚሉ ከሆነ ለምን ነብዩ ﷺ በፆም ያሳለፉትን ሰኞን ለዚህ ድርጊታቸው መረጃ ያደርጋሉ? ዒድ ይፃማል እንዴ?
ቀንደኛ የመውሊድ አቀንቃኝ የሆነው ኢብኑል ዐለዊ ግን መውሊድን መሀይም እንጂ በዒድ አይገልፀውም ይላል። መውለድ ዒድ (በአል) ነው የምትሉ የዋሀን ሆይ! መሃይማን ባትሆኑ ኖሮ መውሊድን ‘ዒድ ብላችሁ አትገልፁም ነበር’ እየተባላችሁ ነው!! በርግጥ እሱ በዚህ በኩል የሚነሳውን ትችት ለመሸሽ ያክል ነው ይህን የሚለው። እንጂ ዞር ብሎ “ቀኑ ከዒድም በላይ ነው” ይላል። [አልኢዕላም፡ 8] የዞረበት ጉድ! የቢድዐ ፍቅር ሰዎቹን የት እንደሚያደርሳቸው ተመልከቱ። ለዚህ ሙግቱ ከከንቱ ትንተና ባለፈ ከቁርኣንም ከሐዲሥም ከሰለፎች ንግግርም አንድም ሊያቀርበው የሚችለው ነገር የለም።
ሲጠቃለል የነብዩ ﷺ የሰኞ ፆም እና አመታዊ የሱፍያ ጭፈራ በየትም አቅጣጭ አይገናኝም። አራምባና ቆቦ ነው።
(ኢብኑ ሙነወር፣ መስከረም 20/2014)
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor