🧿አጭር መልዕክት
✍ዘጠኝ መመሪያዎች!!
♻️ በዱንያ ስትኖር ከሙስሊም ወንድምህ ጋ በአላህ መንገድ ላይ ተዋደህ እንደመኖር የሚያስደስት ነገር የለም። በተቀራኒው ምድር ላይ ከሙስሊም ወንድምህ ጋ በሆነ ባልሆነው ተኮራርፈህ እንደመኖር ስሜትን የሚጎዳ ነገር የለም።
የሚዋደዱ ጓደኛሞች ወሬ በማመላለስ በመሃከላቸው ያለዉን መሀባ ማጥፋት ብሎም ማጣላት ትልቅ በሽታ ነው። ከድግምት ጋር የሚያመሳስል ስራም ተደርጎ ይወሰዳል። ብዙ ጊዜ የሰው ልጅ በንግግርም ሆነ በተግባር በሰው ልጅ ላይ ድንበር የሚያልፈው የአላህን እና የመልእክተኛውን ﷺ መመሪያዎች ባለመረዳት እና ባለመተግበሩ ነው።
አምላካችን አላህ በሱረተል ሑጁራት ላይ ለአማኞች ዘጠኝ መመሪያዎችን አስቀምጧል። ማንኛውም ሙስሊም ማንኛውንም ዐይነት ሰው ላይ ከመናገሩ በፊት እነዚህን መመሪያዎች ማጤን አለበት።
እነዚህ መመሪያዎች እነማን ናቸው ከተባለ?
.
1ኛ . አረጋግጡ (فَتَبَيَّنُوٓاْ)
● ነገረኛ ወሬን ቢያመጣልህ ወሬውን አሰራጭተህ ጉዳት ባንተም በሌሎች ላይ ደርሶ ከመፀፀትህ በፊት አረጋግጥ።
قال الله تعالى ﴿يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِن جَآءَكُمْ فَاسِقٌۢ بِنَبَإٍ فَتَبَيَّنُوٓا۟ أَن تُصِيبُوا۟ قَوْمًۢا بِجَهَٰلَةٍ فَتُصْبِحُوا۟ عَلَىٰ مَا فَعَلْتُمْ نَٰدِمِينَ﴾ الحجرات
“እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ነገረኛ ወሬን ቢያመጣላችሁ በስህተት ላይ ኾናችሁ ሕዝቦችን እንዳትጎዱና በሠራችሁት ነገር ላይ ተጸጻቾች እንዳትኾኑ አረጋግጡ፡፡”
2. አስተካክሉም (وَأَقۡسِطُوٓاْۖ)
.
قال الله تعالى ﴿وَأَقْسِطُوٓا۟ۖ إِنَّ ٱللَّهَ يُحِبُّ ٱلْمُقْسِطِينَ ﴾
“በነገሩ ሁሉ አስተካክሉም፡፡ አላህ አስተካካዮችን ይወዳልና”
.
3. አስታርቁ (فَأَصۡلِحُواْ)
.
قال الله تعالى ﴿إِنَّمَا ٱلْمُؤْمِنُونَ إِخْوَةٌ فَأَصْلِحُوا۟ بَيْنَ أَخَوَيْكُمْۚ وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ لَعَلَّكُمْ تُرْحَمُونَ﴾
“ምእመናኖች ወንድማሞች ናቸው፡፡ በሁለት ወንድሞቻችሁም መካከል አስታርቁ፡፡ ይታዘንላችሁም ዘንድ አላህን ፍሩ፡፡
.
4. አይሳለቁ (لَا يَسۡخَرۡ)
قال الله تعالى ﴿يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ لَا يَسْخَرْ قَوْمٌ مِّن قَوْمٍ عَسَىٰٓ أَن يَكُونُوا۟ خَيْرًا مِّنْهُمْ وَلَا نِسَآءٌ مِّن نِّسَآءٍ عَسَىٰٓ أَن يَكُنَّ خَيْرًا مِّنْهُنَّۖ﴾
“እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ወንዶች ከወንዶች አይቀልዱ፡፡ ከእነርሱ የበለጡ ሊኾኑ ይከጀላልና፡፡ ሴቶችም ከሴቶች (አይሳለቁ)፡፡ ከእነርሱ የበለጡ ሊኾኑ ይከጀላልና”
5. አታነውሩ (وَلَا تَلۡمِزُوٓاْ)
.
قال الله تعالى ﴿وَلَا تَلْمِزُوٓا۟ أَنفُسَكُمْ وَلَا تَنَابَزُوا۟ بِٱلْأَلْقَٰبِۖ بِئْسَ ٱلِٱسْمُ ٱلْفُسُوقُ بَعْدَ ٱلْإِيمَٰنِۚ وَمَن لَّمْ يَتُبْ فَأُو۟لَٰٓئِكَ هُمُ ٱلظَّٰلِمُونَ﴾
“ነፍሶቻችሁንም አታነውሩ፡፡ በመጥፎ ስሞችም አትጠራሩ፡፡ ከእምነት በኋላ የማመጽ ስም ከፋ፡፡ ያልተጸጸተም ሰው እነዚያ እነርሱ በዳዮቹ ናቸው”
.
6. በመጥፎ ስሞችም አትጠራሩ (وَلَا تَنَابَزُواْ)
.
قال الله تعالى ﴿وَلَا تَنَابَزُوا۟ بِٱلْأَلْقَٰبِۖ بِئْسَ ٱلِٱسْمُ ٱلْفُسُوقُ بَعْدَ ٱلْإِيمَٰنِۚ وَمَن لَّمْ يَتُبْ فَأُو۟لَٰٓئِكَ هُمُ ٱلظَّٰلِمُونَ﴾
“በመጥፎ ስሞችም አትጠራሩ፡፡ ከእምነት በኋላ የማመጽ ስም ከፋ፡፡ ያልተጸጸተም ሰው እነዚያ እነርሱ በዳዮቹ ናቸው”
.
7. ከጥርጣሬ ራቁ (ٱجۡتَنِبُواْ كَثِيرٗا مِّنَ ٱلظَّنِّ)
.
قال الله ﴿يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ ٱجْتَنِبُوا۟ كَثِيرًا مِّنَ ٱلظَّنِّ إِنَّ بَعْضَ ٱلظَّنِّ إِثْمٌۖ﴾
“እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከጥርጣሬ ብዙውን ራቁ፤ ከጥርጣሬ ከፊሉ ኃጢአት ነውና”
.
8. አንዱ አንደኛው ላይ አይሰልል (وَلَا تَجَسَّسُواْ)
.
قال الله تعالى ﴿وَلَا تَجَسَّسُوا۟﴾
“ነውርንም አትከታተሉ”
.
9. ሀሜትን ራቁ (وَلَا يَغۡتَب بَّعۡضُكُم بَعۡضًاۚ)
.
قال الله تعالى ﴿ وَلَا يَغْتَب بَّعْضُكُم بَعْضًاۚ﴾
“ከፊላችሁም ከፊሉን አይማ”
● ሀሜት ማለት እኮ የሰውን ስጋ የሞተ ኾኖ እንደመብላት ነው ማንነው ይህንን ለራሱ የሚወደው?!
قال الله ﴿وَلَا يَغْتَب بَّعْضُكُم بَعْضًاۚ أَيُحِبُّ أَحَدُكُمْ أَن يَأْكُلَ لَحْمَ أَخِيهِ مَيْتًا فَكَرِهْتُمُوهُۚ وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَۚ إِنَّ ٱللَّهَ تَوَّابٌ رَّحِيمٌ ﴾
«ከፊላችሁም ከፊሉን አይማ፡፡ አንደኛችሁ የወንድሙን ስጋ የሞተ ኾኖ ሊበላው ይወዳልን? (መብላቱን) ጠላችሁትም፤ (ሐሜቱንም ጥሉት)፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ጸጸትን ተቀባይ አዛኝ ነውና”
.
•►ማጠራቀሚያ …! ማንኛውም ሙስሊም አንድ ነገር ሲናገር ወይም ሲሰራ እንደዚህን መመሪያ መከተል ያስፈልጋል።
☑️ ሙእሚን ሁሌም ሲያስታውሱት ያስታውሳል ሲመክሩትም ይመከራል።
.
قال الله تعالى ﴿ وَذَكِّرۡ فَإِنَّ ٱلذِّكۡرَىٰ تَنفَعُ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ ﴾ [ الذاريات: 55]
“አስታውስ፤ ያንተ ማስታወስ ለአማኞች ትጠቅማለችና”