🏷️የዛዱል መዓድ ፈታዋ 🌾
فتاوى زاد المعاد
ቁ/272
የዕለተ ረቡዕ 1/7/1446 ዓ.ሂ ትምህርት
🔊በኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም
ዳውንሎድ ለማድረግ ይህን ይጫኑ 🔗
https://rb.gy/hwu4b3▪️1/ የሆነ ስራ ለመስራት ፈልጌ የአጎቴ ልጅ ብር ሊያበድረኝ ነበር የሚኖረው ሳውዝ አፍሪካ ነው እዛ የሚሰሩ ልጆች ሲጋራና ዊግ ይሸጣሉ አብዛሃኞቹ የአጎቴ ልጅ እነዚህን ይሸጣል አይሸጥም አላውቅም የሱን ብር ተቀብዬ መስራት እችላለው?
▪️ 2/ ከዚህ በፊት አከራይቼ ነበረ ተከራዮቹ የቤት ክራዩን ሳይከፍሉ ከጠፉ 3 አመት ይሆናቸዋልና የቤት ክራዩን ብር እነሱ ጥለውት ከሄዱት እቃ ሽጬ መውሰድ እችላለሁኝ?
▪️3/ እኔ ሰለምቴ ነኝ ቤተሰቦች ክርስቲያን ናቸው እህቴም ሰልማ ነበር ቤተሰብ ጋር በሄደችበት ክርስቲያን ልጅ አገባች እናት መልስ ልትጠራቸው ፈልጋ ብር አነሳት እናቴን በብር ባግዛት በሃራም መተባበር ይሆንብኛል?
▪️4/ እኔ ከባለቤቴ ጋር ተጣልቼ ከአሁን በኋላ ካንተ ጋር መኖር አልፈልግም ብዬ ማልኩኝ ከዛም በኋላ ሰዎች አስታረቁን አብረን መኖር ጀመርን ለማሃላው ምን ማድረግ አለብኝ?
▪️5/ ነሲሓ የሚያስፈልገው ጉዳይ ነው እርሶ ይህን ያክል እያስተማሩ በሴቶች ላይ በዚህ ልክ እየለፉ ጥሩ አኽላቅና ስነ–ምግባር እንዲኖረን በአላህ ፍቃድ እየሰሩ ቢሆንም እኛ ሴቶች ግን በሰው ህይወት ገብተን የሚመለከተንንም የማይመለከተንንም እያወራን እንገኛለን። ስለ ሰው ባል፣ ሚስት፣ልጆች ባጠቃላይ ስለ፣ ብሔር ስለ ሀብት፣ ስለ ሸይኽ፣ ስለ ደርሳዎች የሚቀረን የለም። የቀራን እስከማንመስል ኢልም ላይ ያለን እስከ ማንመስል በጣም የሚያሳፍር ባህሪ ነው የምናንፀባረቀው ነሲሓ ያስፈልገናል ።
▪️6/ ወንድ የእጅ ጌጥ መልበስ ሀራም ነው?
▪️7/ እናቴ የማታ ደርሶችን ለመከታተል ለደህንነቴ ከመስጋት የተነሳ አትፈቅድም እና እሷን እሺ ብዬ ልታዘዝ ወይስ እንቢ ብዬ ወደ ደርስ ልሂድ?
▪️8/ አንድ ሰው ለሌላ ሰው ልደት እንኳን አደረሰህ ማለት እንዴት ይታያል? ከማለትም አልፎ ቀለል ያለ ስጦታ ሰጥቶ አላህ እድሜህን/ሽን ያርዝመው ማለትስ?
▪️9/ ለወገብ ህመም፣ ውፍረትን ለመቀነስ፣ ለግፊት፣ ለስኳር ፣ለኮልስትሮልእና ለብዙ አይነት በሽታዎች ለመቀነስ ዶክተሮች እስፖርት ያዛሉና ሙዚቃ ሳይኖር ለሴቶች በሴቶች አሰልጣኝ እስፖርት መስራት እንዴት ይታያል?
▪️10/ ለመድረሳ ግንባታና ለመስጂድ ግንባታ እንዲሁም ለመድረሳ ወጪ የዘካን ገንዘብ መስጠት ይቻላል?
▪️11/ የቅርብ ቤተሰብ ችግርተኛ እያለ የዘካን ገንዘብ ለመድረሳ መስጠት እንዴት ይታያል ?
▪️12/ የዛሬ 3 አመት አካባቢ በህመም ምክኒያት የረመዷን መፆም አልቻልኩም ነበርና በስኣቱ ባለማወቅ ለሚስኪን አብልቼ ብቻ ትቼው ነበር ቀዷእ ማውጣት እንዳለብኝ ያወቅኩኝ አሁን ነው ግን አሁንም በጣም እያመመኝ ስለሆነ መፆም አልችልም ምን ማድረግ ነው ያለብኝ?
▪️13/ ከአባት ቀድማ የሞተች ሴት ልጅ ከአባቷ ንብረት ድርሻ/ውርስ አላት?
ከአባትዋ ቡሃላ የሞተችስ የምትወርስ ከሆነ ድርሻዋ ለልጆችዋ ይደርሳል?
ከደረሳቸውስ በህይወት ካሉ እህቶች እኩል ነው?