ሁለተኛው አይነት የመንታ እርግዝና ደግሞ መልካቸው እንደ ወንድምና እህት የተመሳሰለ ግን አንድ አይነት ያልሆነ ሲሆን ጾታቸው የተለያየ ወይም አንድ ሊሆን ይችላል። ይህ ደግሞ የሚፈጠረው ምንም እንኳን በብዙ ሴቶች ላይ በኦቩሌሽን/ውጻት ጊዜ ከኦቫሪ የሚወጣው አንድ እንቁላል ብቻ ቢሆንም ባንዳንድ ሴቶች ላይ በተለይም በቤተሰባቸው መንታ የመውለድ(በእናት በኩል) ታሪክ ያላቸው እንዲሁም እድሜያቸው ከገፋ በሚያረግዙ ሴቶች ላይ ባንድ ኦቩሌሽን/ውጻት ጊዜ ከኦቫሪ የሚወጣው እንቁላል ሁለት ሲሆንና ሁለቱም ከተለያየ የወንድ ዘር(በአንድ የግብረስጋ ግንኙነት ጊዜ በሚሊየን የሚቆጠር የወንድ ዘር ነው ወደ ሴቷ ማህጸን የሚገባው) ጋር ሲዋሃዱ ነው፡፡
በቀላሉ ለማርገዝ ተቸግረው በፈርቲሊቲ (የመካንነት) ህክምና ድጋፍ የሚያረግዙ ሴቶችም በህክምናው ምክንያት መንታ ወይም ከዚይ በላይ የማርገዝ እድላቸው ይጨምራል።
4. 39 አመቴ ነው የወር አበባዬ በየ26 ቀኑ ነው የሚመጣው፤ ለማርገዝ አመቺዉ ጊዜ መቼ ነዉ?
የወር አበባሽ ሁሌም በ26 ቀን ከሆነ የሚመጣው የኦቩሌሽን ጊዜሽ የሚሆንው ያለፈው የወር አበባ ከጀመረበት ቀን ጀምሮ በመቁጠር ከ8ኛው ቀን እስከ 15ኛው ቀን ባለው ጊዜ ውስጥ ነው፡፡ ነገር ግን አንዳንዴ ከ26 ቀን የሚረዝም ወይንም የሚያጥር ከሆነ የሚከተለዉን ዘዴ መጠቀም ትችያለሽ፡
የወር አበባ የመጣበትን ቀን አንድ ብሎ የሚቀጥለው ከመጣበት በፊት ያለውን ቀን እንደ መጨረሻ በመውሰድ የየወሩ የወር አበባ ኡደት ርዝመት ምን ያህል ቀን እንደሆነ ለተወሰኑ ወራት መመዝገብ፡፡ ከዛም ከአጭሩ ቀን ላይ 18 መቀነስ የመጀመሪያውን እርግዝና ሊፈጠር የሚችልበትን ጊዜ ይነግርሻል፤ ከረጅሙ ላይ ደግሞ 11 መቀነስ የመጨረሻውን እርግዝና ሊከሰትበት የሚችለውን ጊዜ ይነግርሻል፡፡
እድሜ ከ35 በላይ ሲሆን ቶሎ ማርገዝ ሊከብድ ይችላል ስለሆነም በተደጋጋሚ መሞከር ይበረታታል። ከ6 ወር በላይ ለማርገዝ ሞክሮ ካልተሳካ በዘርፉ የተሰማሩ የህክምና ባለሙያዎችንም ማማከር ጥሩ ነው፡፡
5. ማርገዜን እንዳወኩ የእርግዝና ክትትል መጀመር ያስፈልገኛል ወይስ ካመመኝ ብቻ ልሂድ?
አንድ ሴት ማርገዟ እንደታወቀ ወደ ህክምና መስጫ ቦታ ሄዳ የእርግዝና ክትትል መጀመር ይኖርባታል። የእርግዝና ክትትል ማድረግ ቀድሞ የነበሩና በእርግዝና ጊዜ የሚከሰቱ የጤና እክሎችን በጊዜ ተደርሶባቸውእና አስፈላጊውን ህክምና ለማድረግ ያስችላል፡፡ ይህም እርግዝናው የሚወለደውም ልጅ ጤናማ እንዲሆን ይረዳል፡፡
የእርግዝና ክትትል ቶሎ በመጀመር በጊዜ ታውቀው ሊታከሙ ከሚችሉ የጤና እክሎች መካከል የሚከተሉት ይጠቀሳሉ፤
o የደም ግፊትነገር
o ስኳር
o አይረን የተባለ ንጥረ እጥረት
o የኩላሊት ችግር
o ከባድ የማስታወክ ችግር
************
አስተያየትም ሆነ ጥያቄዎቻችሁን ብታካፍሉን ደስ ይለናል። በእርግዝና ወቅት ቅድምመከትል ክትትል እያደረጉ ሃኪም የሚሰጠዉን ምክር መከትል ሁሌም ቅድሚያ ሊሰጠዉ ይገባል።
ይቅናችሁ እንግዲህ! ለገንፎ መጥራት እንዳትረሱ ታዲያ!
በመጨረሻም - መቼም አንድ ቀን ስለልጅ መዉለድ ማሰባቸዉ አይቀርምና ሼር በማድረግ ለወዳጅ፣ ዘመድና ጓደኛ እንድታካፍሉ በማክበር እንጠይቃለን!ስለተባባራችሁን እናመሰግናለን።
ምንጭ፦www.semunon.com