የኡሁድ ዘመቻ ከመከሰቱ ከቀናት በፊት አንድ ሙሽሪክ ምናልባት ሙሀመድ ወድቆ ቢሰበር በሚል ጉድጓድ ሲቆፍር ከረመ።
ጦርነቱም ተጀመረ፤ ሀቢቡና ሙሀመድﷺ በተፋፋመ ውግያ ውስጥ ሳሉ ድንገት በአጋጣሚ ከተቆፈረላቸው ጉድጓድ ውስጥ ወደቁ።
ከወደቁበት ጉድጓድ ለመነሳት ሲሞክሩ ዑትባ የተሰኘ እርጉም በያዘው ሰይፍ በተደጋጋሚ ራስ ቅላቸውን እና ፊታቸውን ይደበድብ ጀመር።
ረሱል ደከሙ፣ ደማቸው ከየፊናው መፍሰስ ጀመረ፣ የሰይፍ ስባሪ ከፊታቸው ስር ዘልቆ ገባ'ና ውስጥ ላይ ተሰበረም።
ድንገት ይህን የተመለከተው የልብ ጓደኛ፣ የመንፈስ ወንድም፣ የእውነት ተንከባካቢ አቡበክር፦‹‹ፊዳከ ያ ረሱለሏህ! ነፍሴ ትሰዋልዎ›› እያለ ከጉድጓዱ ገብቶ የተሰካውን ብረት ከፊታቸው ለመንቀል ትግል ጀመረ። አልተሳካም፤ ትግሉም ቀጠሏል።
ሰሀባዎች ተራበሹ...፤ ‹‹ረሱል ﷺ ተገደሉ›› የሚሉ ወሬዎች ከጦር ሜዳው ላይ ይንሸራሸሩ ጀመር።
ይህን ወሬ የሰማው አቡ ኡበይዳ ወዳጁ ሰዐወ ከወደቁበት ጉድጓድ እየተንደረደረ ሂዶ በመግባት፦‹‹አቡ በክር ሆይ! በአላህ ቦታውን ልቀቅልኝ እኔ ልንቀልላቸው›› ብሎ ተማፀነ።
ከፊታቸው የተሰካውን ብረት ለመንቀል አቡ ኡበይዳም በተራው ትግል ጀመረ፤ አልተሳካለትም። የተሰካውን ብረት በጥርሱ ነክሶ መጎተት ሲጀምር በጎተተ ቁጥር ጥርሶቹ ተራ በተራ ይራገፉ ጀመር፤ እሱም መጎተቱን ቀጠለ።
የሚራገፉ ጥርሶቹን ከቆብ ያልቆጠረው ይህ ሰሀቢይ ከብዙ ትግል በኋላ ጥርሶቹን ሰውቶ ብረቱን ነቀለው።
ረሱል ﷺ ቁጭ አሉ። በተከበሩ እጆቻቸው ከፊታቸው የሚፈሰውን ደም መጠራረግ ጀመሩ፤ ያልበሉትን እዳ የሚያስከፍላቸውን ህዝብ እያሰቡ እጃቸውን ወደ መውላ ከፍ አደረጉ።
ይህን ጊዜ አቡበክር ቀልቡ ተሸበረ፤ ህዝቡ በነብይ እርግማን እንደሚቀጠፍም አመነ፣ ስጋት ተቆጣጠረው፤ ዋ! ህዝቤ ጠፋህ ብሎም ተስፋ ቆረጠ።
ሀቡና ሙሀመድ ﷺደማቸው አፈር ላይ እንዳይፈስ እየጠራረጉ፦‹‹ኢላሂ! ህዝቤን ይቅር በል፤ አያውቁም'ና›› እያሉ ሆድ በሚብስ ሁኔታ ዱዓ አደረጉ።
ሀቢቡና💚💚💚
join👇👇👇
t.me/IslamisUniverstiy_public_group