ኮብላይ ተስፋ
ጊዜ ነፋስ ነው - የባሕር አውሎ
ወጀቡ ጤዛ እየዘራ....
ይንከራተታል በየትም - ነፍስ የሚበርድ ቆፈን አዝሎ።
ተስፋ ያ'ረኩት ነገ - ያልፋል በነፋስ ታዝሎ
ጊዜ ይጠድፋል ከአውሎ
ይከስማል ጥላው ቸኩሎ።
ግብብ መስኮቴን ብከፍተው - የንጋት ጮራ እንዲገባ
ቀኑ ድንግዝግዝ ለብሷል...
ሳታፈራ እረግፍለች - ርጥብ አደይ አበባ።
ሳይነጋ ዳግም ጨልሟል - ዞሯል የአመሻሽ ጥላ
ነፍሴ እሽ ሩሩ ስትል - ተስፋ ጉጉቷን አዝላ፤
ተስፋዋ በእቅፏ ሞተ - ጠለቀች በዋዛ ጀንበር
ሁሉም ከንቱነት ሆነብኝ - ድካም ነው ነፋስን ማስገር።
እንደ እፉዬ ገላ ከስሞ - ገና በአበባው ጉጉቴ
በየት ጥሎኝ አለፈ - ከነፋስ ፈጥኖ ልጅነቴ...
```
አሻግሬ ባይ ዱር ለብሷል - የመጣሁበት መንገድ
ይግባኝ አይሉት ለሸንጎ - ጊዜ ሳይነጋ ሲረፍድ።
እንዴት ተጣጣሁ ከኅልሜ
ዋ! ልጅነት ቀለሜ
ላልደርስ እባክናለሁ - ላልችለው ጊዜን ተሸክሜ።
ቀና ብል ለዓይኖቼ ራቀ - እንደ ጉም ተ'ኖ ጠፋ
በሸካራ መዳፌ...
ከጠወለገ እንባ ጋር - ታበሰ በዋዛ ተስፋ።
እንባዬን ከፊቴ ሊጠርግ - ቢነሣ ይቡስ መዳፌ
ክንዴን ዝሎ አገኜውት - የሞተ ተስፋ ታቅፌ።
መንገደኛ ነፋስ ነው - ኅልማችን ሁሉ ከንቱ
የመኖር ቆፈን፥ ውሽንፍር - የጊዜ ብርዱ እትቱ..
እንደ ክረምት ቁልቁለት
እያዳለጠችኝ ሕይወት
ስንት መከራ ልሸከም - ለአንዲት ዓለም - ለአንዲት ኑረት..?
༺❀༻
ጊዜ ነፋስ ነው - የባሕር አውሎ
ወጀቡ ጤዛ እየዘራ....
ይንከራተታል በየትም - ነፍስ የሚበርድ ቆፈን አዝሎ።
ተስፋ ያ'ረኩት ነገ - ያልፋል በነፋስ ታዝሎ
ጊዜ ይጠድፋል ከአውሎ
ይከስማል ጥላው ቸኩሎ።
ግብብ መስኮቴን ብከፍተው - የንጋት ጮራ እንዲገባ
ቀኑ ድንግዝግዝ ለብሷል...
ሳታፈራ እረግፍለች - ርጥብ አደይ አበባ።
ሳይነጋ ዳግም ጨልሟል - ዞሯል የአመሻሽ ጥላ
ነፍሴ እሽ ሩሩ ስትል - ተስፋ ጉጉቷን አዝላ፤
ተስፋዋ በእቅፏ ሞተ - ጠለቀች በዋዛ ጀንበር
ሁሉም ከንቱነት ሆነብኝ - ድካም ነው ነፋስን ማስገር።
እንደ እፉዬ ገላ ከስሞ - ገና በአበባው ጉጉቴ
በየት ጥሎኝ አለፈ - ከነፋስ ፈጥኖ ልጅነቴ...
```
አሻግሬ ባይ ዱር ለብሷል - የመጣሁበት መንገድ
ይግባኝ አይሉት ለሸንጎ - ጊዜ ሳይነጋ ሲረፍድ።
እንዴት ተጣጣሁ ከኅልሜ
ዋ! ልጅነት ቀለሜ
ላልደርስ እባክናለሁ - ላልችለው ጊዜን ተሸክሜ።
ቀና ብል ለዓይኖቼ ራቀ - እንደ ጉም ተ'ኖ ጠፋ
በሸካራ መዳፌ...
ከጠወለገ እንባ ጋር - ታበሰ በዋዛ ተስፋ።
እንባዬን ከፊቴ ሊጠርግ - ቢነሣ ይቡስ መዳፌ
ክንዴን ዝሎ አገኜውት - የሞተ ተስፋ ታቅፌ።
መንገደኛ ነፋስ ነው - ኅልማችን ሁሉ ከንቱ
የመኖር ቆፈን፥ ውሽንፍር - የጊዜ ብርዱ እትቱ..
እንደ ክረምት ቁልቁለት
እያዳለጠችኝ ሕይወት
ስንት መከራ ልሸከም - ለአንዲት ዓለም - ለአንዲት ኑረት..?
༺❀༻