ወዳጄ አሁን አንተ እያነበብክ ባለህበት ቅፅበት ብዙዎች ሞት አፋፍ ላይ ደርሰው መልካም ስራን ባስቀደምኩ፣ ረመዷንን ሳልዘናጋ በተጠቀምኩ ኖሮ በማለት ይመኛሉ።አሁን አንተ እዚህ ቁጭ ብለህ ይህን በምታነብበት ቅፅበት ብዙዎች ኦክስጅን(አየር) አጥተው ፊታቸው ጠቁሮ ሞት አፋፍ ላይ ደርሰዋል።አንድ ሰዓት ኦክስጅን(አየር) ለመሳብ ብቻ 40,000 ብር ተጠይቀው የሚከፍሉት አጥተው ገርገራ(የሞት ስካር) ላይ ናቸው።ወዳጄ ሆይ! አላህ 1 ሰዓት ስተነፍስ 40,000 ብር ያስከፍልሃልን!??? ቢያስከፍህ ኖሮስ ከፍለህ ትዘልቀው ነበርን? ወዳጄ ሆይ ሁሉንም ነገር እንደ ቀልድ መመልከትህን አቁም ተነስ ወቅቱ ረመዷን ነው።ትንሽ እንኳን ብትዘራ ብዙ የምታጭድበት!ሱና ሰላት ብሰግድ በፈርድ የሚቆጠርበት!በዚህወር በለይለተል ቀድር ቀን እስንፋሳችን የሆነው ቁርዓን ወደ ሰማአ ዱንያ የወረደበት ወር ነው።ወይስ ነፍሳችንን ጎሮሯችን ካልደረሰች አንነቃም?!
ረመዷንን መጠቀም ፍቃድህ ብቻ ሳይሆን ግዴታህም እንደሆነ ልብ በል።ረመዷንን አግኝቶ ሳይጠቀምበት ያለፈው አላህ ከእዝነቱ ያርቀው ጂብሪል(ዐ.ሰ) ይህን ሲል አሽረፈል ኸልቅ (ሰ.ዐ.ወ) አሚን አሉ።
ብልጥ ሁን ወዳጄ!!
#ቆይ አላህን በየትኛው ፀጋው ታስተባብለዋለህ?ንፁህ አየር ስለሰጠህ ወይስ ንፁህ ውሃ ስላጠጣህ ወይስ ከጥቂት ሰዓታት በፊት ስለመገበህ?ወይስ ይህን ታላቅ ወር ስላደረሰህ? አረ በየትኛው እስኪ ንገረኝ?! አላህም ይህን ጥያቄ በሱረቱል ረህማን 31 ጊዜ ደጋግሞ አስፍሮልሃል።
فَبِأَيِّ آلَاءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ
(ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?78፥13
ወይስ አንተ ጥርጣሬ ውስጥ ነህ?
فَبِأَيِّ آلَاءِ رَبِّكَ تَتَمَارَىٰ
ከጌታህም ጸጋዎች በየትኛው ትጠራጠራለህ?53፥55
#አማኝ ልብ ያለን እንደሆነ ይህን ረመዷን ሳንጠቀምበት አይለፈን።ከረመዷን አዲስ የህይወት ካርታ ይዘን መውጣት አለብን።አዲስ ማንነት ያስፈልገናል ረመዷን የመጣው ተቅዋን(የአላህን ፍራቻ) ልንማር ዘንድ ነውና ከረመዷን በኋላ ተቂይ(አላህን ፈሪ) ልብ ማግኘታችን ይከጀላል።ካለዚያ ምናልባት ከዝንጉዎቹ እንዳንገባ ያሰጋል።
በመጨረሻም ምመክርህ ለውጥ ትፈልጋለህ? ስለዚህ ተለወጣ ከለውጥ የሚያግድህ ነገር አለን? ኡማው ያለበት ሁኔታ አሳሰበህ? አማኞች ላይ የሚደርሰው ግፍ እንቅልፍ ነስቶሃላ።
ብሰራቱን ልንገርህ ነገሮችን ሁሉ በአላህ ፈቃድ መለወጥ ትችላለህ።
ከዚህ ሁሉ በፊት ግን አንተ እራስህ መለወጥ አለብህ።አላህም ጥበብ በተሞላው ንግግሩ እንዲህ ብሏል፦
....إِنَّ اللَّهَ لَا يُغَيِّرُ مَا بِقَوْمٍ حَتَّىٰ يُغَيِّرُوا مَا بِأَنفُسِهِمْ ۗ....
....አላህ በሕዝቦች ዘንድ ያለውን ጸጋ በነፍሶቻቸው ያለውን (ኹኔታ) እስከሚለውጡ ድረስ አይለውጥም፡፡....13፥11
#ሰዎች አላህን ከማምለክ እሱን ወደማመፅ ሲዞሩ እሱም ፀጋውን ያነሳባቸውና በቅጣት ይቀይረዋል።እኛም አላህን ከማመፅና ወንጀል ከመስራት ከተቆጠብን አላህ ደግሞ በላኡን አንስቶ በፀጋ ይመልስልናል።ውርደትን አንስቶ የበላይነትን ያጎናፅፈናል።ስለዚህ ጣቶቻችንን ወደሌሎች ከመቀሰራችን በፊት እራሳችን እንመልከት የገዛ እራሳችንን እንለወጥ
ቤተሰብ ይሁኑን
@theamazingquran