ሰበር ዜና ‼️
በግንቦት 01/2013 “ታላቅ የጎዳና ላይ ኢፍጣር በኢትዮጵያ” በሚል በተዘጋጀው ፕሮግራም ላይ ከአዘጋጅ አካላት የተሰጠ መግለጫ::
_______________________________________ሃላል ፕሮሞሽን ከነጃሺ በጎ አድራጎት ደርጅት ጋር በመተባበር ዛሬ ግንቦት 01/2013 “ታላቅ የጎዳና ላይ ኢፍጣር በኢትዮጵያ” በሚል ስያሜ የጎዳና ላይ ኢፍጣር ለማዘጋጀት ህጋዊ ፍቃድ ከሚመለከተው አካል አግኝቶ እንቅስቃሴ መጀመሩ ይታወቃል።
እስከ አሁኑ ሰአት ድረስ ይህንን መልካም አላማ ያዘለ የሰላምና የአንድነት ተምሳሌት የጎዳና ላይ ኢፍጣር ለማከናወን ቀን ከለሊት እየለፋንና ወጤታማ ለማድረግ ጥረት እያደረግን እንገኛለን።
ሆኖም ከመንግስት አካላት ዘንድ የዝግጅት ቦታውን እንድንቀይር የተጠየቅን ሲሆን ይህም ፍፁም ተገቢ አለመሆኑን ለሚመለከታቸው አካላት በማስረዳት እስካሁኗ ሰአት ድረስ ሰንነጋገር ቆይተናል።
ነገር ግን መንግስት በአቋሙ በመፅናቱ እኛም እንደተለዋጭ የተሰጠው ቦታ ላይ ፕሮግራሙን ማከናወን የማንችል መሆኑን
እናሳውቃለን።
ስለዚህም ጥሪ ያደረግንለት ማህበረሰብ በግንቦት 01/2013 በመስቀል አደባባይ የተሽከርካሪ ጎዳና ላይ ልናደርግ ያሰብነውን ፕሮግራም ለመሰረዝ የተገደድን መሆናችንን እንገልፃለን።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በመንግስት በኩል አሁንም የዚህን ፕሮግራም ፍፁም መልካም አላማና ሰላማዊነት ተረድተው ውሳኔያቸውን ማስተካከል እንዳለባቸው እናምናለን።
ስለዚህም እስከመጨረሻው ደቂቃ ድረስ ይህንን ለውጥ ተስፋ በማድረግ ዝግጅታችንን የምንቀጥል ይሆናል።
ከምስጋና ጋር
ለሚመለከተው አካል ሼር በማድረግ እናድር!!
⇩Join us⇩
https://t.me/theamazingquran