ለዛሬ ተዘጋጅቶ የነበረው የአብዮት አደባባይ ኢፍጣር ዝግጅትን መንግስት በቦታው አታድርጉ ማለቱን አዘጋጆቹ ከላይ በተያያዘው ደብዳቤ ገልጸዋል። እኩልነትህን ያልተቀበለ አካል ተሰምቶ መብትህ ሲከለከል በመለማመጥና በመንበርከክ እኩልነትህ እንደማይረጋገጥ ተረድተህ ለክብርህ በጋራ ቁም! «ብርሃናችሁ ይህን ከመሰለ ጨለማችሁ ምን ሊመስል እንደሚችል ተረድተናል» ብለህ በኢፍጣሩ የመሳተፍ ሃሳብ ያልነበረክ ጭምር ለኢፍጣር በቤትህ ያዘጋጀከውን ፈጥር አልያም ቴምርም ቢሆን ይዘህም ቢሆን ከስፍራው ተገኝተህ አፍጥር። ነገሩን አቃለው ለሚመለከቱት ካሉ ጉዳዩ የፈጥር ሳይሆን በእኩል የመታየት ጉዳይ እንደሆነ አስረዳቸው። ዳሩን ባለማስከበራችን መሃሉ ዳር ሆኖ መሪ ተቋም አልባ ወደመሆን እያመራንና መጅሊስን እያጣን እንደሆነ አስታውሳቸው። ሁለተኛ ዜግነቱን አምኖ የተቀበለ ከአብዮት አደባባዩ የፈጥር ዝግጅት መቅረት መብቱ ነው።
Ahmedin jebel
Ahmedin jebel