ናፍቆኛል
አንቺ ውዷ እህቴ ሰው ሀገር ያለሽው፣
የባእድ ሀገራት ነዋሪ የሆንሽው፣
ትዳርሽን ትተሽ ስራ ላይ ያለሽው፣
ባልሽን ልጅሽን የትም የበተንሽው፣
ወላጆችሽ ናፍቀው አንቺ የሌለሽው፣
አይናፍቁሽሞይ ሆነሽ ከወዳኛው።
እኔስ በጣም በጣም በጣምም ናፍቆኛል፣
ሀገር ተመልሰሽ ባይሽ ደስ ይለኛል፣
ወላጆች ቢደሱ ናፍቆታቸው ወጥቶ፣
ትዳር የሌላችሁ ሷሊህ ባል ተገኝቶ፣
ትዳርም ያላችሁ ትዳራችሁ ሰምሮ፣
ባየው ደስ ይለኛል ሁሉ ነገር ሞልቶ።
እህቴ
በውጭ ሀገራት ስራ ከመፈለግ
መጥተሽ ከቤትሽ ውስጥ
ልጅ መውለድ ማሳደግ፣
ይልመድብሽ እህት ተውበሽ በተውሂድ፣
ወድህ ይመርብሽ በቤትሽ ማእረግ።
እስከዛው ነይቺ በዱኣሽ ላይ ፅኒ፣
ትዳርሽ ይናፍቅሽ ዱኒያዋን ቀንሺ።
ከሰው ቤት አንቱታ ይሻላል የራስቤት፣
ጎዶሎው ቢበዛም ስላላት ንግስትነት።
በሰው ከመታዘዝ እንቅልፍን ከማጣት፣
በሀሳብ ከመጓዝ ወዲህ ከመሰልቸት፣
የምትወጪበትን ከመቁጠር እለታት፣
ነይና ተደሺ ወላጅም ይደሰት።
🖊አቡ ተቅይ ቃዒድ
http://t.me/LoveOfMarriage
አንቺ ውዷ እህቴ ሰው ሀገር ያለሽው፣
የባእድ ሀገራት ነዋሪ የሆንሽው፣
ትዳርሽን ትተሽ ስራ ላይ ያለሽው፣
ባልሽን ልጅሽን የትም የበተንሽው፣
ወላጆችሽ ናፍቀው አንቺ የሌለሽው፣
አይናፍቁሽሞይ ሆነሽ ከወዳኛው።
እኔስ በጣም በጣም በጣምም ናፍቆኛል፣
ሀገር ተመልሰሽ ባይሽ ደስ ይለኛል፣
ወላጆች ቢደሱ ናፍቆታቸው ወጥቶ፣
ትዳር የሌላችሁ ሷሊህ ባል ተገኝቶ፣
ትዳርም ያላችሁ ትዳራችሁ ሰምሮ፣
ባየው ደስ ይለኛል ሁሉ ነገር ሞልቶ።
እህቴ
በውጭ ሀገራት ስራ ከመፈለግ
መጥተሽ ከቤትሽ ውስጥ
ልጅ መውለድ ማሳደግ፣
ይልመድብሽ እህት ተውበሽ በተውሂድ፣
ወድህ ይመርብሽ በቤትሽ ማእረግ።
እስከዛው ነይቺ በዱኣሽ ላይ ፅኒ፣
ትዳርሽ ይናፍቅሽ ዱኒያዋን ቀንሺ።
ከሰው ቤት አንቱታ ይሻላል የራስቤት፣
ጎዶሎው ቢበዛም ስላላት ንግስትነት።
በሰው ከመታዘዝ እንቅልፍን ከማጣት፣
በሀሳብ ከመጓዝ ወዲህ ከመሰልቸት፣
የምትወጪበትን ከመቁጠር እለታት፣
ነይና ተደሺ ወላጅም ይደሰት።
🖊አቡ ተቅይ ቃዒድ
http://t.me/LoveOfMarriage