ፍቅርን በትዳር ውስጥ


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: ko‘rsatilmagan


የኩን ሰለፍያ አለልጀዳ አሰለፍይ መነሀጅ የትዳር ክፍል
ተጨማሪ ከፈለጉ
↓↓↓
https://t.me/AbuTeqiyPomeChannel
🌹ፍቅር ማለት
በቃላት ጥምርታ ስም ከመጥራት ውጪ ሊገለፅ የማይችል ረቂቃ ሀሳብ ነው።
ማግኔታውይ የተፈጥሮ ድንቅ ስጦታ ነው።
🌻በትዳር ውስጥ ፍቅር ሲያብብ ምንኛ ያስደስታል
ፍቅርን በትዳር
ድርብ ድርብርብ መታደል ነው።
አስተያየት 📞 @CommentAnd1_bot

Связанные каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


ላላጉበት አላህ መልካም ትዳር ይወፍቃቸው


ላገባችሁት ግን

ይቺን ጀባ
,ለባለ ትዳሮች ብቻ
የባልና ሚስት የሀላል ፍቅር ጨዋታ በግጥም

ባል:
አንቺ የኔ ፍቅር የህይወት ጨረቃ
ልቤ ይከፋዋል ሳጣሽ ለደቂቃ
ሴቶች ብዙ ናቸው አንቺ ግን ልዩ ነሽ
ህይወቴን አድሻት ካጠገቤ ሁነሽ

ሚስት:
አንተ የኔ ፍቅር የህይወት ነፀብራቅ
ፍቅርህ ምግቤ ነው ከጎኔ አትራቅ
ወንዶች ብዙ ናቸው አንተ ግን ልዩ ነህ
ፍቅርህን መግበኝ ካጠገቤ ሁነህ

ባል:
የትዳር አጋሬ የልጆቼ እናት
ደስታዬ አለሜ የሀላል ሚስቴ ናት
ጌታዬ ይመስገን እሷን አድሎኛል
ውዴን የመሰለ ከቶ የት ይገኛል

ሚስት:
የልጆቼ አባት የትጋዳሬ አጋር
ተስፋዬ ብሩህ እስካለሁ ካንተ ጋር
መኖርህ መኖሬ መጥፋትህ መጥፋቴ
ሳጣህ ቅር ይለኛል አትጥፋ ከፊቴ

ባል:
የሽቶ መኣዛ የቴምር ጭማቂ
ሁቢ ማር ወለላ ሁሌም ተናፋቂ
ጣፈጭ ነገር ሁሉ አንቺን ይመስሉኛል
ብቻ ምን ልበልሽ… ቃላቶች ያጥሩኛል!

ሚስት:
የዐይኔ ማረፊያ የህይወቴ ፀደይ
የፊትህ ብርሃን ይበልጣል ከፀሐይ
የረህማን ፅጦታ የጀሊሉ ኒዕማ
አንጀቴ ይርሳል ድምፅህን ስሰማ

ባል:
ሚስቱን የሚመታ የትዳር አጋሩን
የፍቅር አይደለም ሳስበው ነገሩን
ውዷ ባለቤቴ ክብርሽ ይከበር
አንቺን የመታው ቀን እጄ ይሰበር

ሚስት:
እኔ እንክት ልበል እኔ ልሰባበር
እሾህ አይውጋብኝ እንኳንስ መሰበር
የፍቅር አርበኛ ፊትአውራሪ ጀግና
አንተ መውድድ እንጂ ዱላ መች ታውቅና

ባል:
አኔ እዚህ ጎራ አንቺ ወዲያ ማዶ
ልቤ አረረልሽ በፍቅርሽ ማገዶ
የልቤ በረዶ መዳኒቴ ነሽ
ውዷ ባለቤቴ ሁቢ እንዴት ነሽ?

ሚስት:
ፈረስ አይጋልበው በበቅሎ አይደረስ
በርሬ አንዳልመጣ ያለህበት ድረስ
ውዱ ባለቤቴ ፍቅርህ ለበለበኝ
አሁንስ ከብዶኛል በዱኣህ አስበኝ

ታሳቢነቱ በሩቅ ተነፋፍቀው ላሉ የትዳር ጥንዶች

አላህ የዚህን አይነት ሙሀባ መዋደድ መፋቀር ተመኘሁላችሁ ስጦታየ ናት


ፍቅርን በትዳር ውስጥ👇
https://whatsapp.com/channel/0029VanDV3lLNSa1Ls4uw62C


https://t.me/LoveOfMarriage


የሚስት መብቶች
ቀለብና መጠለያ
 አንድ ሰው በአካባቢው ተለምዶ መሰረት የባለቤቱንና የልጆቹን ወጪ የመሸፈን ግዴታ አለበት፡፡

ሚስት ባለ ሃብት ብትሆንም እንኳ፣ ባል ለሚስቱ የምግቧን፣ የመጠጧን፣ የልብሷንና የአስፈላጊ ጉዳዮች ወጪዋን የመሸፈን ግዴታ አለበት፡፡ እንዲሁም ለርሷ ተመጣጣኝ የሆነን መኖሪያ ወይም ማረፊያም ሊያዘጋጅላት ይገባል፡፡
የወጪ መጠን፡ ወጪ የሚለካው እንደ ባልየው የገቢ መጠንና እንደየ አገሩ የአኗኗር ዘይቤ ሲሆን፣ ማባከንም ሆነ መጨናነቅ የሌለበት ሊሆን ይገባል፡፡ አላህ (ሱብሀነ.ወተዓላ) እንዲህ ብሏል፡- ‹‹የችሎታ ባለቤት ከችሎታው ይቀልብ፤ በርሱም ላይ ሲሳዩ የተጠበበት ሰው፣ አላህ ነፍስን የሰጣትን እንጅ አያስገድዳትም፡፡›› (አል ጠላቅ 7)
ይህን ወጪ ሲሸፍን መመጻደቅ፣ እንዲሁም በመጨናነቅ እሷንም ሆነ እራሱን ማዋረድ የለበትም፡፡ ገንዘብ ሲያወጣ፣ አላህ (ሱብሀነ.ወተዓላ) በገለጸው መልኩ በመልካም እሳቤ ሊሆን ይገባል፡፡ ምክንያቱም ይህ ሚስት በባሏ ላይ ያላት መብት እንጂ እርሱ በቸርነቱ የለገሳት አይደለም፤ እናም መብቷን በአግባቡ ሊጠብቅላትና ሊሰጣት ይገባል፡፡
በኢስላም፣ በሚስትና በቤተሰብ ላይ የሚወጣ ወጪ ከባድ ምንዳን ያጎናጽፋል፡፡ ነብዩ (ሶለላሁ.ዐለይሂ.ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹አንድ ሙስሊም ከአላህ እመነዳበታለሁ በሚል እሳቤ በሚስቱ ላይ ወጪ ሲያወጣ ለርሱ ምጽዋት ይሆንለታል፡፡›› (አል ቡኻሪ 5036 /ሙስሊም 1002) በሌላም ዘገባ ነብዩ (ሶለላሁ.ዐለይሂ.ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹በርሷ ብትመነዳባት እንጂ አንተ የአላህን ፊት ከጃይ ሆነህ አንድም ወጪን አታወጣም፤ በሚስት አፍ ውስጥ የምታስቀምጣት ጉርሻ እንኳን ብትሆን፡፡›› (አል ቡኻሪ 56 /ሙስሊም 1628) ወጪ አልሰጥም ያለ ሰው፣ ወይም እየቻለ ማውጣት ካለበት የቀነሰ ሰው፣ በርግጥ ከባድ ወንጀል ውስጥ ተዘፍቋል፡፡ ነብዩ (ሶለላሁ.ዐለይሂ.ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ለአንድ ሰው ወንጀለኛነት፣ የሚያስተዳድረውን ሰው ማንገላታቱ ይበቃዋል፡፡›› (አቡ ዳውድ 1692)
መልካም አኗኗር ወይም ግንኙነት
መልካም አኗኗር በሚለው የተፈለገው መልዕክት መልካም ስነ ምግባር የሚለው ነው፡፡ ልበ ለስላሳነት፤ ለብ ያለ ንግግርን መናገር፤ አንድም የሰው ልጅ ሊርቃቸው የማይችሉ ስህተቶችንና ድክመቶችን ችሎ ማለፍና የመሳሰሉትን ነው፡፡ አላህ ሱብሀነ.ወተዓላ እንዲህ ብሏል፡- ‹‹በመልካምም ተኗኗሩዋቸው፤ ብትጠሉዋቸውም (ታገሱ)፤ አንዳችን ነገር ልትጠሉ፣ አላህም በርሱ ብዙ ደግ ነገርን ሊያደርግ ይቻላልና፡፡›› (አል ኒሳእ 19)
ነቢዩ (ሶለላሁ.ዐለይሂ.ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ከሙእሚኖች መካከል የተሟላው ሙእሚን በስነ ምግባሩ በላጭ የሆነው ነው፤ በላጮቻችሁ ለሚስቶቻቸው በስነ ምግባራቸው ጥሩዎቹ ናቸው፡፡›› (አል ቲርሚዚ 1162)
ነቢዩ (ሶለላሁ.ዐለይሂ.ወሰለም) እንዲህም ብለዋል፡- ‹‹ከሙእሚኖች መካከል የተሟላው ሙእሚን በስነ ምግባሩ ጥሩውና ለሚስቱ ገራገር የሆነው ነው፡፡››
(አል ቲርሙዚ 2612 / አህመድ 24677)
ነቢዩ (ሶለላሁ.ዐለይሂ.ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹በላጫችሁ ለቤተቡ ጥሩዋችሁ ነው፤ እኔ ለቤተሰቤ ጥሩዋችሁ ነኝ፡፡›› (አል ቲርሚዚ 3895) አንድ ሠሐቢይ፣ ነቢዩን (ሶለላሁ.ዐለይሂ.ወሰለም)፡- «አንቱ የአላህ መልክተኛ ሆይ የአንዳችን ሚስት በሱ ላይ ያላት መብት ምንድን ነው?» በማለት ጠየቃቸው፤ እሳቸውም፡ ‹‹ስትበላ ልታበላት፤ ስትለብስም ልታለብሳት፤ ፊቷን ላትመታት፤ ላታዋርዳት፤ በቤትህ ውስጥ እንጂ ላታኮርፋት ነው፡፡›› አሉት፡፡ (አቡ ዳውድ 2142)
መቻቻል
የሴቶች ተፈጥሯዊ ባህሪ ከወንዶች ጋር ይለያያል፤ በመሆኑም ይህን የሚለዩባቸውን ባህሪያት ወንዱ ሊላመደውና አቅልሎ ሊመለከተው ይገባል፡፡ የጋብቻን ሕይወት ከብዙ አቅጣጫ ለማየት ጥረት ማድረግ አለበት፡፡ ማንም ከስህተት ነፃ አይደለም፤ እናም ስህተት ሲከሰት ትዕግስት ማድረግና ከስህተቱ ባሻገር ያሉትን መልካም ጎኖች መመልከት ያስፈልጋል፡፡ አላህ (ሱብሀነ.ወተዓላ)፣ ባልንም ሚስትንም፣ አንዱ የሌላኛውን መልካም ወይም ጠንካራ ጎን እንዲመለከቱ ያሳስባል፡፡ እንዲህ ይላል፡- ‹‹በመካከላችሁም ችሮታን አትርሱ፡፡›› (አል በቀራ 237)

ይቀጥላል……………

https://whatsapp.com/channel/0029VanDV3lLNSa1Ls4uw62C
https://t.me/LoveOfMarriage


ጋብቻ በኢስላም
 ጋብቻ ኢስላም ልዩ ትኩረት ከቸራቸው ማህበራዊ ጉዳዮች አንዱ ነው .

ጋብቻ ኢስላም ልዩ ትኩረት ከቸራቸውና ካበረታታቸው ማህበራዊ ጉዳዮች መካከል አንዱ ነው፡፡ የነብያት ፈለግም ነው፡፡
ኢስላም ለጋብቻ ዝርዝር ድንጋጌና ስርዓትን በመዘርጋት ትኩረት ሰጥቶታል፡፡ የባለ ትዳሮች መብት መከበር የጋብቻው ግንኙነት እንዲጎለብትና እንዲረጋ ያደርጋል፡፡ በመንፈስ የተረጋጋ፣ በእምነቱ የጸና፣ በሁሉም የማሕበራዊ ጉዳዮች ላይ የመጠቀ፣ ሕፃናት በውስጡ የሚያድጉበት የሆነን ስኬታማ ቤተሰብ ለመመስረት ያስችላል፡፡
 
ከነኚህ ኢስላማዊ ድንጋጌዎች መካከል፡
ኢስላም ለአንድ ጋብቻ ትክክለኛነት በባልም ሆነ በሚስት በኩል የግድ ሊሟሉ የሚገባቸው መስፈርቶችን አስቀምጧል፡፡ እነሱም የሚከተሉት ናቸው፡፡
ኢስላም ለሚስትነት ያስቀመጣቸው መስፈርቶች፡
ሙስሊም፣፡
ይሁን እንጂ ኢስላም ከሙስሊሟም ቢሆን በሃይማኖቷ ጠንካራዋን እንድንመርጥ ይመክራል፡፡ ምክንያቱም ወደፊት ለልጆችህ እናትና ተንከባካቢ፣ ለአንተ ደግሞ በመልካም ነገር ላይ የምታግዝህና የምታጸናህ እሷ በመሆኗ ነው፡፡ ነብዩ (ሶለላሁ.ዐለይሂ .ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ባለ ሃይማኖቷን ምረጥ አለያ እጅህ አመድ አፋሽ ትሆናለች›› (አል ቡኻሪ 4802 / ሙስሊም 1466)

ጥብቅና ጨዋ መሆን አለባት፡፡
በዝሙትና በእንዝላልነት የምትታወቅ ሴትን ማግባት ክልክል ነው፡፡ አላህ (ሱብሀነ .ወተዓላ) እንዲህ ይላል፡- ‹‹ከምእመናት ጥብቆቹም ከነዚያ ከናንተ በፊት መጽሐፍን ከተሰጡት ሴቶች ጥብቆቹም (ተፈቀዱላችሁ)›› (አል ማኢዳ 5)
ለዘላለሙ ሊያገባቸው እርም ከተደረጉ መሐሪሞቹ መካከል መሆን የለባትም፡ በጋብቻው አንዲት ሴትን ከእህቷ ወይም ከአክስቶቿ ማለትም ከአባቷ እህት ወይም ከእናቷ እህት ጋር በአንድ ላይ ማግባት አይፈቀድለትም፡፡
ኢስላም ለባልነት ያስቀመጣቸው መስፈርቶች፡
ባል ሙስሊም መሆን አለበት፡፡
በኢስላም፣ ሙስሊም ሴትን ሃይማኖቱ የመጽሐፍ ተከታይ (አህለል ኪታብ) ወይም መጽሐፍ የለሽ ቢሆንም ለካሃዲ መዳር የተከለከለ ነው፡፡ ኢስላም አንድን ወንድ በባልነት ለመቀበል ወንዱ ሁለት ባህሪዎችን የተላበሰ እንዲሆን ይፈልጋል፡፡
በሃይማኖቱ ጽኑ መሆኑና
መልካም ስነ ምግባር የተላበሰ በሆኑ ናቸው፡፡
ነብዩ (ሶለላሁ.ዐለይሂ.ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ሃይማኖቱንና ስነምግባሩን የምትወዱለት ልጃችሁን ከጠያቃችሁ አጋቡት፡፡›› (አል ቲርሚዚ 1084 / ኢብኑ ማጃህ 1967)
የባልና የሚስት መብቶች
አላህ (ሱብሃነ.ወተዓላ) በባልም በሚስትም ላይ ሊጠብቁት የሚገባ የሆነ መብት ሰጥቷቸዋል፡፡ እንዲሁም የጋብቻን ሕይወት የሚያሳምሩና የሚጠብቁ ነገሮችን በሙሉ እንዲፈፅሙ አነሳስቷል፡፡ እነኚህን ጉዳዮች የመጠበቅ ኃላፊነት በሁለቱም ወገን ላይ የተጣለ ነው፡፡ ባልም ሆነ ሚስት አንዳቸው ከሌላኛው የማይቻልን ነገር እንዲፈፅም መጠየቅ የለባቸውም፡፡ አላህ (ሱብሃነ.ወተዓላ) እንዲህ ብሏል፡- ‹‹ለነርሱም (ለሴቶች) የዚያ በነርሱ ላይ ያለባቸው (ግዳጅ) ብጤ በመልካም አኗኗር (በባሎቻቸው ላይ መብት) አላቸው፡፡›› (አል በቀራ 228) የሕይወት ጉዞ ቀጣይነት እንዲኖረው አና የተከበረው ቤተሰብ እንዲጸና ነገርን ማግራራትና ጉድለትን ማለፍ እንዲሁም መለገስ ያስፈልጋል

ይቀጥላል………………………
https://t.me/LoveOfMarriage




አሰለሙአለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካትሁ::

እስቲ ዛሬ በፈገግታ ጀምሩት።


የሆነ ሰው አንድ አካባቢ ከሚስቱ ጋር ተጣልቶ ሚስቱን በዱላ ይቀጣል።

ሲቀጣ ያየው ሰው ዬ. አንተ የማትረባ ጎበዝ ከሆንክ ሚስትን በሚስት አተቀጣትም ይለዋለል።

ከርቀት ነበር እሱ አልሰማውም እና ምን አልከኝ ሲል።

ሚስት ቀድማ ሰምታው ነበር እና ኧረ ተውው ይህንን ሞኝ ዝም ብለህ ምታኝ አለችው ይባላል።


የሀገሬ ሰው የወደቀበት ሚስጥር


Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር) dan repost
ኒካሕና ቃዲ
~
እንደሚታወቀው በኢስላም የትኛዋም ሴት ያለ ወሊይ ፈፅሞ ልታገባ አይፈቅድላትም። ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:–

أَيُّمَا امْرَأَةٍ نُكِحَتْ بِغَيْرِ إِذْنِ وَلِيِّهَا فَنِكَاحُهَا بَاطِلٌ، فَنِكَاحُهَا بَاطِلٌ، فَنِكَاحُهَا بَاطِلٌ
"ያለ ወሊዩዋ ይሁንታ የተገባች የትኛዋም ሴት ጋብቻዋ ውድቅ ነው! ጋብቻዋ ውድቅ ነው! ጋብቻዋ ውድቅ ነው!" [አቡ ዳውድና ቲርሚዚ ዘግበውታል።]

ወሊይ ከሌለስ? በዚህን ጊዜ ኒካሑ በቃዲ ይታሰራል። ስለዚህ ኒካሕ ለማሰር ቃዲ የሚያስፈልገው ወሊይ ለሌላት ሴት ነው ማለት ነው። ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
َ (فالسلطان ولي من لا ولي له)
"አስተዳዳሪ ወሊይ ለሌለው ወሊይ ነው።" [አልባኒይ ሶሒሕ ብለውታል]

በተጨማሪም ወሊዮች ያለ ተጨባጭ ምክንያት ለመዳር ፈቃደኛ ሳይሆኑ ከቀሩ ኒካሑ በቃዲ ይታሰራል። ከዚህ ውጭ አባት ወይም ሌላ ወሊይ ወይም ወኪል ካለ ኒካሑን የሚያስሩት እነሱ እንጂ ቃዲዎች አይደሉም። ወሊይ ወይም ወኪሉ "ሰጥቻለሁ" ካለ፣ አግቢው ወይም ተወካዩ "ተቀብያለሁ" ካለ ኒካሕ ታስሯል። ኹጥባውን (ሸርጥ ካለመሆኑም ጋር) ወሊይ ወይም ሌላ ቦታው ላይ የተገኘ ሰው ሊያደርገው ይችላል።

ኒካሕ ለማሰር የተለየ ውስብስብ መስፈርት የለም። የዐረብኛ ቃላት መጠቀምም አይጠበቅም። መስፈርቶች እስከተሟሉ ድረስ በየትኛውም ቋንቋ ቢሆን መስጠትና መቀበል ከተገኘ ኒካሕ ታስሯል። ስለዚህ በሃገራችን በሰፊው እንደሚደረገው ወሊይ እያለ ቃዲ መጥራት አይጠበቅም። ቃዲዎች ወሊይ ባለበት ሁኔታ ኒካሕ ለማሰር አትቀደሙ። ያለ ስልጣናችሁ ጣልቃ አትግቡ።

ወሊይ የሆናችሁ ሰዎች ደግሞ ቃዲዎችን ለሰርግ ከጠራችሁ እንደማንኛውም እድምተኛ ተስተናግደው ይመለሱ እንጂ እዚያው ተቀምጣችሁ ለነሱ ውክልና አትስጡ። "ልጄን እከሊትን ድሬሃለሁ" ማለት ያቅታችኋል? ምንም የተለየ የተቀመጠ ቃል የለምኮ። እሱም "ተቀብያለሁ" ካለ፣ ቦታው ላይ ሁለት ታማኝ ምስክሮች ከኖሩ ኒካሑ ታስሯል አለቀ። ባገር እያለህ፣ ዐቅልህ ጤነኛ ሆኖ ሳለ እንዴት ከፊትህ ለሚፈፀም ጉዳይ ውክልና ትሰጣለህ? ምንም የሚያስፈራ ነገር የለምና እራስህ ፈፅመው። ሁሉም ነገር በቃዲ በኩል እንዲያልፍ መደረጉ አንዳንድ መረን የለቀቁ ባለስልጣናት በማያገባቸው የእምነታችን ጉዳይ ጣልቃ እንዲገቡ በር እየከፈተ ነው። አንዳንድ ቃዲዎችም ጉዳዩን ያላግባብ የሚጠቀሙበት ሁኔታ አለ።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor


የሚያጓጓ  ትዳር
بسم الله الرحمن الرحيم المقدمة إن الحمد لله، نحمده ونستعينه ونستغفره، ونعوذ بالله من شرور أنفسنا وسيئات أعمالنا، من يهده الله فلا مضل له، ومن يضلل فلا هادي له، وأشهد أن لا إله إلا الله وحده لا شريك له، وأشهد أن محمداً عبده ورسوله، صلي الله عليه وعلى آله وأصحابه ومن تبعهم بإحسان إي يوم الدين وسلم تسليناً كثيراً. أما بعد:
አሰለሙአለይኩም ወረህመቱሏሂ ወበረካትሁ


ለዛሬ

               የሚያጓጓ  ትዳር
ከፍል ሁለት  
     🎁 ለመሆኑ ጋብቻ ለምን ያስፈልጋል?🎀
ቁጥር  1

በክፍል አንድ  እንዳሳለፍ ነው  የተወሰነ የጋብቻ  ጥቅምን  ለማየት  ሞክረን  ነበር።
በዚህ እርዕስ ደግሞ  ጥቅሞቹን በግልፅ በማብራራት  ላይ እናተኩራለን።
መቼም  የጋብቻ  ጥቅምን  በሚገባ   ስንረዳ ነው የሚያጓጓ ትዳርን  የምንናፍቀው።

ለዚህም ነው ኢስላም በጋብቻ ላይ በከፍተኛ ሁኔታ ቅስቀሳ  ያደረገውና ያነሳሳው  እንዲሁም ጋብቻን  እንዲወደድ ያደረገው ግለሰብ፣ ማህበረሰብ፣ እንዲሁም የሰው ልጅ በአጠቃላይ በጋብቻ  ውስጥ ያለውን  ጥቅም እንዳገኝ በማሰብ ነው።

አላህ ሱበሀነ ወተዓላ በዚህ በተዋበ  የጋብቻ ህይወት  ውስጥ ብዙ ተቆጥረው የማያልቁ፣ እንደ ማር የሚጣፍጡ፣ የፀጋ በረከቶችን ስላደረገበት ይህን በረከት የሰው ልጅ እንዲቀምስ  ለማድረግ ሲባል ነው  ኢስላም ሙሉ ትኩረት የሰጠው።

በጥቅሉ ስለ ጋብቻ ይህን ያህል ካልን  የጋብቻ ጥቅሞችን  አንድ ሁለት ብለን  የተወሰኑትን   እንመልከት።

ሀ, #የሰው_ልጅ_የዘር_ሀረግ_እንዲቀጥል_ለማድረግ _………

√የሰው ልጅ የዘር ሀረግ  እንዳይቋረጥ ዘርን ለማብዛት የሚያስችል ምርጡ ዘዴ ወይም የህይወት ጎዳና አማራጭ  የሌለው የተቀደሰው  ጎዳና  ጋብቻ  ብቻ ነው። የምድር ጌጦች ሰዎች እንደመሆናቸው  መጠን  ምድር ሰውን ትፈልጋለች። ከዚህም አኳያ የሰው ልጅ የራሱን አምሳል እየተካ  እስከ ፍፃሜ ቀን ድረስ ለምድር አስተዋፅኦ  የሚያደርግበት  መስመር  ጋብቻ ብቻ ነው።

ይህንኑ  ሀሳብ  ነብዩ መሀመድ ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም በአንድ ሀዲሳቸው ሲገልፁት ብለው  የሰው ልጅ ጋብቻ በማድረግ መባዛት  እንዳለበትና የሰው ዘር ሀረግ  እንዳይቋረጥ  አብክረው  ይመክራሉ።

ኢማሙ አህመድና ኢብኑ ሂባን በዘገቡት ሀደስ  ላይ በማለት  ጋብቻ ውስጥ ሊገኝ የሚችለውን የመባዛትን ጥቅም ቁልጭ አድርገው አሳይተዋል።
በመሰረቱ የዘር መብዛት በራሱ ግለሰባዊ፣ ማህበራዊና፣ጠቅላላ ህዝባዊ (ኡማዊ) ጥቅም እንዳለው ቀደም ሲል በነበረው ህዝብ ውስጥ ከመታወቁም የተነሳ እንዲህ ይባል ነበር  [የበላይነት ለብዙሃን ነው] በማለት በዝቶ የታየው አካል ማህበረሰብ ትልቅ ክብር ይሰጠው ነበር፣ከዚህም አልፎ ይፈሩ እንደ ነበር ታሪክ ያስተምረናል።ከዚህ አንፃር ለጋብቻ  ከፍተኛ ትኩረት  መስጠት  ይኖርብናል።

በጋብቻ ሰበብ  ከሚገኘው  ጥቅም አንዱ የዘር ሀረግ ማስቀጠል ሲሆን  በልጆች ሳቢያ ሊገኙ የሚችሉ ጥቅሞችን ኢማሙል ጋዛሊ  የተባሉት ታላቅ አሊም  ( አል ዚዋጀል ኢስላሚ አስሰኢድ) በተሰኘው ኪታባቸው ላይ ዘርዝረዋል።  ትርጉማቸውን  እነሆ

√ የሰው ልጅ የዘር ሀረግ እንዳይቋረጥ በማድረግ የአላህን  ውዴታ ማግኘት፣

√ረሱል ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም በህዝብ ብዛት ከአንቢያዎች የበላይ እንዲሆኑ በማድረግ የረሱል ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለምን ውዴታ ማግኘት፣

√ መልካም ልጅ ወልዶ ከመልካም ልጅ የሚገኘውን ዱዓ በማግኘት በህይወትም ሆነ በሞት ተጠቃሚ መሆን

√ ልጆች በልጅነት ከሞቱ ለወላጅ የቂያማ ቀን (ሸፈዓ) አማላጅ ስለሚሆኑ  ይህንን  ጥቅም ማግኘት፣

√ የራስን ፍሬ በአይን  በማየት የሚገኝውን ደስታ በልጆች ማግኘት፣

√ በተለይ ወላጆች ወደ እርጅናው  የእድሜ እርከን ሲደርሱ ጧሪ ቀባሪ የሚሆን ልጅ ለማግኘት ያስችላቸዋል።

ከብዙ  በትቂቱ  ጋብቻ ካሉት  ጥቅሞች መካከል እነዚህ ነበሩ።

ኢንሻአላህ
ክፍል ሁለት  ቁጥር 2 ይቀጥላል

https://t.me/LoveOfMarriage


🔻🔻🔻
ለወዳጀዎ ሼር ያድርጉት




የአስጎሪ፣ጭረቻና አካባቢው ኦፊሲላዊ ቻናል ። dan repost
ቢነገር በነገር የማይጠገበው፣
ቢፃፍ ቢተነተን የማይጨረሰው፣
የተውሒድ የሱና ብርሃን ፈጣቂው፣
ውቡ እስልምና የማይበገረው፣
ትናንት እንደነበር ዛሬም የዘለቀው፣
ለነገ ትውልዶች የሚተላለፈው።


ዛሬም ይነገራል በጣም በደመቀው፣
በሱና ብርቅዮች በውድ አላህ ባሮች።

ሰአቱ ቀረ ይህ የሚጠበቀው።
አላህ ከፈቀደ ዛሬ ምሽት 3:30 ላይ 
ይሄው ይጀመራል. አይቀርም በጭራሽ

ተጋባዥ እንግዶች 👇
1⃣ሼህ አቡ ሰላሁዲን

2⃣ወንድም ኑረዲን አል አረቢ


የደዓዋ ርዕስ በሰአቱ ይገለፃል

የፕሮግራሙ ቦታ ኦላይን👇
ተውሒድ እና ሱና በጭረቻ (ግሩፕ)
https://t.me/TewhidAnd_Sunah



እስቲ ሼር አድርጉት ያልሰማው ይሳማ፣
በዚህም ይታወስ ውቡን እስልምና።


ኑ ❗️ አብረን እንስራ dan repost
اَلسَلامُ عَلَيْكُم وَرَحْمَةُ اَللهِ وَبَرَكاتُهُ‎
ፍላጎተው ከሆነ የተወሰኑትን እንጋብዘዎት ↓




የሚያጓጓ ትዳር
بسم الله الرحمن الرحيم المقدمة إن الحمد لله، نحمده ونستعينه ونستغفره، ونعوذ بالله من شرور أنفسنا وسيئات أعمالنا، من يهده الله فلا مضل له، ومن يضلل فلا هادي له، وأشهد أن لا إله إلا الله وحده لا شريك له، وأشهد أن محمداً عبده ورسوله، صلي الله عليه وعلى آله وأصحابه ومن تبعهم بإحسان إي يوم الدين وسلم تسليناً كثيراً. أما بعد:
አሰለሙአለይኩም ወረህመቱሏሂ ወበረካትሁ
የሚያጓጓ ትዳር
ከፍል አንድ
🎁 ጋብቻ🎀
ቁጥር 2

ከቁጥር 1 የቀጠለ
በኒካህ ሀላፊዎች ዙሪያ
በቁጥር 1 ላይ ስለ ኒካህ ሀላፊዎች በዝርዝር አይተናል።
እዚህ ላይ መወሰድ የሚገባው ካባድ
•ጥንቃቄ
① ተራው ሳይጠበቅ (ሌሎች ወሊዮች እምቢ ሳይሉ) ዘሎ ወደ ቃዲ አይኬድም።

.ጥንቃቄ
② ወላጅ ወይም የሚመለከተው ወሊይ በተጨባጭ ምክንያት ከከለከለ ሌሎች አማራጮችን መጠቀም አይፈቀድም። አርፎ መቀመጥ ነው።

.ጥንቃቄ
③ የወሊዮች ምክንያት አሳማኝ ባይሆን እንኳ ያለ ወሊይ ይሁንታ የሚገባበት ጋብቻ አደጋዎች ሊኖሩት ስለሚችሉ ሴቶች ከመግባታቸው በፊት የሚችሉትን ያክል ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባል። ዛሬ ብዙ ሰው ስነ ምግባሩ ወርዷል። ሴቷ ከቤተሰብ ተቀያይማ የገባችበት ጋብቻ ወይ ተመልካች አጥታ የሰቆቃ ህይወት ስትገፋ ወይ ደግሞ እንደ ዋዛ እየፈረሰ "ከሁለት ያጣች" ስትሆን ማየት እየተለመደ መጥቷል። ስለዚህ ከፍ ያለ ስጋት ካለ የቤተሰብ ተቃውሞ ተጨባጭ ባይሆን እንኳ መግባት አይገባም። ወላሁ አዕለም!!
ተጨማሪው ማብራሪያ ከወንድም Ibenu munwor: የተወሰደ ነው።

ለ, የመህር ወይም የጥሎሽ ገንዘብ ፣
ሐ, ከሁለት ያላነሱ ምስክሮች
መ, በመጨረሻ ወይም ቁቡልና ኢጃብ (መስጠትና መቀበል ናቸው ደንቦቹ።

®አላህ ሱበሀነ ወተዓላ ጋብቻ በዚህ መልኩ ህጋዊ ሆኖ እንዲፈፀም በማድረግ የሰው ልጅ የዘር ሀረግ ከመበላሸት ጠበቀው። ሴትንም ልጅ በማንኛውም አጋጣሚ ለችግር እንዳትጋለጥ ጠበቃት።

የሰው ልጅን የስሜት ነበልባል ሰላማዊና ህጋዊ በሆነ መንገድ እንዲወጣበት አደረገለት። እንድሁም በአባትነት እዝነት፣ በእናትነት ርህራሄ በሷሊህ ልጆች የሸበረቀ ቤተሰባዊ ፍቅር እንዲደረጅ አደረገው።

ከዚህ ቤተሰብ ስር የሚበቅሉ ልጆች በጥሩ ሁኔታ አድገው በቤተሰብ ውስጥ ያለውን አስደሳች ህይወት በመንተራስ ለራሳቸውና ለቤተሰቦቻቸው ብሎም ለሀገራቸው ጠቃሚ እንዲሆነ ጋብቻን ትልቅ መሰላል አደረገው። በተጨማሪም አላህ ሱበሀነ ወተዓላ ወንድንና ሴትን ከፈጠረ በኋላ በመዋለድና በመባዛት የሰው ልጅ ዘር እስከ ፍፃሜው ቀን ድረስ
ቀጣይነት እንዲኖረው ለማድረግ የተጠቀመው መንገድ አሁንም ጋብቻን ነው።

ስለዚህ የጋብቻ ስረዓቱና ዕቅዱ የወጣውና የተነደፈው ከሀያሉ አላህ ሱበሀነ ወተዓላ ዘንድ መሆኑ ግልፅ ነው።
ነገር ግን ይህን መለኮታዊ ህግ በምድር ላይ ተግባራዊይ ይሆን ዘንድ አላህ ሱበሀነ ወተዓላ ለሰው ልጅ የሰጠው ገና ከጅምሩ አደምና ሀዋን በፈጠረ ጊዜ ነው። ሀያሉ አላህ ይህንንም ያደረገው የሰው ልጆች ጥንድ እንዲሆኑ በማሰብና ጋብቻን ዋና አላማ በማድረግ የጋርዮሽ ህይወትን ገና ከጅምሩ እንዲለማመዱ ለማድረግ በአደምና በሀዋ ተጀምሯል። ይህንንም ሀሳብ አላህ አዘወጀል በተከበረው ቁረዓኑ ውስጥ እንዲህ ሲል ጠቅሶታል:-

يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّاسُ ٱتَّقُوا۟ رَبَّكُمُ ٱلَّذِى خَلَقَكُم مِّن نَّفْسٍۢ وَٰحِدَةٍۢ وَخَلَقَ مِنْهَا زَوْجَهَا وَبَثَّ مِنْهُمَا رِجَالًۭا كَثِيرًۭا وَنِسَآءًۭ ۚ وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ ٱلَّذِى تَسَآءَلُونَ بِهِۦ وَٱلْأَرْحَامَ ۚ إِنَّ ٱللَّهَ كَانَ عَلَيْكُمْ رَقِيبًۭا
እናንተ ሰዎች ሆይ! ያንን ከአንዲት ነፍስ (ከአዳም) የፈጠራችሁን ከእርስዋም መቀናጆዋን (ሔዋንን) የፈጠረውን ከእነርሱም ብዙ ወንዶችንና ሴቶች የበተነውን ጌታችሁን ፍሩ፡፡ ያንንም በርሱ የምትጠያየቁበትን አላህንና ዝምድናዎችንም (ከመቁረጥ) ተጠንቀቁ፡፡ አላህ በእናንተ ላይ ተጠባባቂ ነውና፡፡
(አል ኒሳዕ :1)

እንድሁም በሌላ አንቀፅ እንድህ ይለናል

وَمِنْ ءَايَٰتِهِۦٓ أَنْ خَلَقَ لَكُم مِّنْ أَنفُسِكُمْ أَزْوَٰجًۭا لِّتَسْكُنُوٓا۟ إِلَيْهَا وَجَعَلَ بَيْنَكُم مَّوَدَّةًۭ وَرَحْمَةً ۚ إِنَّ فِى ذَٰلِكَ لَـَٔايَٰتٍۢ لِّقَوْمٍۢ يَتَفَكَّرُونَ
ለእናንተም ከነፍሶቻችሁ (ከጎሶቻችሁ) ሚስቶችን ወደእነርሱ ትረኩ ዘንድ መፍጠሩ፣ በመካከላችሁም ፍቅርንና እዝነትን ማድረጉ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው፡፡ በዚህ ውስጥ ለሚያስተውሉ ሕዝቦች ተዓምራቶች አልሉ፡፡ (አል ሩም :21)

ከነዚህ ድንቅ የቁረዓን አንቀፆች የምናገኘው ቁም ነገር
1አንቀፅ ላይ,አላህ ሱበሀነ ወተዓላ ይህን ምድር አጣቦ የሚገኘው የሰው ዘር ከአንዲት ነፍስ የጀመረ እንደሆነና ከዚያችም ነፍስ ደግሞ የህይወት ጓደኛዋን በመፍጠር ከዚያም በሁለቱ የትዳር (የጥምርታ)ህይወት የሰውን ልጅ እንዳስገኘ የገለፀ መሆኑን ያሳያል።

2,አንቀፅ ላይ ደግሞ ከዚያች ከአንዲት ነፍስ መቀናጆዋን ከፈጠረ በኋላ በሁለቱ መካከል ለሰው ልጅ እጅግ አስፈላጊ እና አንገብጋቢ የሆኑትን #ፍቅርን እና #እዝነትን ማድረጉ የአላህን ምንነት ለመረዳት ከሚያስችሉ አስደናቂ ምልክቶች መካከል ናቸውና አስተውሏቸው። ምክንያቱም የአላህ ፀጋን በመረዳት ከአመስጋኞች እንዲትሆኑ በማለት ያሳስበል።

ስለዚህ ጋብቻ የአላህ ፍቃድ፣ ትዕዛዝም ነው።በመሆኑም የሚያጓጓ ትዳር ለመመስረት ሂዴቶችን በሚገባ ማለፍ ይጠይቃል።


ኢንሻአላህ
ክፍል ሁለት
ቁጥር 1 ይቀጥላል …………
http://t.me/LoveOfMarriage


ፕሮግራሙ ላይ ያላችሁን አስተያየት ጠቁሙኝ።

ጥሩ ነው ይቀጥል 🍇


በዝቷል ይቀነስ 🍉

ሰልችቶናል ይቋረጥ 🔪






የሚያጓጓ  ትዳር
بسم الله الرحمن الرحيم المقدمة إن الحمد لله، نحمده ونستعينه ونستغفره، ونعوذ بالله من شرور أنفسنا وسيئات أعمالنا، من يهده الله فلا مضل له، ومن يضلل فلا هادي له، وأشهد أن لا إله إلا الله وحده لا شريك له، وأشهد أن محمداً عبده ورسوله، صلي الله عليه وعلى آله وأصحابه ومن تبعهم بإحسان إي يوم الدين وسلم تسليناً كثيراً. أما بعد:
አሰለሙአለይኩም ወረህመቱሏሂ ወበረካትሁ
               የሚያጓጓ  ትዳር
ከፍል ሁለት  
                 🎁 ጋብቻ🎀
ቁጥር  1

  የሚለው  የአረብኛ  ቃል ሲሆን  ቋንቋዊ ትርጉሙ   ጥንድነት(ጥምርታነት) የሚለውን  ፍች  ይሰጠናል። መሰረታውይ ትርጉሙ  ይህ ከሆነ አላህ ሱበሀነ ወተዓላ ይህንን  የጥንድነት ህይወት  በሰው ልጅ ላይ ብቻ ሳይሆን  በአጠቃላይ  በፈጠራቸው ላይም አድርጎታል።  ለምሳሌ;  እንስሳት፣እፅዋት፣ህይወት ያላቸው ነገሮች  በአጠቃላይ ጥንድ ጥንድ አድርጎ መፍጠሩን  በተከበረው ቁርዓን  ውስጥ  እንዲህ ሲል ገለፀ፣
وَمِن كُلِّ شَىْءٍ خَلَقْنَا زَوْجَيْنِ لَعَلَّكُمْ تَذَكَّرُونَ
ትገነዘቡም ዘንድ ከነገሩ ሁሉ ሁለት (ተቃራኒ) ዓይነትን ፈጠርን፡፡ አል ዛሪያት 49

ከዚህ አንቀፅ እንድንገነዘብ ለማድረግ ከተጠቀመባቸው ነገሮች አንዱ ከሁሉም ፉጡሮች ጥንድ (ሁለት ተቃራኒ) የሆኑ ነገሮችን መፍጠሩ ነው።{ሁሉም ስንል} የሰው ልጅ እዚህ ቃል ውስጥ የሚካተት ይሆናል። የሰው ልጅ ጥንድ ሆኖ ለመፈጠሩ በተጨማሪ ቁርዓን  በግልፅ እንዲህ ሲል ይነግረናል;

يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّاسُ إِنَّا خَلَقْنَٰكُم مِّن ذَكَرٍۢ وَأُنثَىٰ وَجَعَلْنَٰكُمْ شُعُوبًۭا وَقَبَآئِلَ لِتَعَارَفُوٓا۟ ۚ إِنَّ أَكْرَمَكُمْ عِندَ ٱللَّهِ أَتْقَىٰكُمْ ۚ إِنَّ ٱللَّهَ عَلِيمٌ خَبِيرٌۭ
እናንተ ሰዎች ሆይ! እኛ ከወንድና ከሴት ፈጠርናችሁ፡፡ እንድትተዋወቁም ጎሳዎችና ነገዶች አደረግናችሁ፡፡ አላህ ዘንድ በላጫችሁ በጣም አላህን ፈሪያችሁ ነው፡፡ አላህ ግልጽን ዐዋቂ ውስጥንም ዐዋቂ ነው፡፡

በማለት በመጀመሪያው  መስመር ላይ የሰውን ልጅ ሀለት ተቃራኒ ፆታ ካላቸው  አካላት ከወንድና ከሴት የፈጠረው መሆኑን በግልፅ ያሳያል።  ይህ የሰው ልጅ የመፈጠሪያና የመራቢያ መንገዱ ወይም ዘዴው ግብረ  ስጋ ግንኙነት ሲሆን የዚህም ህጋዊ መንገድ ጥንድነት /ጥምርታ/ በሸሪኣዊ  ፍቹ  #ጋብቻ በመባል የሚታወቀው የትዳር ህይወት ነው።

ለዚህም የትዳር ህይወት እስልምና የራሱ የሆነ ህግና ስርዓት አዘጋጅቶለታል። በመሰረቱ በሸሪኣ  ጋብቻ ወይም ትዳር ማለት  በሁለት ተቃራኒ ፆታዎች በወንድና በሴት መካከል  በፍቃደኝነት  የሚደረግ  ህጋዊ ግንኙነት ማለት ነው።

አላህ ሱበሀነ ወተዓላ የሰውን ልጅ ግንኙነት ልክ እንደ እንስሳ ልቅና ስረዓተ ቢስ አላደረገውም። ይልቁንም ከሰው ልጅ ክብርና ማእረግ ጋር ሊሄድ የሚችል  ተስማሚና ጣፋጭ ህግን በማዘጋጀት የሰው ልጅ ክብሩን እንዲጠብቅ አድርጎታል።

ይህ በእስልምና ውስጥ የተዘረጋው የጋብቻ ደንብ(ስነ ስረዓት) የሁለቱ ተጋቢዎችን ግንኙነት የተከበረና ህጋዊ ከማድረጉ የተነሳ   ሰዎች ሲጓጉለት፣ሲናፍቁት፣ቦታ ሰጥተውት ልዩ ሱያደርጉት ይታያል። 
ደንቦቹም ………
ሀ, መጀመሪያ የባልና  የሚስት ሙሉ ፍቃደኝነት (ይህ ሲባል በሴት ልጅ በኩል እሷን ሀላፊ ሆኖ የመዳር መብት ያለው አካል ለኒካህ ሀላፊ ነው።

የዚህን ማብራሪያ ወንድም ኢብኑ ሙነወር አላህ ይጠብቀውና  በሚገባ ገልፆታል
ለኒካሕ ሃላፊ (ወልይ) የሚሆኑት እነማን ናቸው?
============================
: ያለ ሃላፊ (ወሊይ) ኒካሕ ዋጋ አለው?
~~~~~~~~~~~~~~~~
በመጀመሪያ ወሊይ ለኒካሕ ወሳኝ ቅድመ ሁኔታ ነው። ያለ ወሊይ እውቅና የተፈፀመ ጥምረት ፈፅሞ ከጋብቻ አይቆጠርም። ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል:– 
(لا نكاح إلا بولي )
"በወሊይ ካልሆነ በስተቀር ኒካሕ የለም!!" [አልባኒ ሶሒሕ ብለውታል።]

* ስለዚህ ፈትም ሆነች ልጃገረድ አንዲት ሴት ያለ ወሊይ ፈፅሞ ልታገባ አይፈቅድላትም። ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል:–  

أَيُّمَا امْرَأَةٍ نُكِحَتْ بِغَيْرِ إِذْنِ وَلِيِّهَا فَنِكَاحُهَا بَاطِلٌ، فَنِكَاحُهَا بَاطِلٌ، فَنِكَاحُهَا بَاطِلٌ
"ያለ ወሊዩዋ ይሁንታ የተገባች የትኛዋም ሴት ጋብቻዋ ውድቅ ነው! ጋብቻዋ ውድቅ ነው! ጋብቻዋ ውድቅ ነው!" [አቡ ዳውድና ቲርሚዚ ዘግበውታል።]

ክፍል ሁለት:– ወሊይ የሚሆኑት እነማን ናቸው?
~~~~~~~~~
ወሊይ የሚሆኑት በቅደም ተከተል የሚከተሉት ናቸው:–
1ኛ:– አባት፣
2ኛ:– የአባት አባት፣
3ኛ:– ወንዶች ልጆች፣
4ኛ:– ወንድም፣
5ኛ:– የወንድም ልጆች፣
8ኛ:– አጎቶች (የአባት ወንድም) …እያለ ይቀጥላል።

ማሳሰቢያ: –

* ወሊይ የሚሆነው በአባት በኩል ያለ ሃላፊ ብቻ ነው። በእናት በኩል ያሉትን አያካትትም። ሌላው ቀርቶ በእናት ብቻ የሚገናኙት ወንድም እንኳ ወሊይ መሆን አይችልም።
* በአባትም በእናትም የሚገናኝ ወሊይ በአባት ብቻ ከሚገናኘው ይቀደማል። ለምሳሌ በአባትም በእናትም የሚገናኙት ወንድም በአባት ብቻ ከሚገናኙት ይቀድማል።
* ተቀዳሚ የሆነው ወሊይ በቀላሉ የማይገኝ ከሆነ ተራውን ጠብቆ ሌሎች ወሊዮች ኃላፊነቱን ይወስዳሉ።

* አንድ ሰው ወሊይ ለመሆን
~~~~~~~~~~~~~~~~~
• ሙስሊም መሆን አለበት። ካፊር ወሊይ ሆኖ ሊድር አይችልም።
• አእምሮው ጤነኛ መሆን አለበት።
• ለአቅመ ኣደም የደረሰ መሆን አለበት።
• ወንድ መሆን አለበት።

* ወሊይ ከነ ጭራሹ ከሌለ ወይም ለአቅመ ኣደም የደረሱ ካልሆኑ ቃዲ ወሊይ ይሆናል።
َ (فالسلطان ولي من لا ولي له )
"አስተዳዳሪ ወሊይ ለሌለው ወሊይ ነው።" [አልባኒ ሶሒሕ ብለውታል]

* ወሊይ (ሃላፊ) በቅርብ ከሌለ ሌላ ሰው መወከል ይችላል። ውክልናው እንዲሁ "ይበጃል ላልከው ዳርልኝ" አይነት ክፍት ሊሆን ይችላል። ወይም "ለእከሌ ዳርልኝ" የሚል የተገደበ ሊሆን ይችላል።
* የሸሪዐ ቃዲዎች በሌሉበት ሃገር የኢስላማዊ መርከዝ ሃላፊ ወይም የመስጂድ ኢማም ወሊይ ሆኖ መዳር ይችላል።
* ወሊዩ ሺርክ ላይ የተዘፈቀ ወይም ሶላት የማይሰግድ ከሆነ ተራው ተጠብቆ ወደተሻሉት ኃላፊነቱ ይሻገራል።
* ወሊዩ #ያለ_ተጨባጭ_ምክንያት ለመዳር ፈቃደኛ ካልሆነ ተራው ተጠብቆ ወደተሻሉት ኃላፊነቱ ይሻገራል። ሌሎችም ፈቃደኞች ካልሆኑ ወደ ቃዲ ይሻገራል።
======================
🖼
ኢንሻአላህ  ቁጥር 2 ይቀጥላል
🖊ወንድማችሁ  አቡተቅይ ቃዒድ 



አደራ ለአላህ ስትሉ ሼር አድርጉት
በአሁኑ ሰአት ድንበር የሚታለፍበት  ተግባር ሆኖል።

ከልብ ነው ከታች ጠቁሙኝ



ሼር ካደረጋችሁ                📢



ሼር  ካላደረጋችሁት              🔇 

http://t.me/LoveOfMarriage


ናፍቆኛል

አንቺ ውዷ እህቴ  ሰው ሀገር ያለሽው፣
የባእድ ሀገራት ነዋሪ የሆንሽው፣
ትዳርሽን  ትተሽ   ስራ ላይ ያለሽው፣
ባልሽን  ልጅሽን   የትም የበተንሽው፣
ወላጆችሽ ናፍቀው  አንቺ የሌለሽው፣
አይናፍቁሽሞይ  ሆነሽ ከወዳኛው።


እኔስ በጣም በጣም በጣምም ናፍቆኛል፣
ሀገር ተመልሰሽ ባይሽ ደስ ይለኛል፣

ወላጆች ቢደሱ ናፍቆታቸው ወጥቶ፣
ትዳር የሌላችሁ ሷሊህ ባል ተገኝቶ፣
ትዳርም ያላችሁ  ትዳራችሁ ሰምሮ፣
ባየው ደስ ይለኛል ሁሉ ነገር ሞልቶ።

እህቴ
በውጭ ሀገራት   ስራ ከመፈለግ 
መጥተሽ ከቤትሽ ውስጥ
                    ልጅ መውለድ ማሳደግ፣
ይልመድብሽ እህት ተውበሽ በተውሂድ፣
ወድህ ይመርብሽ   በቤትሽ ማእረግ።


እስከዛው  ነይቺ  በዱኣሽ ላይ ፅኒ፣
ትዳርሽ ይናፍቅሽ ዱኒያዋን ቀንሺ።

ከሰው ቤት አንቱታ ይሻላል የራስቤት፣
ጎዶሎው ቢበዛም  ስላላት ንግስትነት።

በሰው ከመታዘዝ  እንቅልፍን ከማጣት፣
በሀሳብ ከመጓዝ  ወዲህ ከመሰልቸት፣
የምትወጪበትን ከመቁጠር እለታት፣
ነይና ተደሺ ወላጅም ይደሰት።

🖊አቡ ተቅይ ቃዒድ
http://t.me/LoveOfMarriage


የሚያጓጓ   ትዳር

ለሚወዱት ውድ ጓደኛዎ የሚሰጥ(ሼር) የሚደረግ   ምርጥ  ስጦታ

ከ ____________
ለ________________

                   ምስጋና
ምስጋና  ለአላህ ሱበሀነ ወተዓላ ነው።አሏሁ ሱበሀነ ወተዓላ  እስልምናን ከመስጠት  ጀምሮ እጅግ  በርካታ ስፍር ቁጥር የማይደረስባቸው ውለታዎችን
ለዋለልኝ  ውለታሁሉ አመሰግነዋለሁ፣ ።

    የሚያጓጓ  ትዳር
ክፍል   አንድ
"بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በኾነው፡፡" በአላህ አዘወጀል ስም
ፁሁፌን  አሀድ  ብዬ እጀምራለሁ።

                       መግቢያ

ጋብቻ እንደሚታወቀው ሀይማኖታውይ ስረዓት ከመሆኑ ባሻገር  የሰው ልጅ ከተፈጠረበት ጊዜ አንስቶ ያለ ህግና የህይወት ዑደት ነው። ወንድ ሴትን  ሴትም  ወንድን መፈለጉና መፈላለጉ  ተፈጥሮአዊ  ባህሪያችን ሆኖ ሳለ አብዘሀኛው  የአለማችን  ማህበረሰብ  ይህን የመሰለ ሀይማኖታውይና ተፈጥሮአዊ የሰው ልጆች ስረአትን  ሲጠቀሙበት አይታይም፣ እንዳውም  ሲያራክሱት ሲንቁት  ይታያሉ። በተለይ ወጣቱ ክፍል አላህ ያዘነለት ብቻ ሲቀር  ይህን ምርጥ የህይወት መድረክ  በመራቅ አላህ ባይፈቅደው መጥፎ ተግባር ህይወቱን በከንቱ ሲያሳልፍ  ይስታወላል።

ትዳርን  ከመመስረት  ይልቅ በስሜታዊ የሸይጧን ፍቅር ውስጥ በመግባት የጋብቻን ክብርና  ታላቅነት ዘንግተው  በደመነፍሳቸው በመጓዝ  ጋብቻ ውስጥ ያለውን  በእዝነት፣ በርህራሄ፣ በልጅ፣ እንድሁም  በውዴታ የታጀበውን እውነተኛ ፍቅር አጥተው በመንከራተት ላይ  ይገኛሉ።

የጋብቻ ህይወትን ለመቅሰም የታደሉት ጥቂቶች ደግሞ በጋብቻ አለም ሊገኝ  የሚችለውን  ደስታና እርካታ እንድሁም የመንፈስ እርጋታ  አጥተው እውነተኛ የፍቅር ህይወትን  ባለማወቅና   ባለማግኘት  በትዳር ህይወታቸው  ደስታን  አጥተው   የመከራ  ህይወት  ፣የተንዛዛ  ወዝ የሌለውን   አሰልቺ  ህይወት  ሲገፉ   ውስጥ  ይነካል።


እንድህ አይነቱን ህይወት በመምራት ላይ የሚገኙ  በርካታ  ባለትዳሮች  ሊኖሩ እንደሚችሉ  በመገመት   ለዚህ  የሰፋ  ችግር  ሁነኛ መፍትሄ  ለማስቀመጥ  የተለያዩ  የመፍትሄ ሀሳቦችን  ለማቅረብ እንሞክራለን።


በአጠቃላይ  ከስሙ  እንደምትረዱት "የሚያጓጓ  ትዳር"  በሚል  ፕሮግራም  በክፍል  በክፍል አድርገን  እየከፋፈልን   ሰፋ  ያለ ጊዜ  ሰጥተ ነው  የምንማማር  መሆኑን ለማሳሰብ  እወዳለሁ

ከፍል ሁለት  ይቀጥላል
ኢንሻአላህ

✍አቡ ተቅይ ቃዒድ
http://t.me/LoveOfMarriage


አሰለሙአለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካትሁ


ከአመታት በፊት ተጀምረው የነበሩ በተለያየ ምክንያት ተቋርጠው የኖሩ ተከታታይ ፁሁፎች ነበሩ። ከዛሬ ከነገ ነገሮች ይስተካከላሉ እና ባለበት ለመቀጠል ተስቦ የነበረ ቢሆንም። ከመዘገየቱ. የተነሳ የሀሳብ መቆራረጥ እንዳይኖር

አላህ ከፈቀደ እንደ አዲስ አንዱን ፁሁፍ ብቻ እንጀመረዋለን።

ርዕሱ
የሚያጓጓ ትዳር


እንሻአላህ

ከዚህ
     በኋላ   በትዳርም ላይ ላሉ ፣  ገና  ወደ ትዳር  አለም ለመግባት  በዝግጅት ላይ  ላሉ  ፣እንድሁም  ከነጭራሹ  ጋብቻ  ትዝ ላላቸው  ወገኖች  በሙሉ  ጠቃሚ  የሆኑ  ምክሮችን ከቁረዓን  ከሀዲስ፣ ከአሊሞች፣ ከኡዝታዞች  እንዲሁም   ከተሞክሮ  ከተገኙ ምክሮች እየመራረጥን   አላህ እሰከፈቀደ  ድረስ ማቅረባችንን  እንቀጥላለን።


በተጨማሪ  ለተወሰነ ጊዜ ኢንሻአላህ
በቋሚነት  በሳምንት  አንድ  ቀን   በአንድ  እርእስ ላይ  በክፍል  በክፍል  ማቅረብ  እንጀምራለን ፣

#ሰኞ     የሚያጓጓ  ትዳር (ጥምርታ) 



በሚሉ  እርዕስ ላይ  እናተኩራለን።


በእርግጠኝነት  በጣም  ማራኪ የሆነ  ድንቅ ፕሮግራም ነው እንደምትወዱት  ተስፋ አደርጋለሁ
አላህ  ትዳርን በፍቅር  አስውቦ አሟልቶ ሰጥቶን  እንመካከር  #Leafet ብላችሁ አትውጡ ችግር ካለ በውስጥ መስመር አድርሱኝ  እንማማር።

እውነተኛ  ትዳር ለሚፈልጉ  ወገኖች ሊንኩን አሰራጩላቸው 

አላህ እንዳዘዘን 
በትዳር እንዋብ
በትዳር እናብብ
በትዳር እንርካ
ዲን እንዳዘዘን ተግብረን በዱኒያም በአሄራ ከደስተኞች ጋር እንሁን።



20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.