«በአዲሱ ዘመቻ እና ድሎቹ እንገናኛለን!» -አርበኛ ዘመነ ካሴ
“ከግድያ ሙከራ መትረፍ የኦሎምፒክ ውድድር ቢሆን ኖሮ የወርቅ ሜዳሊያ አሸንፍ ነበር።"-ይህን ያለው ከ600 ጊዜ በላይ ከግድያ ሙክራዎች እንዳመለጠ የሚነገርለት የቀድሞው የኩባ መሪ ፊደል ካስትሮ ነበር።
የግድያ ዜና በ 2025ቱ ( የፈረንጆች አቆጣጠር) የጃፓን ቶክዮ የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና አንዱ የውድድር አይነት ከሆነ በሰሞኑ የነ አብይ አህመድ የተስፋ መቁረጥ "የገደልነው ዘመቻ" ብቻ ወርቅ ባላገኝ የብር ሜዳሊያ አላጣም። የመለያ ቁጥሬም 21-12 ይሆናል።
•በሁሉም ረገድ፣ በሁሉም ሰበብ እና ምክንያት ልትጠልፉኝና ልታጠለሹኝ የሞከራችሁ እና በየቀኑ የምትሞክሩ ሰዎችና ቡድኖች መጨረሻችሁ ውርደት እና የእድሜ ልክ መሸማቀቅ እንደሚሆን ዛሬ ድረስ በጥቂቱ በምታውቁት፣ነገና ከነገ ወዲያ ደግሞ ሰፊውን ማንነቱን በምትረዱት በዘመነ አምላክ ስም እነግራችኋለሁ። አምላኬ ይቅር ይበለኝና ብዙዎች አይሆን ሞክረውኝ፣ ደጋግመው ሞካክረውኝ መጨረሻቸው የሌባ ጣት ጥፍራቸው ውስጥ መደበቅ ሆነ። (ድንግል ማርያምን ያሳዝኑኛል።)
የቀብሮ ጫጫታ የማያስደነብረኝ፣ጀርባዬ ላይ ሊወጣ የሚሞክረው ሁሉ ቢሳካለት እንኳን የማይከብደኝ "ዝሆን" ነኝ።በቃ እንደዚህ ነው የሰራኝ።
•ከንግስና ዙፋንና ዘውድ ጀምሮ በተለያዩ የህዝብ አስተዳደር እርከኖች እና ሃላፊነቶች እስከ ጦር ሜዳ ውሎዎች በብዙ ፈተና መሃል እያለፈ ሃገር የገነባ ቤተሰባዊ ማንነትና የመከራ ዘመን በቅጡ የገነባኝ ሰው ነኝ።በአለሙ ውስጥ በማንኛውም ሁኔታ እንደ ህፃን በደስታና በሃዘን በእምባ የምሟሟ ተራ ሰው፣ ምድራችን በድንገት ጨረቃ ብትሆን እንኳን የማይጨንቀኝ ልበ-ሙሉ "ጨካኝ" ፍጡር ነኝና በጅራፍ ጩኸት ልታስደነብሩኝ የምትሞክሩ የዋሆች አትድከሙ።
•እኔና ጓዶቼ ፣ከትውልድ አጋሮቻችን ጋር እንደምናሸንፍ የተፃፈው የእናቶቻችን ማህፀን ውስጥ እያለን ነው።ወኔና ድል አድራጊነትንም የተጋትነው በእትብት ነው።ይህ ትውልድ አሸናፊ ትውልድ ነው።ልድገመው!ይህ ትውልድ የአሸናፊነት እጣፋንታውን ግንባሩ ላይ ተነቅሶ ወደዚህ ምድር የተላከ ትውልድ ነው። እየታገለ ነው ፥ድል አድርጎ የአማራን ህዝብ ህልውና በፀሃይ ፊት ያረጋግጣል።
ይህ ትግል ለትግሉ ብቻ የተሰጠ እና የሚሆን ራሱን የቻለ ልዩ ነፍስ ይፈልጋል። እንጨት እንጨት የሚል ሰዋዊና ፖለቲካዊ ስብእና ተይዞ ፥ነፍስን ቅናት፣ምቀኝነትና ተንኮል በሚባሉ የመንፈስ ቆሻሾች መርዞ ታጋይም አታጋይም መሆን አይቻልም። እና "ልፋ ያለው በህልሙ ዳውላ ይሸከማል" እንዲሉ በብዙ የተበከለች ነፍስ ተሸክማችሁ ለ ደካማ ተልእኮ አጉል የምትደክሙ ወገኖች ከድል ሃውልት ውጭ ከፊታችን መቆም የሚችል ነገር የለምና ነፋስን ለማሰር በመሞከር ጊዚያችሁን አታጥፉ። ይህ ትውልድ እያለ የአማራን ህዝብ ጉልበት መሬት አታስነኩትም። በኩራት ቆሞ ገጥሟችኋል፥ ያሸንፋችኋል።
እና በባንዶች ፊታውራሪ በተመስገን ጥሩነህ አገላለፅ "ዘመነን አስወግደነዋል፥ ከዚህ በኋላ ድምፁን አትሰሙትም" የሚለውን የሰሞኑን ብልፅግናዊ አዲስ መዝሙር ስቃችሁበት እለፉ።ሌት ተቀን እያቀድንላቸው ነው።ከጠፋሁም ያጠፋኝ የጠላት ስሥ ብልት ልየታ ቢዚ አድርጎኝ ነው።የዘመነ ትውልድ የአለማችን እድለኛና ገድለኛ ትውልድ ነው።መንጋው እንዲበተን እረኛውን ምታው የቆዬ ብሂል በኛ ትግል ውስጥ አይሰራም።ትግሉ ሚሊዮን እረኞች ከበውታል፥መንጋው ራሱ ረኛ ከሆነ አመታት አልፈዋል።
ዘመነ የእናንተን ሞት ቆሞ ለማዬት ለተአምር ተፈጠረ እንጅ በዘመነ መጥፋት ለአንድ ሴኮንድ እንኳን የሚንገራገጭ ትግል የለም። ይህ ትውልድ ከቀደምቶቹም ከነገዎቹም ትውስታና መንፈስ ቀድቶ የትሸከመውና ያጎለበተው ከእድሜውና ተሞክሮው በላይ ያበሰለው አንዳች ነገር አለው።ስለሆነም ያሸንፋል።
ይኸው ነው! በአዲሱ ዘመቻ እና ድሎቹ እንገናኛለን!!
አዲስ ትውልድ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ
አርበኛ ዘመነ ካሴ
ጥቅምት 10 ቀን-2017 ዓ.ም
#Amhara #Ethiopia