የብልጽግና ፓርቲ ጉባኤ ከጥር 23 እስከ 25 ይካሄዳል – አቶ አደም ፋራህ
AMN-ታህሣሥ 16/2017 ዓ.ም 2ኛው የብልጽግና ፓርቲ ጉባኤ ከጥር 23 እስከ 25 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚካሄድ የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት እና ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አደም ፋራህ ተናገሩ። በአንደኛው ታሪካዊ የብልጽግና ፓርቲ የተቀመጡ አቅጣጫዎች እና ውሳኔዎችን በመፈጸም በኩል አበረታች ሥራዎች መፈጸማቸውን የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህ ተናግረዋል። ባለፈው የፓርቲው ጉባኤ የተቀመጡ አቅጣጫዎች በኢኮኖሚ፣ በፖለቲካዊ፣ በማህበራዊ፣ በዲፕሎማሲ...