የድሬዳዋ ስታድየም የፊፋን ሙሉ ፍቃድ እየጠበቀ ነው
ኢትዮጵያ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) መስፈርት ያሟላ ስቴድየም ባለማዘጋጀቷ ዋናው የወንዶች ብሔራዊ ቡድን ባለፉት አራት ዓመታት ዓለም አቀፍ ጨዋታዎቹን በገለልተኛ ሀገር ለማድረግ መገደዱ ይታወቃል፡፡ በተለያዩ ክልሎችና ከተሞች የተገነቡና እየተገነቡ የሚገኙ በርካታ ስቴድየሞች ቢኖሩም የእግር ኳስ መጫወቻ ሜዳው ሳር ካፍና ፊፋ በሚፈልጉት ደረጃ አለመገኘቱ ትልቁ ችግር ሆኖ ዘልቋል፡፡
ይህን የካፍና የፊፋ ጥያቄ ይመልሳል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት በእድሳት ላይ የሚገኘው አንጋፋው የአዲስ አበባ ስታዲየም ነው፡፡ ይሁን እንጂ የዚህ ስታድየም የመጫወቻ ሜዳና ሌሎች ከእድሳቱ ጋር በተያያዘ ምክንያት አሁንም ድረስ አገልግሎት ለመስጠት ። የብሄራዊ ስታዲየም ግንባታም ቢሆን በታቀደለት ጊዜ መጠናቀቅ አልቻለም፡፡
የባህር ዳር ስታዲየም የካፍን ግብረመልስ መሠረት አድርጎ የመጫወቻ ሜዳው በሚፈለገው መስፈርት መሠረት እንዲሠራ ለማድረግ አበረታችና ተስፋ ሰጪ ጥረት እየተደረገበት ይገኛል፡፡
የእነዚህ ስታድየሞች ግንባታና የመጫወቻ ሜዳ ጉዳይ ችግር መች እልባት ያገኛል ለሚለው ጥያቄ አሁንም ድረስ ቁርጥ ያለ መልስ ማግኘት አይቻልም፡፡ ዋልያዎቹን በቅርቡ ከስደት ይታደጋል ተብሎ የተሻለ ተስፋ የተደረገበት አንድ ስታድየም ግን ከወደ ምስራቅ ተገኝቷል፡፡
50 ዓመታትን ያስቆጠረው አንጋፋው የድሬዳዋ ስታዲየም እድሳትና የመጫወቻ ሜዳው ሰው ሠራሽ ሳር የማልበስ ሥራ እየተከናወነ እንደሚገኝ ቀደም ሲል ተገልጿል፡፡ የኢትዮጵያን ፕሪምየር ሊግ ከ1ኛ እስከ 11ኛ ሳምንት ሲያስተናግድ የቆየው የድሬዳዋ ስታድየም የእግር ኳስ መጫወቻ ሜዳ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጨዋታዎችን ደረጃቸውን በጠበቀ መንገድ እንዲያስተናግድ ነው እየተሠራ የሚገኘው፡፡ 50 ሚሊዮን ብር የወጣበት የመጫወቻ ሜዳው ሥራ ካለፈው ዓመት አንስቶ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችን ሲያስተናግድ ቆይቷል፡፡
የመጫወቻ ሜዳው ለሶስት ዓመት የዓለምን እግር ኳስ በበላይነት በሚመራው ፊፋ መስፈርት ማረጋገጫ ማግኘቱ ከተገለፀ ሰንብቷል፡፡ አሁን ደግሞ ስታድየሙ ቀሪ የእድሳት ሥራዎቹን አጠናቆ ሙሉ ፈቃድ ለማግኘት እየጠባበቀ እንደሚገኝ ታውቋል፡፡ ስታዲዮሙን ኢትዮጵያ ለማስተናገድ ላቀደችው የ2029 አፍሪካ ዋንጫ ከወዲሁ ዝግጁ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ መሆኑን የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ቢሮ አሳውቋል።
የኢፌዴሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ ሰሞኑን በስታዲየሙ ተገኝተው ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት እንደ ተጠቆመው፣ የድሬዳዋ ስታድየም አራት የመልበሻ ክፍሎች፣ የማሳጅ ክፍል፣ ሱቆች፣ ግዙፍ ስክሪን፣ ፋርማሲዎች፣ ባንኮች እና ሌሎች አገልግሎቶችን ፊፋ በሰጠው የማስተካከያ ግብረመልስ መሠረት በማካተት ተገንብቶ ተጠናቋል።
በጉብኝቱ ወቅት እንደተገለፀው፣ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ለስፖርት ዘርፍ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት የስታዲየሙ እድሳት ዓለም አቀፍ መስፈርት እንዲያሟላ ከማድረግ በተጨማሪ በተለያዩ ስፖርቶች ብቁ ስፖርተኞችን ለማፍራት የሚያስችል የስፖርት አካዳሚ በመገንባት ላይ ይገኛል፡፡ የአካዳሚው ግንባታ ሂደትም 92 ከመቶ የደረሰ ሲሆን፤ የሜካኒካል ሥራዎች ብቻ እንደሚቀረው በሚኒስትሯ የተመራው ልኡክ ሥፍራው ላይ ተገኝቶ ምልከታ ባደረገበት ወቅት ተገልጿል።
አካዳሚው የውሃ ዋና ገንዳ፣ የእግር ኳስ መጫወቻ ሜዳ፣ የሜዳ ቴንስ፣ ጂምናዚየም፣ የሠልጣኞች መኖሪያ ክፍሎች፣ የመመገቢያና የስብሰባ አዳራሾች፣ ቤተመጽሃፍት እንዲሁም አንፊ ቴአትር በውስጡ የሚይዝ ይሆናል።
በምልከታው ወቅትም የኢፌዴሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስትሯ ሸዊት ሻንካ፤ የስፖርት መሠረተ ልማት ላይ የከተማው ከንቲባ ለሰጡት ትኩረት እና እየተገነቡ ለሚገኙ ፕሮጀክቶች ምስጋናቸውን ገልፀዋል፡፡ ትውልድን ለማነጽና ሀገርን ለመገንባት መሰል መሠረተ ልማቶች ያስፈልጋሉ ያሉት ሚኒስትሯ፣ እነዚህ የተጀመሩ ፕሮጀክቶችም ተጠናቀው አገልግሎት ወደመስጠት መግባት እንደሚ ኖርባቸው አሳስበዋል።
ብርሃን ፈይሳ
አዲስ ዘመን ሐሙስ ታኅሣሥ 17 ቀን 2017 ዓ.ም
via የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት