የተኩስ አቁም ስምምነት ከታወጀ በኋላ በጋዛ ሰርጥ እስራኤል በፈጸመችዉ ጥቃት ቢያንስ 80 ፍልስጤማዉያን ተገድለዋል
የእስራኤል ወታደሮች በጋዛ ቢያንስ 82 ሰዎችን መግደላቸውን የህክምና ምንጮች ለአልጀዚራ የገለፁ ሲሆን ሃማስ እና እስራኤል የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ካስታወቁ በኋላ ባሉት ሰዓታት ውስጥ ቢያንስ 30 ሰዎች በጋዛ ከተማ ውስጥ ብቻ ተገድለዋል።ረቡዕ ምሽት በጋዛ ሰርጥ ሰሜናዊ ክፍል በሚገኘው በጋዛ ከተማ ኢንጂነርስ ዩኒየን ህንፃ አቅራቢያ በሚገኝ ቤት ላይ bአንድ ጥቃት ቢያንስ 18 ሰዎች መሞታቸውን የአልጀዚራ አረብ ዘጋባ ያሳያል።
የፍልስጤም ሲቪል መከላከያ የ12 ሰዎችን አስከሬን ከጋዛ ከተማ ሼክ ራድዋን ሰፈር ማግኘቱን አስታዉቋል።በማዕከላዊ ጋዛ በቡሬጅ ካምፕ ካራጅ አካባቢ በተሰበሰቡ ሰዎች ላይ ባነጣጠረ የእስራኤል ሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት አምስት ሰዎች ተገድለዋል።ፍልስጤማውያን ረቡዕ አመሻሽ ላይ በእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተደረሰውን የተኩስ አቁም ስምምነት ለአጭር ጊዜ ደስታቸዉን ከገለጹ በኋላ ወደ ድንኳናቸው ሲመለሱ የጥቃቱ ሰለባ ሆነዋል።
የተኩስ አቁም ስምምነቱ እስከ እሁድ ድረስ ተግባራዊ መሆን አይጀምርም፡፡በጋዛ ውስጥ ያሉ ሰዎች የእስራኤል የቦምብ ጥቃት ከመቆሙ በፊት የከፋ ዉድመት ሊደርስ ይችላል የሚል ስጋት ዉስጥ ወድቀዋል፡፡"በሰው አልባ አውሮፕላኖች እና በከባድ መሳሪያዎች የሚሰነዘረው ጥቃት እየጨመረ እንደሚሄድ እየጠበቅን ነው" ሲሉ ነዋሪዎች ስጋታቸዉን ገልጸዋል፡፡