በአዲስአበባ አንድ ነዋሪ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ለመንቀሳቀስ በአማካይ ከ1 ሠዓት በላይ ይፈጅበታል ተባለ።
ይህ የተባለው በአሜሪካ ሃገር ተቀማጭነቱን ያደረገው የኢ.ቲ.ሲ ኢንስቲትዩት ከአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ እና ከሻካ አናሊቲክስ ጋር በመተባበር በአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት የትራንስፖርትና የመኪና ማቆሚያ አሰራር (ፓርኪንግ ሲስተም) ላይ የተጠቃሚዎችን እርካታ የቅድመ ዳሰስ ውጤቶችን ይፋ ባደረገበት ወቅት ነው።
ጥናቱ ያተኮረው በምዕራፍ አንድ - የአዲስ አበባ ኮሪደር ፕሮጀክት ላይ ሲሆን አራቱን ኮሪደሮች የሸፈነና ከ400 በላይ ነዋሪዎችን ያሳተፈ ነው።በዚህ ጥናት መሰረት በአዲስ አበባ ከተማ አንድ የትራስፖርት ተጠቃሚ ከከተማው አንዱ ስፍራ ወደ ሌላኛው ስፍራ ለመንቀሳቀስ በአማካኝ 1:15 ደቂቃ ይውስድበታል ተብሏል።ይህም አሰልቺ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ የጊዜ ብክነትና በተጠቃሚ ከፍተኛ መጉላላትን እንደሚያስከትል በአውደ ጥናቱ ላይ ተነግሯል።
Via Arts TV