ጥር 8፣2017 - ለህዳሴ ግድብ ከተሸጠው ቦንድ አብዛኛው ለህዝቡ ተመልሷል ተባለ
ለህዳሴ ግድብ ከተሸጠው ቦንድ አብዛኛው (ከ14 ቢሊዮን ብር በላዩ) ለህዝቡ ተመልሷል ተባለ፡፡ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ 14 ዓመታት ለተጠጋ ጊዜ ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ለገቢ ማሰባሰቢያነት ሲውል የነበረውን ቦንድ ለግለሰቦችና ለተቋማት ሲሸጥ መቆየቱ ይታወቃል፡፡ ለአብነትም ከግድቡ ጅማሮ አንስቶ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2016 ዓ.ም ያለውን እንኳን ብንመለከት በሃገር ውስጥ 17.4 ቢሊዮን ብር የሚያወጣ ቦንድ ተሸጧል፣ በውጭ ሃገራት ላሉ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያ...