75 በመቶ አዲስ አበቤ የቫይታሚን" D" እጥረት አለበት
ከአዲስ አበባ ነዋሪዎች 75 በመቶዎቹ የቫይታሚን " D" እጥረት እንዳለባቸው ጥናት አሳይቷል፡፡ ይህም 75 በመቶ አዲስ አበቤ የቫይታሚን" D" እጥረት እንዳለበት ያመላክታል ።
ዓመቱን ሙሉ ፀሐይ በማያጣት ኢትዮጵያ በሽታ የመከላከል አቅምን ያዳክማል፣ ድብርትንም ያስከትላል ለተባለው የቫይታሚን ዲ እጥረት አብዝቶ የመከሰቱ ችግር የአኗኗር ዘይቤ ለውጥ እንደ ምክንያት ተጠቅሷል፡፡
ጥናቱ እንደ ሀገርም ከ50 በመቶ በላዩ ኢትዮጵያዊ የቫይታሚን ዲ እጥረት አለበት ይላል፡፡
የአጥንት መሳሳትን ጨምሮ የቫይታሚን " D" እጥረት የሚያስከትላቸውን የጤና እክሎች ለመከላከል ቢያንስ በሳምንት አንድ ቀን ገላን በፀሀይ በማጋለጥ ለተወሰነ ደቂቃ መሞቅ እንደሚያስፈልግ ተመክሯል ።
ሸገር ሬዲዮ