የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ለሚሰጣቸው አገልግሎቶች የሚከፈል ክፍያን የሚያሻሽል አዲስ ደንብ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ይፋ ሆኗል።
የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ክፍያ
ለኢትዮጵያውያን 950 ብር ሆኗል፤ 350 ብር ለምዝገባ እና ቀሪው በትምህርት አይነት የፈተና ክፍያ። ለውጪ ዜጋ 100 ዶላር።
የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና (Exit Exam) ክፍያ
ለኢትዮጵያውያን 2,000 ብር ተደርጓል። 500 ብር የምዝገባ እና 1,500 ብር ደግሞ የፈተና ክፍያ መሆኑ ተገልጿል። ለውጪ ዜጋ 100 ዶላር።
የድኅረ-ምረቃ መግቢያ ፈተና (NGAT) ክፍያ
ለኢትዮጵያውያን 3,500 ብር የተደረገ ሲሆን፣ 500 ብር የምዝገባ እና 3,000 ብር የፈተና ክፍያ መሆኑ ተመላክቷል። ለውጪ ዜጋ 100 ዶላር።
የሙያ ፈቃድና ብቃት ምዘና ክፍያ
ለኢትዮጵያውያን 3,500 ብር ሲሆን፣ 1,000 ብር የምዝገባ እና 2,500 ብር የፈተና ክፍያ መሆኑ ተገልጿል። ለውጪ ዜጋ 150 ዶላር።
ደንቡ ሌሎች ተቋሙ ለሚሰጣቸው ልዩ ልዩ አገልግሎቶች የክፍያ መጠንንም አስቀምጧል።
የትምህርት ማስረጃ ምትክ ሰርተፊኬት ለማግኘት
➻ ለኢትዮጵያውያን 600 ብር ፤ ለውጪ ዜጎች 115 ዶላር።
ምትክ ሰርተፊኬትና የማረጋገጫ አገልግሎት ለማግኘት
➻ ለኢትዮጵያውያን 900 ብር ፤ ለውጪ ዜጎች 170 ዶላር።
በስም ላይ የፊደል ግድፈት ለማስተካከል
➻ ለኢትዮጵያውያን 700 ብር ፤ ለውጪ ዜጎች 130 ዶላር።
የትምህርት ማስረጃ ለማጣራት
➻ ለኢትዮጵያውያን 400 ብር ፤ ለውጪ ዜጎች 75 ዶላር።
ኦፊሺያል ትራንስክሪፕት ለማስላክ
➻ ለኢትዮጵያውያን 750 ብር ፤ ለውጪ ዜጎች 50 ዶላር።
(የተሻሻለው ደንብ ቁጥር 593/2018 ሙሉ ይዘት ከላይ ተያይዟል።)
https://t.me/MedNotev