ክፉ ባልንጀርነት መልካሙን አመል ያጠፋል ( ፩ኛ .ቆሮ . ፲፭ ፥ ፴፫ )
ባልንጀርነት ማለት ተዋደደ ፣ ተስማማ፣ ተካከለ ማለት ሲሆን እኩያ፣ አምሳያ፣ ባልደረባ፣ ዘመደ፣ ጓደኛ፣ ጎረቤት፣ አቻ፣ ኅብረት፣ አንድነትና ትክክለኝነት ያለው ማንኛውም ነገር ነው። ይህም በሁለት ይከፈላል።
፩ኛ መልካም ባልንጀራ ፦ ማለት ሕይወትህን ሕይወቱ፣ ድካምህ ድካሙ፣ ጎዶሎህን ጎዶሎ፣ ደስታህን ደስታው፣ ክብርህን ክብሩ፣ ኀዘንህን ኀዘኑ፣ ስደትህን ስደቱ፣ መከራህን መከራው አድርጎ ከጎንህ የማይጠፋ ዘንበል ስትል ቀና ፣ ዘመም ስትል ደገፍ እያደረገ በምክርና በሐሳብ ካንተ ሳይለይ ምሥጢር የምታካፍለውንና የምትነግረውን ቆጥቦ የሚይዝ ፣በጥቂቱ የሚታመን በብዙ የልብህ መንግስት ውስጥ የሚሾም ማለት ነው።
ባልንጀራን መውደድ ትእዛዘ እግዚአብሔር እና መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት ነው ። ነገር ግን ባልጀራውን የማይወድ በጨለማ፣ በድንቁርና፣ በገሃነም ይኖራል፤ “ ባልንጀራህን እንደራስህ ውደድ” እንደተባለው (ዘሌ ፲፱ ፥ ፲፰ ) ለሰው ልጅ ሁሉ ሕግን የሰጠ አምላክ ሰዎች እርስ በእርሳቸው ተዋደው ቢኖሩ የመዋደድ በረከትን አንዱ ሌላውን ቢያጠፋ ደግሞ የኃጢአት ውጤት የሆነውን ቅጣት ያስተላልፋልና።
በአርአያ ሥላሴ የተፈጠረ የሰው ልጅ ሁሉ ማንንም ከማን ሳያበላልጥ እኩል በሆነ ፍቅር መመልከት ተገቢ በመሆኑ በዕድሜ፣ በዕውቀት፣ በሥራ ቦታ፣ በማኅበራዊ ኑሮ ሁሉ ባልንጀራ የሆነውን የሰው ዘር በመውደድ፣ ትእዛዝን በመፈጸም እና ለመፈንሳዊ በረከት በመሽቀዳደም መበርታት ያስፈልጋል ። ስለዚህ ባልንጀራን እንደ ራስህ አድርጎ መውደድን ፣ ራስን አሳልፎ እስከ መስጠት የሚደረስበት መሆኑን ማወቅ ተገቢ ነው።
ጠቢቡ ሰለሞን እንዲህ አለ “ባልንጀራህን የሚንቅ እሱ በእግዚአብሔር ፊት ይበድላል።” (ምሳ ፲፬ ፥ ፳፩ ) በቅዱስ ወንጌል ታሪኩ የተጻፈለት ደጉ ሳምራዊ በመንገድ ላይ ወድቆ ያገኘውን ቁስለኛ አንስቶ መልካም ነገር ስለአደረገለት መልካም ባልንጀራ በማት ተጠቁሟል።( ሉቃ ፲ ፥ ፳፭ ) በሀገራችን ኢትዮጵያም ቅዱሳት መካናትን ለመሳለም የሚመጣውን ኅብረተሰብ ኢትዮጵያውያን እግር አጥበው፣ መኝታ ሰጥተው፣ ስንቅ ጨምረው የሚል ናቸው። ስለዚህ በደዌ ሥጋና በረኀበ ሥጋ ማጥገብና መፈወስ ብቻ ሳይሆን በደዌ ነፍስ ተይዘው የሚቃትቱትን እና እርዳታ ለሚሹ ሁሉ ደርሶ ከቃለ እግዚአብሔር ተመግበው፣ በንስሐ ታክመው ጸጋና ረድኤት ተጎናጽፈው በመንፈሳዊ ሕይወት እንዲኖሩ ማድረግ ባልንጀራን መውደድ ነው።
፪ኛ ክፉ ባልንጀራ፦ የሰውን ልጅ የፈጠረ እግዚአብሔር ክፋት የሚስማማው ስላልሆነ የዋህነት፣ ቅንነትና በጎነት እንዲስማማ አድርጎ ቢፈጥርም በኃሚአት ምክንያት ክፋት ወደ ሰው ልጅ መጥቷል፤ ክፋት የማን ነው ቢባል ከዲያቢሎስ በመሆኑ ከበጎ ሥራችን ክፉ ሥራችን የሚበዛ ከሆነ ከእግዚአብሔር ሳይሆን ከሐሰት አባት ከዲያቢሎስ በግብር በመውሰድ የክፋት የኃጥያት ባሪያ እንሆናለን፤ የኃጥያት ደሞዝ ደሞ ሞት ነው። ( ሮሜ ፮ ፥ ፳፫ ) ስለዚህ የክፉ ሰዎች ደመወዝ ለጊዜው ቢመስልም መጨረሻው ሞት ነውና በዚህም ሰውች ገጽታን እየተመለከቱ ልቡናንና እንቅስቃሴውን ሳያውቁ ባስቀመጡት ክቡ ባልንጀራ የተጎዱ ብዙዎች ናቸውና ከክፉ ባልጀራ መራቅ አስፈላጊ ነው። ለማሳያ ያህል በጥቂቱ፦
ሀ‚ የሔዋንና የእባብ ባልንጀርነት፦ የሰዎች ሁሉ እናት የሆነችው ሔዋን እግዚአብሔር የነገራትን ባለ መስማት በእባብ ላይ ባደረው ዲያብሎስ ጋር ጓደኝነት በመጀመሯ እና ምክር በመስማቷ ከፈጣሪ ተጣላች፣ ልጅነቷን አጣች፣ ከገነት ተባረረች፣ በሞተ ሥጋ መርገመ ነፍስ ተፈረደባት። ዛሬም ብዙ ሰዎች በትምህርት ቤት፣ በመሥሪያ ቤት፣ በጎረቤት ሁሉ የጓደኛ ምርጫቸውን ካላስተካከሉ ይፈተናሉ፤ የነፍስም የሥጋም በሽተኛ ይሆናሉ፤ ከእግዚአብሔር የተቀበሉትን ጸጋ ያጣሉ።
ለ‚ የአምኖንና የኢዮናዳብ ባልንጀርነት፦ የንጉሡ የዳዊት ልጅ አምኖን መንፈስ ዝሙት አድሮበት በእኅቱ በትዕማር በመጎዳቱ በዚህ ጊዜ ኢዮናዳብ የሚባለው ጓደኛው ክፉ ምክር መክረው፣ አምኖንም የክፉ ጓደኛውን ምክር ተቀብሎ በተግባር ፈጸመ። እኅቱን አስገድዶ ደፈረ፣ ከክብር አዋረደ፣ አባቱንም እግዚአብሔር አሳዘነ፣ በበጎ ምግባር እአያ መሆን ሲገባው በእንደዚህ ዓይነት መጥፎ ተግባር ሲጠቀስ ይኖራል። በዘመናችን ሰዎች ተቸገርኩ ብለው ሲያማክሩ ወደ መልካም መንገድ ከመምራት ይልቅ ያሰበውን ክፉ ሐሳብ ለማስፈጸም የኃጥያት መንገድ የሚጠርጉ ብዙዎች ናቸው።
በመሆኑም ክፉ ባልንጀርነት መልካሙን አመል ያስጠፋል ማለት እንደዚህ ያለው ነውና በዚህ ዓለም ስንኖር ወደንመ ሆነ ተገደን ከሰዎች ጋር ማኅበራዊ ሕይወት ይኖረናል፤ ይሁን እንጂ ከማን እና ምን ዓይነት የሕይወት ልምድ ካለው ጋር ነው የምንኖረው የሚለውን የማጤን ሥራ ልንሠራ ይገባል። ከክፉ ባልንጀርነት በመጠበቅ በመልካም ባልንጀርነት መጠቀም ያስፈልጋል ።
ምንጭ ፦ ሐመር መጽሔት
@mekra_abaw