ለሕይወት እንጠይቅ
"የዘለዓለም ሕይወትን እወርስ ዘንድ ምን ላድርግ?"ይህን ጥያቄ ጌታን የጠየቀው አንድ ሃብታም ወጣት ነው። ይህ ወጣት የጥያቄውን መልስ ባይተገብረውም የጠየቀው ጥያቄ ግን በጣም አስፈላጊና ወሳኝ ነው። እኛ የሰው ልጆች የተፈጠርነው ለሕይወት ነው ለሕይወት ተፈጥረን ሳለ ግን በዙሪአችን ባሉ distraction ተስበን ዋና ዓላማችንን ችላ እያልን ነው። ክርስቶስ የሞተው በእርሱ ለዘለዓለም እንድንኖር ነው ፣ የክርስቶስ ተከታዮች ክርስቲያን የኾነውም ከክርስቶስ ጋር ለዘለዓለም ለመኖር ነው። አብዛኞቻን ግን ክርስቲያን የኾነው በክርስቶስ ለመኖር ሳይኾን ነፍስ ካወቅን ጀምሮ እራሳችንን በክርስትና ውስጥ ስላገኘነው ነው። ስለዚህም የምንጠይቃቸው ጥያቄዎችም ለሕይወት የሚኾኑ አይደሉም። "በሚካኤል ቀን ልብስ ይታጠባል?" ፣ "አሳማ ይበላል?" ፣ " በሰንበት ቡና ይወቀጣል?"፣ " የሙስሊም ሥጋ የበላ ሰው ቄደር ይጠመቃል?" እያልን ለድኅነት እንኳን ረብ የሌላቸው ጥያቄዎች ላይ ጊዜ እናጠፋለን።
እንዲሁም ልክ ለመንጻት ሥርዓት ብቻ እንደሚጨነቁ ፈሪሳውያን ሰውን በየእያንዳንዱ ነገሮች እያሳቀቅን ከክርስቶስ እናርቃለን እንደው በጌታ "በበዓል ቀን ወፍጮ ፈጨህ ፣ ሥራ ሠራህ"፣ "የአርሴማን ጸበል ተጠምቃ ቡና ጠጣች" ፣ " በማርያም ቀን ልብስ አጠብክ" ፣ " በወር አበባ ላይ ኾና ጸበል ጠጣች" እያሉ ክርስቲያኑን ማሳቀቅ ተገቢ ነው? ይህ በክርስትና ውስጥ የተደበቀ ፈሪሳዊነት ነው! ክርስቶስ አሁን ቢመጣ ኖሮ "ሰንበት ለሰው ተሠራች እንጂ ሰው ለሰንበት አልተሠራም" ብሎ ፈሪሳውያንን እንደ ወቀሰ አንደኛ ተወቃሾች እኛ ነበርን።
ክርስቲያን የኾነው በክርስቶስ የዘለዓለምን ሕይወት እናገኝ ዘንድ ነው ስለዚህ የኹል ጊዜ ጥያቄያችን "ወደ ክርስቶስ እንዴት ልቅረብ?" ፣ "የዘለዓለም ሕይወትን እንዴት ላግኝ?" ይኹን ለሕይወት እንጠይቅ፤ ፈሪሳዊነት ከመካከላችን ይውጣ!