ደስታ ቢራቢሮ ሲሆን ፤ ለመያዝ ብንሞክር የማይጨበጥ....ነገር ግን ፀጥ ብለን ስንቀመጥ ከአጠገባችን ብልጭ የሚል ነው ። ለደስተኝነት አንድ መንገድ ነው ያለው ። እሱም ከምኞታችን አቅም በላይ በሆኑ ነገሮች ላይ መጨነቅን ማቆም ነው። እጅህ ላይ ያለው ካላስደሰተህ እርግጠኛ ሁን ሊመጣ ያለውም አያረካህም ። በበርሃ አበባ ሳትፈነድቅ በገነት ውበት አትመሰጥም ። የፍላጎት ስሌትህን ወደ ጎን አርገውና ፣ ስለ ንጋት ፀሀይዋ መሞቅ ፣ ስለ ቀኑ ብራነት ፣ በነፃ ስለምትተነፍሰው ውድ አየር ፣ ደክሞህ እንኳ ሰለማይደክማት ልብህ ፣ በዙሪያህ ስላሉት ወገኖች ፣ ይህንን ማንበብ እንኳ ስላስቻለህ አይንህ ስታስብ ...
በደንብ ስታጤን ... በእርግጥ ከሌለህ ይልቅ ያለህ ብዙ እንደሆነ ትረዳለህ ፡፡ ያኔ እድለኝነት ይሰማሀል ፡፡ ያኔ እንዳልጎደልክ ይገባሀል .... ያኔ አመሰጋኝ ትሆናለህ ። የራስህ አመለካከት ሲጠራ ደስታህና መልክህ እንደፀሓይ ያበራል ። በቁስ ያልተደገፈ ደስታ ውስጥህን ይሞላዋል ፡፡ ነገ ራሱ የብዙ ዛሬዎች ድምር ነውና ለደስታህ ቀጠሮ አትያዝለት ...የደስታህ ጊዜ አሁን ነው ።