በአላማ ተማር!
፨፨፨//////፨፨፨
እውቀት የጥበብ መግቢያ በር ነው። አላዋቂ ምንምያህል ቢጥርና ቢታገል የጥበብ ደጃፍ ሊደርስ አይችልም። ለዓመታት የምትማሩት ሰው የሆነውን ለመሆን አይደለም፣ ለዘመናት እንቅልፍ አጥታችሁ የምታነቡት የሆነ ቦታ ተቀጥራችሁ ዘመናችሁን በሙሉ ለመፍጀት አይደለም። ለምን እንደምትማሩ ካላወቃችሁ ትምህርቱ ቢቀርባችሁም ግደየለም። መማር ብክነት ሆኖ አያውቅም፤ ትምህርት ቤት ሔዶ እውቀትን መገብየትም ኪሳራ ሆኖ አያውቅም። በምክንያት የሚደረግ የትኛውም ነገር ጥቅም አለው። አሁን አሁን በትምህርት ዙሪያ ብዙዎች በሁለት ጎራ ተከፍለዋል። አንደኛው ለዓመታት መማርን እንደ ግዴታ ያየዋል፣ ሌላኛው ከነጭራሹ ትምህርት መማር እንደማያስፈልግ ያስባል። ምናልባት ሁለቱም በራሳቸው መንገድ ልክ ሊሆኑ ይችላሉ ነገር ግን ሁለቱንም ሊያስማማ የሚችል አንድ ሃሳብ አለ። እርሱም "ለምን ትማራለህ?" የሚለው ጥያቄ ነው። የጥያቄው ምላሽ ሁሉንም ነገር ያስተካክላል። በዓላማ የምትማሩት ትምህርት ትርፉ እጅግ ከፍተኛ ነው፤ ዓላማ የሌለው ትምህርት ግን ከኪሳራዎች ሁሉ የላቀ ትልቅ ኪሳራ ነው።
አዎ! ምንም ውስብስና ግራ የሚያጋባ ነገር የለም። አሁን ላይ እየተማራችሁ ከሆነ ለምናችሁን ፈልጉ፣ ገና የመማር ሀሳብ ካላችሁም ለምናችሁን ፈልጉ። ህይወት እቃቃ ጫወታ አይደለችም። በተገደበ እድሜያችሁ አትጫወቱ። ብዙ ሰው ስለተማረ፣ ብዙ ሰው ማስተርስ (Masters) ፒኤችዲ (PhD) ስለደራረበ፣ ብዙ ሰው ዘመኑን በሙሉ በትምህርት ላይ ስለፈጀ እናንተም የብዙውን ሰው መንገድ የመከተል ግዴታ የለባችሁም። ስም እንጀራም ሆነ ዳቦ አይሆንም፣ ስም ብቻውን አንድ እርምጃ ወደፊት ፈቀቅ አያደርጋችሁም፣ ለዘመናት የለፋችሁበት ትምህርት ብቻውን ነፃ አያወጣችሁም። የተማራችሁትን ካልተገበራችሁት፣ እውቀታችሁን ዓላማችሁ ላይ ካላዋላችሁት፣ የጥበብን በር እንዲከፍትላችሁ ካልፈቀዳችሁለት፣ በመረጣችሁት ዘርፍ ላይ ስመጥር ባለሙያ ካልሆናችሁበት ጊዜያችሁን እያባከናችሁ ነውና ቆም ብላችሁ አስቡ። ለዘመናት ያከማቻችሁት እውቀት ድፍረት ካልሰጣችሁ፣ ህይወታችሁን ካላሻሻለላችሁ፣ ወደፊት ካልገፋችሁ እውቀትነቱ ምኑ ጋር ነው? መማሩስ ጥቅሙ ምንድነው?
አዎ! ጀግናዬ..! በአላማ ተማር! በምክንያት ጊዜህን ስጠው። በዋናነት ተማሪ ብትሆን፣ በትርፍ ጊዜህም ብትማር ጊዜ ማሳለፊያ የሚባል ወይም በሰው ግፊት የምትማረው ትምህርት የለም። ብዙ ጊዜ የተማረ ሰው ይፈራል፣ ብዙ ጊዜ የተማረ ሰው ከተማረበት ውጪ መስራትን እንደ ሀጢያት ይመለከተዋል። በፍፁም አትሸወድ። በተማርክበትም ይሁን ባልተማርክበት ከፍ የሚያደርግህንና ከአላማህ ጋር የሚገናኝ ስራን ካገኘህ ዝቅ ብለህ ስራ። ዘላለም ዝቅ ብለህ አትኖርም፣ እድሜ ልክህን ከሰው በታች እንደሆንክ አትቀርም። መማርህ ዝቅ ብሎ መነሳትን እንዲያስተምርህ አድርግ፣ እውቀትህ ለአላማህ የመፋለም አቅምህን እንዲያበረታ አድርግ። አትዘናጋ፣ መዘናጋት ከፍለህ የማትጨርሰው እዳ ያሸክምሃል፤ ዛሬ ነገ አትበል፣ ቀጠሮ አታብዛ ቀጠሮህ ፈሪና ጭንቀታም ያደርግሃል። ከማንም ምንም አትጠብቅ። ተምረህ ተምረህ የተማረ ሰው የማይገባውን ህይወት እየኖርክ ከሆነ የትምህርት ስረዓቱን ከመውቀስ የራስህን እወቀትና ትምህርት በመጠቀም ከተመፅዋችነት ነፃ ውጣ። የገጠመህን ችግር የሚያሳልፍህ የተማርከው ትምህርት ሳይሆን ያንተ ብስለትና ጥንካሬ እንደሆነ እወቅ።
ግሩም ድንቅ ቀን ይሁንልን! 🏞🌞🌅
(Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋
በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪