በማንም አልደገፍም
ከራስ ጋር ንግግር ፦ "አንድን ነገር ስፈልግ ከልቤ ጠንክሬ እሰራለሁ፣ እርሱን ለማግኘት መተው ያለብኝን ሁሉ እተዋለሁ፣ እስከ ጥግ እጓዛለሁ፣ መጠየቅ ያለብኝ እጠይቃለሁ፣ መጋፈጥ ያለብኝን ነገር ፊት ለፊት እጋፈጣለሁ። ይሔን ሁሉ የማደርገው እውነተኛውን አቅሜን ስለማውቅ ነው፣ ጠንክሬ ብሰራ ምን ማግኘት እንደምችል ስለገባኝ ነው። ለዓመታት የዓለምን ግርግር ተመልክቼያለሁ፣ ለዘመናት ብዙ ነገር ከሰው ስጠብቅ ከርሜያለሁ፣ በጣም ለረጅም ጊዜ አንድ ቦታ ቆሞ ነገሮች በምኞቴ ብቻ እንዲስተካከሉ ስጠባበቅ ቆይቼያለሁ። ሰዎች እንዲወዱኝ ደፋ ቀና ያልኩበት ጊዜ ትዝ ይለኛል፣ ሰዎች እንዲረዱኝ የተጓዝኩት ረጅም ርቀት ትዝ ይለኛል፣ እራሴ ማድረግ የምችለውን ነገር ከሰው ስጠብቅ የነበረበት ጊዜ ትዝ ይለኛል፣ እኔ ለእራሴ ህልም የነበረኝን ተነሳሽነት ሰዎችም እንዲኖራቸው የተመኘውበት ጊዜ ይታወሰኛል። ነገር ግን እያንዳንዱ አስተሳሰቤ እያደር ብዙ ዋጋ አስከፍሎኛል፣ ቀድሞ የነበሩኝ አቋሞቼ ብዙ ርቀት ወደኋላ አስቀርተውኛል። ስቃይን ሸሸው ምቾትን መረጥኩ ነገር ግን በምቾት ውስጥ ስሰምጥ ይሰማኝ ጀመረ፣ ከፈጣሪና ከራሴ በላይ በሰው ስመካና ስደገፍ ራሴን እያጣውትና በራስመተማመኔን እየተነጠኩ እንደሆነ ይገባኝ ጀመረ።
አዎ! በማንም አልደገፍም፣ ከማንም ምንም አልጠብቅም፣ ማንም የወደፊት እጣፋንታዬን እንዲወስንልኝ አልፈቅድም። የእኔ ህይወት የእኔ ነው። በፈጣሪዬ እገዛ የት መድረስ እንደምችል አውቃለሁ፣ ራሴ ላይ ብጨክን ምን ማምጣት እንደምችል በሚገባ ተረድቼያለሁ። የዘመናት ወቀሳዬ ምንያህል እንሚያሳፍረኝ ማንም አያውቅም። በራሴ ጥፋት አንገቴን ስደፋ ነበር፣ ራሴን ለከፋ ውድቀት ሳመቻች ነበር። ነገር ግን እዛው የነበርኩበት ላይ አልቆምኩም። ቀና አልኩ፣ በችግሮቼ ነቃው፣ በውሱንነቴ ተንገበከብኩ፣ "እስከመቼ ከሰው እጠብቃለሁ" አልኩ፣ ረጅሙንና ፈታኙን የህይወት ጉዞ ተቀላቀልኩ። የተሻሉ ቀናት ከፊቴ እንዳሉ ስለማውቅ ለነዛ ቀናት ስል ዋጋ ከፈልኩ፣ ከራሴ በላይ ማንም እንደማይደርስልኝ ስለተረዳው ቀጥታ ወደ እርምጃ ገባው። ከእግዚአብሔር ጋር ህይወትን ድል አድርጌያለሁ፣ ከአምላኬ ጋር ፍፁም ከቀድሞ የተለየ ህይወትን መኖር ጀምሬያለሁ፣ የከፈልኩት ዋጋ በውጤት ተከቦ በእጄ ገብቷል።"
አዎ! ጀግናዬ..! ድጋፍን ፍለጋ ያባከንከውን ጊዜ አስብ፣ ነገሮች ሁሉ በቀላሉ እንዲሳኩልህ የጠበክበትን ወቅት አስብ። ቀላል ነገርን ፍለጋ ብትደክም ይባስ ከባዱንና ፈታኙን ነገር ታገኘዋለህ። የትም ብትሔድ ፈታኙን ነገር ማግኘትህ አይቀርም፤ ምንም ብታደርግ ዋጋ ሳትከፍል የምታገኘው ትልቅ ነገር የለም። ምቾትህ ለስንፍና አሳልፎ እንዲሰጥህ አትፍቀድ፣ ቸልተኝነትህ ለውድቀት እንዲያመቻችህ አትፍቀድ። በጥንካሬ የሚገለጠውን በረከትህን አትግፋው፣ ከብርታትህ የሚመጣውን ስኬት አትሽሸው። የአምላክ እግዛ በሚሰሩ እጆች ላይ ነው። "ከልቤ ከፈለኩት አገኘዋለሁ።" የሚለውን አስተሳሰብ ወደ ውስጥህ አስርፅ። በራስመተማመንህን ሰርትህና ለፍተህ እንጂ በፍፁም ተመኝተሀው እንደማታገኝ እወቅ። ጠንክረህ ስራ፣ የምትመኘውን ህይወትም በፈለከው መንገድ ኑረው።
ግሩም ድንቅ ቀን ይሁንልን! 🏞🌞🌅
(Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!
በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪