ለእራስህ ምን ሰጠህ?
ኬት መጣህ? የት ትገኛለህ? ወዴት እየሔድክ ነው? በእነዚህ መንገዶች ሁሉ ምንም ስህተት የለም። ስህተቱ ጉዞህን በተመለከተ ለእራስህ የሰጠሀው ቦታ ነው። ኬትም ተነስ፣ የትም ተገኝ፣ ወዴትም ተጓዝ ዋናው ነገር እርሱ አይደለም። ዋናው እራስህን ምን ያክል ትቀበላለህ፣ እስከምን በእራስህ ትተማመናለህ፣ በየትኛው ማንነትህ ትኮራለህ፣ በየትኛው ስብዕናህ ይበልጥ ትደሰታለህ፣ ህይወትህን በሙላት የምትኖረው መቼ ነው? የሚለው ነው። ህይወት እስካለ ጉዞ አለ፤ አቅጣጫውም አንተ የመረጥከው ይሆናል። ወደ ፊት ወይም ወደ ኋላ፣ ወደ ቀኝ ወይም ወደ ግራ። ትልቅ ትርጉም ያለውም ሁሌም እንቅስቃሴ ላይ መሆንህ ነው። ወደፊት ለመጓዝህ፣ የተሻለውን ለመምረጥህ፣ እራስህን ለማግኘትህ፣ እራስህን ለማብቃትህ ግን ማረጋገጫ ያስፈልግሃል። ችላለው ካልክ መቻልህ ይታይ፤ አደርገዋለሁ ካልክ ማድረግህ ይገለጥ፣ አሳካዋለሁ ካልክ ማሳካትህ ስሜቱ ይሰማህ። ህይወት ክብደቷን እንድትቀንስ፣ ውስብስብነቷን እንድታጣ፣ አተልጋ በአልጋ እንድትሆን አትመኝ። በቀላል መንገድ ተጉዞ ቀላል ህይወት የሚኖር ሰው የለምና።
አዎ! ጀግናዬ..! ለእራስህ ምን ሰጠህ? ስለ እራስህ ምን ይሰማሃል? እየሔድክ የቆምክ ይመስልሃልን? እየለፋህ ያቆምክ ያክል ይሰማሃልን? ጥረትህ ትርጉም አልባ፣ ድካምህም ድካም ብቻ እንደሆነ ይሰማሃልን? መዳረሻህ ካነሰ ለጉዞህ ስሜት ማጣትህ አይቀርም፤ በትንሽ ግብ ጥረትህ ይገደባል፤ ባነሰ ራዕይ አቅምህ ይገታል፤ በወረደ ህልም ማንነትህ ያንሳል። ትግል አድርገህ የምትሰራው ነገር ሁሌም ትግልነቱ ይቀጥላል፤ ሳይዋሃድህ የምታደርገው ነገር ዘወትር ችግርና ክፍተቱ ብቻ ይታይሃል፤ ያንተ ያልሆነ ነገርም መዘዝ ብቻ ይዞብህ ይመጣል። ለእራስህ ለማድረግ ስትታገል፣ እንዲዋሃድህ ስትጥር ያንተ የሆነውንና እስከዛ ሰዓት ያልሞከርከውን ነገር ትበድለዋለህ። ዋናው ጉዳይ ላንተ የሚሰጥህ ስሜት ሆኖ ትኩረትህ ውጤት ከሆነ ቆም ብለህ ማሰብ ይጠበቅብሃል። እየሔድክ ቢሆንም የመሄድ ስሜት ሊሰማህ ይገባል፤ እየሰራህ ከሆነም የስራውንና ተከትሎት የሚመጣውን የድካም ጠዓም ማጣጣም ይኖርብሃል። እያንዳንዱ እርምጃ ውስጥ መኖርህን የሚያስታውስ፣ ትርጉም ያለው ነፍስ አለ።
አዎ! በየቀኑ መንገድ ላይ ስለወጣህ፣ በሩጫ ስለተጠመድክ፣ መጓዝህ ስላላቆምክ ብቻ ከመዳረሻህ አትደርስም። የጉዞህ ስሜት፣ የሩጫህ ድካም ትጉም ያለው መሆኑን ከውስጥ ሊሰማህ ይገባል። ብትሰራው ባትሰራው፣ ብትሞክረው ባትሞክረው በስሜትህ ላይ ለውጥ የሌለው፣ እርካታን የማይሰጥህ፣ ህይወትህን ነፍስ የማይዘራበት፣ ነፃነትን የማያድልህ፣ ከገንዘብ ውጪ ትርፍ የሌለው ነገር ውስጥ እራስህን ካገኘህ የህይወት ውስብስብ መረብ ውስጥ ተገኝተሃል ማለት ነው። ንቃትህ ለእራስህ ይጠቅምሃልና አመጣጥህን ትተህ፣ ችግሮችህን ረስተህ፣ ድክመቶችህን ወደኋላ ብለህ፣ ያለህበትን አጣብቂኝ ወደጎን ተትህ በዚች ቅፅበት ስላለህበት የህይወት ደረጃ ምን እንደሚሰማህ መርምር። ጥቂትም ቢሆን ለሰዎች ህይወት ምን እያበረከትክ ነው? ካንተ ብቻ የሚገኝ ምን ነገር አለ? የሚያምርብህ፣ የሚገልፅህ፣ የምትሆነው፣ ያንተ የሆነ ነገር ምንድነው? ህይወት ቅፅበት ናትና ሁሌም አሁንህ ውስጥ እንድትኖር፣ በአሁንህ እንድትደሰት የሚያደርግህ የህይወት ስንቅ ያስፈልግሃል። ለእራስህ የሰጠሀውን ግምት አስተካክል፤ ማንነትህን ስታስብ በእራሱ ደስታን የሚጭር፣ ፈገግታን የሚያድል፣ የሚያኮራህ አይነት ስሜት እንዲሰማህ አድርግ።
ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒💫✨
(Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!
በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪