ትሻሻላለህ፣ ትቀየራለህ!
የአየር ሁኔታውን መቀየር አትችልም ነገር ግን አለባበስህን መቀየር ትችላለህ፣ ችግሮችህን ማስቀረት አትችልም ነገር ግን እራስህን ማበርታት ትቸላለህ፣ ጊዜውን ማስተካከል አትችልም ነገር ግን ከጊዜው ጋር መራመድ ትችላለህ፣ በአንዴ ተነስተህ መንግስት መቀየር፣ አሰራሩን ማሻሻል አትችልም ነገር ግን እራስህን በፈለከው መንገድ መገንባትና ማሻሻል ትችላለህ። ከአቅም በላይ የሆኑ፣ የማንቆጣጠራቸው፣ በእነርሱ ላይ ስልጣን የሌለን፣ እኛ ሳንሆን እነርሱ የሚመሩን ምድራዊ ጌቶችና በእግዚአብሔር ፍቃድ የሚዘወሩ ነገሮች አሉ። ከዚህም አንፃር በእነርሱ ከማማረርና ከመናደድ ይልቅ እራሳችንን መመልከት ይኖርብናል። እውነት ነው ህይወት ከባድ ነች፣ የክብደቷ ልኬት ግን ሚዛኑ በእኛ እጅ ላይ ነው። "ሁሉም ነገር ይቻላል" ሲባል በሰው አቀምና እውቀት የሚገደብ መሆኑንም መረዳት ተገቢ ነው።
አዎ! ጀግናዬ..! ቀላሉን መመኘት አቁመህ ለከባዱ መዘጋጀት ስትጀምር፣ ምቾትን መጠበቅ አቁመህ በማይመች ሁኔታ ውስጥ እራስህን ለማመቻቸት ስትጥር፣ ከምታየውና ከምትሰማው በላይ በእራስህ ተስፋ ከተመራህ፣ የአምላክን መልካም ፍቃድ ከጠበክ በእርግጥም ትሻሻላለህ፣ ትቀየራለህ፣ ታድጋለህ። ሃሳብና ምኞትህ ሁሉ ገደብ አላቸው፣ ከገደባቸው የማለፍ አቅሙ ግን ይኖርሃል። ማውጣት ማውረዱ፣ ማሰብ ማሰላሰሉ አይቀርልህምና ማድረግ ስለምትችለው ብታስብ፣ መቀየር ስለምትችለው ብታሰላስል ደግሞ ብዙ ነገር የመቀየር እድሉ ይኖርሃል። ከቢሆነ ኖሮ ሃሳብ ተላቀቅ፣ ቅዠት ከተቀላቀለበት ሃሳብ ውጣ፣ ከአቅምህ በላይ የሆኑ ነገሮች ላይ ማተኮር አቁም። ነፃ ፍቃድ አለን ፍቃዳችን ግን በገዛ ፍላጎትና ምርጫችን የተገደበ ነው፤ ማንም የተሰጠው የተለየ ክህሎት አለው፣ የክህሎቱ ውጤት ግን በእራሱ ውሳኔና ተግባሩ ላይ የተመሰረተ ነው።
አዎ! ልክን አውቆ መኖር፣ እንደ አቅም መራመድ፣ የሚችሉት ላይ ማተኮር ትልቅ ስጦታ ነው። ምንም ማድረግ አልችልም ከማለታችሁ በፊት የምትችሉትን ሁሉ ስለማድረጋችሁ እርግጠኛ ሁኑ። ነገሮች ከአቅማችሁ በላይ መሆናቸውን የምታውቁበት ብቸኛ መንገድ ሙከራችሁ ስታዩ ብቻ ነው። እጅን አጣጥፎ ተቀምጦ ከህይወት ክብደት ማምለጥ አይቻልም፤ ንግግርን ችላ ብሎ፣ ለመግባባት ዝግጁ ሳይሆኑ ቀርቶ የሰመረ የፍቅር ህይወት መመስረት አይቻልም፤ እራስን ገድቦ፣ ማንነትን አሳንሶ፣ እራስን ወደኋላ እየገፉ ለውጤት መብቃትና እራስን ማሻሻል አይቻልም። ከአቅምህ ጋር የሚሔድ ምርጫን ምረጥ፣ በመረጥከው ምርጫ ደስተኛ ስለመሆንህ እርግጠኛ ሁን፣ ባሰብከው ሰዓት ያሰብከው ስፍራም እንደሚያደርስህ ተማመንበት።