ለሰው አታሳዩ!
፨፨፨////፨፨፨
ህይወታችሁ ውስጥ ምን እየተካሔደ ነው? እናንተ ምን ደረጃ ላይ ናችሁ? ምን አግኝታችሁ ምን አጥታችኋል? የምትንሰፈሰፉለት ነገራችሁ ምንድነው? ሰው ባየልኝ ብላችሁ የምትመኙት ነገርስ ምንድነው? ምንም ላይ ድረሱ፣ ምንም አይነት ትልቅ ነገር አድርጉ፣ የትኛውንም አጓጉዊ ተግባር ፈፅሙ በፍፁም ለሰው አታሳዩ፣ እንዴትም ሰው እንዲያውቅ አታድርጉ። በህይወታችሁ ደስተኛ ናችሁ? ለሰው አታሳዩ፣ በህይወታችሁ ደስተኛ አይደላችሁም? ለሰው አታሳዩ፣ የምትፈልጉትን ነገር አግኝታችኋል? ለሰው አታሳዩ፣ በዛሬ ስኬታችሁ ትኮራላችሁ? ያፈራችሁት ንብረት ያስደስታችኋል? ያላችሁ ቤተሰብ ያሳሳችኋል? የትምህርት ደረጃችሁ በራስመተማመናችሁን ጨምሮታል? የሚያስቀና የፍቅር ወይም የትዳር ህይወት አላችሁ? ለሰው አታሳዩ። አስደሳችም ሆነ አሳዛኝ፣ አዎንታዊም ሆነ አሉታዊ ሁኔታ ውስጥ ብትሆኑ ለራሳችሁ ደህንነትና ውስጣዊ ሰላም ብላችሁ ሁኔታችሁን ለሰው አታሳዩ። ደስተኛ እንደሆናችሁ ለሰው ሁሉ ካላሳያችሁ ማን ደስታችሁን በሃዘን ይቀይረዋል? ሀዘናችሁን ለሰው ሁሉ ካላሳያችሁም ማን ድክመታችሁን ያውቃል? የሚያያችሁ ሰው ሁሉ ወዳጃችሁ እንደሆነ አታስቡ፣ በጊዜው ድርጊታችሁን የሚያደንቅ ሁሉ ከልቡ እንደሆነ አታስቡ።
አዎ! ለሰው አታሳዩ! ስኬታችሁን ለሰው አታሳዩ፣ ከፍታችሁን ለሰው አታሳዩ፣ ውድቀታችሁን፣ ስህተታችሁን፣ ድክመታችሁን ለሰው አታሳዩ። የእውነት መሻሻልና ማደግ ከፈለጋችሁ፣ የምር ከልብ የተረጋጋና ሰላማዊ ህይወት መኖር ከፈለጋችሁ በፍፁም ትልቅም ይሁን ትንንሽ ጉዳያችሁን ለሰው አታሳዩ። ሰው ስላየው ነገር ይጠይቃል፣ ያወቀውን ነገርም ይመረምራል፣ ከምርመራው ቦሃላ የራሱን የግል ፍርድ ይሰጣል። ብዙዎች በሚገባ የሚያውቁትን ትልቅ አጀንዳ ቤታቸው አስቀምጠው በጨረፍታ ስላዩትና ስለሰሙት የሰው ጉዳይ በመተንተን ጊዜያቸውን ያጠፋሉ። የተሸፈነ ነገር ይበስላል እንደሚባለው ህይወታችሁን ሸፈን ሸሸግ አድርጉት። ሁለመናችሁን አደባባይ አውጥታችሁ ነፃነት የሚባል ነገር እንደማይኖራችሁ እወቁ። "ሰው እንዲ ይለኛል፣ ሰው እንደዛ ይለኛል" ብላችሁ ከምትጨነቁ ገና ከጅምሩ ሰው የሚለውን ለማሳጣት ደበቅ ብላችሁ ኑሩ። ለአንድ ሰሞን ታይቶ መነጋገሪያ ሆኖ ማለፍ የሰው ምላስ ውስጥ ከመክተት ውጪ ምንም የሚጠቅማችሁ ነገር የለም። በአጉል ፉክክር ተወጥራችሁ ያላችሁን ነገር ሁሉ ለሰው ስላሳያችሁ የበለጣችሁ እንዳይመስላችሁ።
አዎ! ጀግናዬ..! አንተ ማን እንደሆንክ ታውቃለህ፣ ኬት እንደተነሳህ፣ አሁን የት እንዳለህ፣ ወዴት እንደምትሔድም በሚገባ ታውቃለህ። ስለራስህ ያለህ እውቀት ላንተ ይጠቅምሃል፣ ሌላ ሰው ግን ስላንተ ሁሉንም ነገር ማወቁ ለአንተም ሆነ ለሰውዬው የሚጠቅመው ነገር የለም። በቅርበት የሚያዩህ ሰዎች ያዩሃል፣ የሚያወቁህም ያውቁሃል። እይታና እውቀታቸው ግን በልክ ሊሆን ይገባል። ስራ መጀመረህን ዓለም ማወቅ የለበትም፣ ፍቅረኛ መያዝህን ወዳጅ ዘመዱ ሁሉ ማየት አይኖርበትም፣ ማግባትህ በየሚድያው መተላለፍ የለበትም፣ ቤት መኪና መግዛትህን የምታውቀው ሰው ሁሉ ማየት የለበትም። ያገኘሀው የትኛውም ነገር እንዲበረክትልህ ከፈለክ ከሰው አይን ሸሽገው፣ ትኩረት እንዳይበዛበት ዞር አድርገው። በለበስከው ውድ ልብስ ከመሰናከል ራስህን ጠብቅ፣ በገነባሀው ትልቅ ህንፃ ከመውደቅ ራስህን ጠብቅ። በሰው ፊት በንብረትህ ትለካለህ በፈጣሪህ ፊት ግን በልብህ ትለካለህ። የትኛው እንደሚበልጥ አንተ ታውቃለህ። ራስህን የመጠበቅ ግዴታ አለብህ፣ ራስህን ከምትጠብቅበት ዋና መንገድ ውስጥም አንደኛው ከሰው ተደብቆ በነፃነት መኖር ነው። ባንተ ዙሪያ የሚነሱ አጀንዳዎችን ቀንስ፣ የጫጫት መንስኤ ከመሆን ታቀብ፣ ዞር ብለህ ዓለምህ በደስታ ቅጭ።