የመጀመሪያዎቹ ሁኑ!
፨፨፨፨////////፨፨፨፨
መውደቅ ብርቅ አይደለም ነገር ግን ብርቅ ቢሆን እንኳን እስኪ የመጀመሪያዎቹ ሁኑ፤ መሸነፍ ለማንም አዲስ አይደለም ነገር ግን አዲስ ቢሆን እንኳን እስኪ የመጀመሪያዎቹ ሁኑ፤ መተቸት መሰደብ ብርቅ አይደለም ነገር ግን ብርቅ ቢሆን እንኳን እስኪ ለመጀመሪያ ጊዜ ተተቹ ተሰደቡ። ምን ይመጣል? ምን ታጣላችሁ? ምንስ ይጎድላችኋል? ለአንዳንድ ሁነቶች መፍትሔው ድፍረትና ድፍረት ብቻ ነው። መምጣት ያለበት መምጣቱ ላይቀር እንዲሁ በረጅም ገመድ እንደ ታሰረች አህያ ራሳችሁን በፍረሃት አትሰሩት። ከዚህ በፊት ማንም ላይ ያልተከሰተ ነገር አይከሰትባችሁም ቢከሰትባችሁም እንኳን የሞትና የሽረት ጉዳይ አይደለም። በደምብ አስባችሁት ከሆነ ትልቅ ቦታ ከሰጣችሁት ዓለም ላይ የማያስፈራ ነገር የለም። ቦታ በሰጣችሁት ልክ ሊቆጣጠራችሁ የሚፈልገው ነገር ብዙ ነው። አዲስ ነገር ለመሞከር የመጀመሪያ ከሆናችሁ ለማሳካቱም የመጀመሪያዎቹ የምትሆኑት እናንተ ናችሁ። ርቆ መሔድ ስጋትን ይደቅናል፣ እዛው በነበሩበት መቆየትም ጭንቀትን ያመጣል፤ ለየት ማለት አይን ውስጥ ያስገባል፣ ተመሳስሎ መኖርም ያስረሳል። በዚህም አላችሁ በዛ ጭንቀት ሁሌም አለ። የጭንቀታችሁን ምክንያት መምረጥ ግን ትችላላችሁ።
አዎ! የመጀመሪያዎቹ ሁኑ! ከፊት ቅደሙ፣ ብትከስሩም ብታተርፉም ጥቅሙ የእናንተ ነው። ዓለም የምትሸልመው አሸናፊዎችን ነው፣ አሸናፊዎች ደግሞ በመሞከርም ሆነ በመጀመር የመጀመሪያዎቹ ናችሁ። ቆማችሁ ከሆነ ትልቁ ሃሳባችሁ መጀመር ብቻ ይሁን፣ ጀምራችሁም ከሆነ ዋናው ግባችሁ መጨረስ ይሁን። የሰው ልጅ የመጀመሪያ መሆንን ይፈራል፣ ከፊት ሆኖ ነገሮችን አስቀድሞ መጋፈጥ ያስጨንቀዋል፣ ሃላፊነት የበዛበት ነገር ላይ ለመሳተፍ አይፈርድም። ፊትለፊት የማይወጣና ራሱን በአሉታዊ ንግግሮች ያላስገረፈና ቆዳውን ያላጠነከረ ሰው ደግሞ አንድ እርምጃ ወደፊት ፈቀቅ ያለ ህይወት አይኖረውም። ነገሮች ይደጋገማሉ፣ ሃሳቦች ይደራረባሉ ነገር ግን እነዚህ ለረጅም ጊዜ የተደራረቡ ነገሮች ለብዙ ሰዎች አዲስ ናቸው። እናንተ ሰው እየጠበቃችሁ ከሆነ ጊዜ ግን አይጠብቃችሁም፣ እናንተ ወቅታዊ አጀንዳን እያሳደዳችሁ ከሆነ ዓለም ጥላችሁ እየሔደች ነው። ሞኝ ብልጦች መሓል ሲገባ ብልጥ የሆነ ይመስለዋል። ከገባው ግን ቶሎ ሞኝነቱን ተረድቶ ከሁሉም የላቀ ብልጥ ሆኖ መገኘት ይችላል።
አዎ! ጀግናዬ..! ከፊት ተሰለፍ፣ ከአብዛኛው ሰው ቀድመህ ተገኝ፣ ብዙ ሰው ለማያገኘው እድል ራስህን አዘጋጅ። በየትኛውም ውድድር አስቀድመው የጀመሩት ሁሉ አያሸንፉም፣ ነገር ግን ካልጀመሩት ሰዎች በተለየ ከፍተኛ የማሸነፍ እድል አላቸው። ደፋር እንደሆንክ የምታስብ ከሆነ ብዙ ሰው በሚሸሸው ወሳኝ ጉዳይ ላይ ከፊተኞቹ ተርታ የማትመደብበት ምክንያት አይኖርም። ፈሪ ዓለሙ ፍረሃት ነው፣ ደፋር ዓለሙ እውነት ነው። ፈርተህ አትቁም ይልቅ በድፍረት ከፊት ተፋለም፣ ተጨንቀህ እድልህን አትግፋው ይልቅ ነቃ ብለህ በርህን ክፈትለት። አንተ ካልተቀየርክ የትም ብትሔድ ስጋትህ አይቀየርም፣ አንተ ካልነቃህ ምንም ብታደርግህ ፍረሃትህ በውጤትህ ይገለጣል። እርግጥ ነው ለማውራት የቀለለ ሁሉ ሲደረግም ቀላል ሊሆን አይችልም። አንተን ግን የሚያስፈልግህ ቅለቱ ወይም ክብደቱ ሳይሆን ማድረጉ ብቻ ነው። ኮተት አታብዛ፣ ምክንያት አትደርድር። ፍላጎቱ ካለህ ቀድመህ ተራመድ፣ ከማንም ቀድመህ ከመዳረሻው ድረስ፣ የሚገባህን ውጤትም በእጅህ አስገባ።