ባያችሁት አትሰበሩ!
፨፨፨፨//////፨፨፨፨
ውጪውን እያያችሁ፣ ሌላውን ሰው እየተመለከታችሁ፣ ሶሻል ሚድያውን እየበረበራችሁ በንፅፅር ዓለም ለምትባክኑ፣ ሳታቁት ራሳችሁን ንቃችሁ ሌላውን የምታከብሩ፣ ባለማስተዋል ራስን መሆንን ተጠይፋችሁ ሌላ ሰው መሆንን ለምትናፍቁ፣ በተደጋጋሚ በሙላት እየኖራችሁ እንዳልሆነ ለሚሰማችሁ፦ የእናንተ ዓለም ይሔ አይደለም፣ ህይወታችሁን ልትመሩት የሚገባው በዚህ መንገድ አይደለም። አውቃችሁና ፈልጋችሁ እዚህ ሁኔታ ውስጥ አልገባችሁም፣ ብትጠየቁም ምርጫችሁ እንዳልሆነ ትናገሩ ይሆናል። ነገር ግን የማይወደውን ህይወት የሚኖር፣ የማይፈልገው ስፍራ የሚገኝ፣ የማይገባውን ተግባር የሚፈፅም ሰው እናንተ ብቻ አይደላችሁም። ብዙ ሰው እንደነገሩ ይኖራል፣ ካለበትም የከፋ እንዳለ እያሰበ ይፅናናል። እርግጥ ነው ከፈጣሪው በቀር ያለበትን ችግር የሚረዳው የለምና ራሱን ከማፅናናት በቀር አማራጭ የለውም። መጨከን ካለባችሁ ህይወት ላይ ጨክኑ እንጂ ራሳችሁ ላይ አትጨክኑ። ህይወት ብዙ ክፉ ነገር ብታሳያችሁም እናንተ በፍፁም ባያችሁት ነገር እንዳትሰበሩ፤ ዓለም ብዙ ብትፈትናችሁም እናንተ ግን በፍፁም ፈጣሪያችሁን እንዳታማርሩ። ጭፍን አማኝ፣ ጭፍን ተስፈኛ መሆንን ልመዱ። የመጣው ይምጣ እንደ አመጣጡ ተመልሶ ይሔዳል።
አዎ! ባያችሁት አትሰበሩ! ሁን ተብሎም ተደረገ በአጋጣሚ ተከሰተ አሁን አሁን የምታዩት ብዙ ነገር አስፈሪ፣ የምትሰሙትም ነገር እንዲሁ አስደንጋጭ ሊሆንባችሁ ይችላል። ነገር ግን ብትፈሩም እንዳትሰበሩ፣ ብትደነግጡም ተስፋ እንዳትቆርጡ። በራሳቸው ሃይል ሊያሸንፏችሁ የማይችሉ አካላት ድክመታችሁን አጥብቀው ይፈልጋሉ፣ እንድትረጋጉና ራሳችሁን ችላችሁ እንድትቆሙ የማይፈልጉ አካላት በብዙ ትብታብ ሊያስሯችሁ ይፈልጋሉ። ደካማ ሰው ብርታቱ አይታየውም፣ ሰነፍ ሰውም በራሱ ጥንካሬ አይተማመንም። ማንኛውም የሰው ልጅ ትኩረት ማድረግ ከቻለ ምንም ማድረግ እንደሚችል አስተውሉ። ትኩረታችሁ በብዙ መንገድ ተሰርቆ፣ የሚረባውንም የማይረባውንም ወደ አዕምሯችሁ እያስገባችሁ፣ አገኘን ብላችሁ ነፃ የሆነ ነገር እያሳደዳችሁ፣ አጥፊያችሁ ይሁን አልሚያችሁ እንደሆነ ሳትረዱ ያያችሁትን ሁሉ እየተመኛችሁ ከሆነ ዓለም አዙሪት ውስጥ ከታ አቅላችሁን ሳታስታችሁ በፍጥነት ወደ ራሳችሁ ተመለሱ። አትዘናጉ፣ ልባችሁ ሲሰረቅ ዝም ብላችሁ አትመልከቱ።
አዎ! ጀግናዬ..! ያበቃ ቢመስልህም ገና አላበቃም፣ የተሸወድክ፣ የተሸነፍክ፣ የወደክ፣ የተጣልክ ቢመስልህም ጊዜው ገና ነው። ዳግም መነሳት ትችላለህ። በውድቀትና በሽንፈት መሃል የተማርከውን ትምህርት እየኖርክ ዳግም ራስህን ማብቃት ትችላለህ። ሸሩን ለሸረኛ፣ ጎጡን ለጎጠኛ፣ ሰበቡንም ለሰበበኛ ትተህ አንተ ራስህን አድን። የተባለው ሁሉ እውነት እንዲሆን አትጠብቅ፣ የተነገረህን ሁሉ ማመን አቁም። የትኛውንም በነፃ የምታገኘውን ነገር ከመጠቀምህ በፊት እርሱ ሊጠቀምብህ እንዳልሆነ በሚገባ መርምር። አንዳንድ ሁነቶች መግቢያቸው በጣም ሰፊ ነው፣ መውጫቸው ግን እጅጉን ጠባባ ነው። ቦሃላ "ምነው እጄን በሰበረው" ከማለትህ በፊት አገኘው ብለህ ሁሉ ነገር ውስጥ እጅህን አትክተት። አብዛኛው ብልጭልጭና አጓጉዊ ነገር ወጥመድ ነው። በሰዓቱ ያልጠበከውን ደስታ ይሰጥሃል ቦሃላ ግን መቀመቅ ውስጥ ይከትሃል። ሰው ያደረገውን ሁሉ አታድርግ፣ ሰው በተራመደበት መንገድ ሁሉ አትራመድ። አስተዋይነትህን ተጠቀም፣ ስብራትህንም ቀድመህ አስቀረው።