ከባዱ ያከብድሃል!
ከባድ ሁኔታዎች ጠንካራ፣ ብርቱና አይበገሬ ሰዎችን ይፈጥራሉ። ብርቱና ጠንካራ ሰዎችም ቀላል ሁኔታን ይፈጥራሉ፤ ቀላል ሁኔታዎችም ልፍስፍስና ቀላል ሰዎችን ይፈጥራሉ፤ ልፍስፍስና ደካማ ሰዎችም ከባድ ጊዜያትን ይፈጥራሉ። ብስለትህ፣ ጥንካሬህ፣ ብርታትህ በቀላልና ከፈተና በፀዳ ሁኔታ ውስጥ ሊፈጠር አይችልም። እንቅፋት የሚገጥምህ ስለተንቀሳቀስክ ነው፤ የምትወድቀው፣ የምትነሳው እዛው የነበርክበት ስፍራ ስላልተቀመጥክ ነው። ቀና ማለትህ ብዙ ነገሮችን ያስመለክትሃል፤ ብዙ መሞከርህም የተለያዩ የሚሳኩና የማይሳኩ መንገዶችን ያሳይሐል።
አዎ! ጀግናዬ..! በፈታኙና በከባዱ ሁኔታ ውስጥ ተፈጥረህ፣ ተሰርተህ፣ በርትተህ፣ ጠንክረህ ወተሃልና ከባድ፣ አስጨናቂና አስቸጋሪ ሁኔታዎችን መውቀስ፣ መተቸት፣ ማማረር አይጠበቅብህም። ለውጥህ በከባድ ሁኔታ ውስጥ ነው፤ እድገትህ ነገሮች ስላልተሟሉልህ ነው። ኑሮ ስለተወደደብህ የተሻለ ለመስራት፣ የእራስህን ስራ ለመጀመር፣ የተሻለም ለማግኘት ትጥራለህ፤ የሚደርስብህን እያንዳንዱን በደል ተቋቁመህ በእራስህ ለመቆም በመሞከረህ ጥንካሬን ወደማግኘት ትመጣለህ። በብርታትህ ልክ ነገሮችንም ማቅለል ትጀምራለህ፣ የተሻሉ ሁኔታዎችን ትፈጥራለህ፣ ለሌሎች የመድረስ አቅምህን ታጎለብታለህ፤ እራስህን በማብቃት የወገንህ መመኪያ፣ የወዳጆችህ መጠለያ ትሆናለህ።
አዎ! ከባዱ ያከብድሃል፤ ቀላሉም ያቀልሃል። በህይወትህ ከችግርና ከፈተና በፀዳህ ቁጥር የተሻለና ብርቱ ሰው የመሆንህ እድል እየመነመነ ይመጣል። ለውጥ በሌለው፣ ምንም በማትጨምርበት፣ ሙቀት ቅዝቃዜ በሌለበት፣ ከፍታ ዝቅታ በማይታይበት፣ ደረጃው በማይቀንስ በማይጨምር መካከለኛ ( Mediocre ) የሆነ ህይወትን ትመራለህ። ለመቀየር ምክንያት ታጣለህ፣ ለማደግ የሚያስገድድህ ነገር አይኖርም፤ ለመቅረፍ የምትጣጣረው፣ በተሻለ ሁኔታ የሚያታግልህ፣ የሚያሰራህ፣ የሚያለፋህ፣ የሚያተጋህ ከባድ ሁኔታ አይኖርም። በፈተናዎችህ መሐል እራስህን አሳድግ፤ በአስጨናቂ ጊዜያት ውስጥ እራስህን አግኝ፤ በከባድ ሁኔታዎች መሐል ብርቱውን አንተ ፍጠር፤ ከተጎዳህበት አጋጣሚ በላይ ለመሆን እራስህን አጠንክረህ፣ አሻሽለህ፣ አጎልብተህ ተገኝ።