🙏 ብረት ጽኑ ነው እሳት ያሸንፈዋል ፤ እሳት ብርቱ ነው ውሃ ያሸንፈዋል ። ውሃ ብርቱ ነው ደመና ይሸከመዋል ፤ ደመና ኃያል ነው ንፋስ ይበትነዋል ። ንፋስ ብርቱ ነው መሬት ይገድበዋል ፤ መሬት ጽኑ ነው የአዳም ልጅ ያሸንፈዋል ። የአዳም ልጅ ብርቱ ነው ሀዘን ያሸንፈዋል ፤ ኋዘን ጽኑ ነው ጠጅ ያሸንፈዋል ። ጠጅ ብርቱ ነው እንቅልፍ ያሸንፈዋ ፤ እንቅልፍ ብርቱ ነው ሞት ያሸንፈዋል ።
🙏 የዚህ ሁሉ ነገር ማጠቃለያ ግን ሴት ነች ። ሴት ልጅ ሁሉን ነገር ታሸንፋለች ፡፡ አባቶች ተመራምረው በህይወት ልምዳቸው ቀምረው የደረሱበት አንድ ሀቅ የዚህ አለም የመጨረሻዋ አሸናፊ ሴት መሆኑዋን ነው ። በሴት የማይሸነፍ ምንም ነገር የለም ፤ሞትም ጭምር ። በታሪክ ሞትን ያሸነፈው ክርስቶስ ብቻ እንደሆነ ነው የምናውቀው ፡፡ ታድያ ሴት ሞትን እንዴት አድርጋ ነው የምታሸንፈው ? ብለን አባቶችን ስንጠይቅ ''ሞት የሚሸነፍበት ብቸኛው ዘዴ በመውለድ ነው ። ሴት ልጅ በመውለድ ሞትን ታሸንፈዋለች ሲሉ ይመልሳሉ ።
🙏 ክብር ሁሉን ድል ለሚያደርጉ እናቶቻችን 🙏