ማንም አያዝንላችሁም!
፨፨፨፨////////////፨፨፨፨
ማንም ሁኑ የምትኖሩት የእራሳችሁን ህይወት ነው፤ ምንም አግኙ የእናንተን ነገር በዋናነት የምትጠቀሙት እናንተው ናቹ። የሚገባችሁ ነገር ዛሬ ካላችሁ ነገር የሚበልጥ እንደሆነ ማረጋገጥ እስካልቻላችሁ ድረስ ህይወት የተለመደውን ነገር ትሰጣችኋለች፣ በተለመደው መንገድ ትመራችኋለች፣ የሚመጥናችሁ ቦታ ታደርሳችኋለች። እርግጥ ነው ህይወት ከባድ ነች። በተለይ ሀዘን ሲደራረብ፣ መኖር ትርጉም ሲያጣ፣ ግፊቶች ሲበዙ፣ ብቸኝነት ሲያጠቃን፣ ውስጣዊ ሰላምና መረጋጋት ሲጠፋ ህይወት ከባድ ነች። ክብደቷ የሚቀንሰውም እያንዳንዱን ጥያቄ በጥልቀት መርምሮ ምላሽ በመስጠት ብቻ ነው። ህይወት ትርጉም ካልሰጣችሁ ትርጉሙን ፈልጉ፣ የተፈጠራችሁለትን አላማ መርምሩ፣ ግብ አስቀምጡ። በብቸኝነት ከተቸገራችሁ፣ ሰዎች ከራቋችሁ በቅድሚያ የእራሳችሁ ወዳጅ መሆን ጀምሩ፣ ለእራሳችሁ ጊዜና ቦታ መስጠት ጀምሩ። ሀዘናችሁን መቋጫ አብጁለት፣ ስንፍናችሁን ወደኋላ በሉት፣ ለውስጣዊ ሰላምና መረጋጋታችሁ ትኩረት ስጡ። ሁሌም ቢሆን ጥረታችሁ ለማሸነፍ ይሁን፣ ሁሌም ቢሆን ሙከራችሁ የተሻለ ስፍራ ለመገኘት ይሁን።
አዎ! በሚያሳዝን ሁኔታ ካላችሁበት ከባድ ሁኔታ አንፃር ሰዎች እንዲያዝኑላችሁ፣ ሰዎች ስለእናንተ ተጨንቀው ጊዜ እንዲሰጧችሁ ብትፈልጉም ማንም አያዝንላችሁም። ችግራችሁ የእናንተ ብቻ ነውና ችግራችሁን ለመጋፈጥ የምትወስኑት ውሳኔም የእናንተ ነው። ከእግዚአብሔር ቀጥሎ የሚያስብላችሁ ሰው እራሳችሁ ናችሁ።ሁሌም ቢሆን የሰው ነገር የአንድ ሰሞን ጉዳይ ነው። አንድ ሰሞን ያዝንላችሁ ይሆናል፣ አንድ ሰሞን ሊረዳችሁ ይሞክር ይሆናል፣ አንድ ሰሞን ከጎናችሁ ይቆም ይሆናል ነገር ግን በፍፁም የህይወት ዘመናችሁን በሙሉ ሊያዝንላችሁ፣ ሊደግፋችሁና ከጎናችሁ ሊቆም አይችልም። ምክንያቱም እርሱም እንደእናንተ የሚያዝንለትና የሚደግፈው ይፈልጋልና። የህይወት ዘመን ድጋፋችሁ ፈጣሪያችሁ ብቻ ነው፤ መፅናኛችሁ፣ አሳቢያችሁና ነፃ አውጪያችሁ አምላካችሁ ብቻ ነው። ሰው እንዲያዝንላችሁ አትጠብቁ፣ ሰው ከንፈር እንዲመጥላችሁ አትመኙ። ይልቅ ፈጣሪያችሁ እንዲያስባችሁ ተማፀኑት፣ እግዚአብሔር እንዲመለከታችሁ ጠይቁት። ብትሰበሩ የሚያቀናችሁ፣ ብትወድቁም የሚያነሳችሁ ሃይል አላችሁ ሃይላችሁም ምንጩ የአምላካችሁ መንፈስ ነው።
አዎ! ጀግናዬ..! ያንተ ጉዳይ ትናንት የእራስህ ጉዳይ ነበረ፣ ዛሬም ያንተ ጉዳይ ነው፣ ነገም እንዲሁ የእራስህ ጉዳይ ነው። ሸክም ቢኖርብህ ከብደቱን የምታውቀውም ሆነ የማውረድህን ዋጋ የምትረዳው አንተው። የሰው ልጅ ችግርህን እንዳቅሙ ሊካፈልህ ወይም ሊረዳህ ይችል ይሆናል፣ ነገር ግን የችግርህ መፍትሔ ሙሉ በሙሉ ያለው ባንተ እጅ ነው። "እንዲህ አድርግ፣ እንደዛ አድርግ፣ ይሔንን አቁም፣ ያንን ጀመር" ትባላለህ የተባልከውን ካላደረክ ግን ዛሬም እዛው ትናንት የነበርክበት ስፍራ ትሆናለህ። ያንተ መንቀሳቀስ ጥቅሙ ለእራስህ ነው፣ መቀመጥህም እንዲሁ ጉዳቱ ለእራስህ ነው። በዚህ ሰዓት ካንተና ከፈጣሪህ በቀር ምን እንደሚያስፈልግህ የሚያውቅ ሰው የለም። ተጨንቀህ ይሁን ተረጋግተህ፣ ከፍቶህ ይሁን ነፃ ሆነህ፣ አዝነህ ይሁን ተደስተህ ማንም መረጃው የለውም። ለእራስህ ማድረግ ያለብህን አድርግ፣ በቻልከው ልክ ሰው ባስፈለገህ ሰዓት ለእራስህ ቀድመህ ተገኝ፣ እንዳቅምህ ህመምህን እራስህ አክመው፣ ከሰው በላይ ፈጣሪ እንዲያግዝህ አድርግ፣ እጅህን ለአምላክህ ስጥ። መቆም በሌለብህ ሰዓት አትቁም፣ እግዚአብሔር አምላክህን ተደግፈህ መኖርህን ቀጥል፣ በፈጣሪህ መሪነት ወደፊት መጓዝህን ቀጥል።
ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒💫✨
(Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋
🔺🔻በYouTube ቤተሰብ ስለሚሆኑ እናመሰግናለን!
SUBSCRIBE NOW! 👇
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊💪