በማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ላይ አጭበርባሪዎች በዝተዋል፤ ይጠንቀቁ!
******
አጭበርባሪዎች የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ መጨመርን እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም የተለያዩ ማጭበርበሪያ ዘዴዎችን ተጠቅመው የመረጃና ገንዘብ ምዝበራ በማካሄድ ላይ ናቸው፡፡
አጭበርባሪዎች ከሚጠቀሙባቸው ዘዴዎች ጥቂቶቹን እና መከላከያ መንገዶችን እንጠቁማችሁ፡፡
1. ፊሺንግ (Phishing)
በዚህ የሶሻል ምህንድስና ጥቃት አጭበርባሪዎች ማኅበራዊ ሚዲያን ጨምሮ በተለያዩ ዲጂታል የመልእክት መለዋወጫ መንገዶች ሀሰተኛ መልእክቶችን በመላክ ተጠቃሚዎች የግል እና ሌሎች እንደ ሂሳብ፣ የይለፍ ቃል የመሳሰሉ መረጃዎቻቸውን አሳልፈው እንዲሰጡ፣ እንዲሁም አደገኛ ሊንኮችን እንዲከፍቱ እና ሶፍትዌሮችን እንዲጭኑ ያደርጋሉ፡፡
2. የኢንቨስትመንት ማጭበርበሮች (Investment Scams):
የውሸት በሆኑ ወይም በሌሉ ምርቶች ወይም ንግዶች ላይ ኢንቨስት ለማድረግ የሚያበረታቱ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ማስታወቂያዎች ተበራክተዋል። ብዙዎችም የምዝበራ ሰለባ ሆነዋል፡፡
3. ነፃ የሙከራ አገልግሎቶች (Free Trial Products):
በሀሰተኛ የምርቶች ነጻ ሙከራ (Free-trial) ማስታወቂያ ሰዎችን በማታለል ለነጻ የምርት ሙከራው እንዲመዘገቡና የክፍያ ካርድ መረጃቸውን እንዲያስገቡ የማድረግ ማጭበርበሪያ ዘዴ ነው፡፡ ተጠቂው ከሱ እውቅና ውጪ ውል ውስጥ በመግባቱ ምክንያት ክፍያ ያለባለቤቱ እውቅና ተቀናሽ ይሆናል።
4. የኦንላይን ግብይት ማጭበርበሮች
በኦንላይን ግብይት የተለያዩ ምርቶችን በቅናሽ እንሸጣለን በሚል የምዝበራ ተግባር ላይ የተሠማሩ አጭበርባሪዎች አሉና ይጠንቀቁ፡፡
5. ክሊክቤይት (Clickbait)፡
ይህ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የተጠቃሚዎችን ትኩረት የሚስቡ ጉዳዮችን የያዙ ይዘቶችን በማውጣት ተጠቃሚዎች ይበልጥ ለማወቅ ሊንኩን እንዲጫኑ የማድረጊያ ዘዴ ነው፡፡ ይህን ዘዴ አጭበርባሪዎች ሲጠቀሙበት ተጠቂው ጥቃት አድራሾቹ ወደ ሚመሩት ማስፈንጠሪያ በሚገባበት ጊዜ የግል መረጃውን አሳልፎ ሊሰጥ ይችላል።
6. የውሸት ጓደኛ ጥያቄዎች (Fake Friend Requests)፡
አጭበርባሪዎች የማኅበራዊ ሚዲያ አካውንቶችን በመክፈት ወይም የሌሎችን አካውንቶች በመጥለፍ ወደተለያዩ የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች የጓደኝነት ጥያቄ ይልካሉ። እነዚህን ጥያቄዎች መቀበል የእርሶን እና የጓደኞቻችሁን መለያ እንዲጠለፍ እና የግል መረጃ እንዲያፈተልክ ያደርጋል።
7. የሥራ እድል ማጭበርበሮች
ሀሰተኛ የስራ እድል ማስታወቂያዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ በማህበራዊ ድረ-ገጾች ላይ በስፋት ይተዋወቃሉ። ገቢዎን ያሳድጉ ወይም ከቤት ሆነው ሥራ ይስሩ በማለት አጓጊ ጥቅማጥቅሞችን በመንገር ተጠቃሚው ቶሎ ውሳኔ እንዲወስን (sense of urgency) በማድርግ ማጭበርበሩን ይፈጽማሉ።
እነዚህ አጭበርባሪዎች የተጠቃሚውን መረጃ የግል እና ሊሎች መረጃዎች ይወስዳሉ ወይም ለሥልጠና ወይም ለሌላ ጉዳይ በቅድሚያ ክፍያ ይጠይቃሉ።
8. ስጦታ
በራሳቸውም ሆነ የሌሎችን ስምና ዝና በመጠቀም ሀሰተኛ የማኅበራዊ ሚዲያ ገፆችን በመክፈት ተከታይ ስትሆኑ፣ ተከታይ ስታስገቡ፣ ልጥፎችን ስታጋሩ፣ አስተያየት ስትሰጡ፣ ስትወዱ ስጦታ እንሰጣለን በሚሉ ሀሰተኛ ማስታወቂያዎች ያጭበረብራሉ፡፡ እነዚህ አጭበርባሪዎች የተከታዮችን ግላዊ መረጃ ለመውሰድ መልካም አጋጣሚ ይሆንላቸዋል፡፡
እንዴት ከአጭበርባሪዎች ራሳችንን እንጠብቅ?
• ከማያውቁት ግለሰብ የሚደርስዎትን የማኅበራዊ ሚዲያ እንወዳጅ ጥያቄ አይቀበሉ፡፡
• የቅናሽ ማስታወቂያዎችን በጥርጣሬ ይመልከቱ፤
• በኦንላይን ብቻ ለተዋወቁት ግለሰብ ገንዘብ አይላኩ፡፡
• በማኅበራዊ ሚዲያ የግል መረጃዎን አይስጡ።
• የማስታወቂያ አስነጋሪዎችን ህጋዊነት ሳያረጋግጡ ምንም አይነት እርምጃ አይውሰዱ፡፡
• ከማህበራዊ ሚዲያ ጓደኛ የሚመጣን የእርዳታ ጥሪ በጥንቃቄ ይፈትሹ።
• ከማያውቁት አካል በሚደርስዎት አጭር የፅሁፍ መልእክት፣ ኢሜይል ወይም የማኅበራዊ ሚዲያ መልእክት የሚያገኙትን ማስፈንጠሪያ (link) አይክፈቱ፡፡
• ትክክለኛ የማህበራዊ ሚዲያ ገፆችን ይከተሉ፡፡