ፍጥጫ
እያሰኘኝ ሳይኖረኝ ምንም ላላገኝ ያለአቅሜ ስመኝ
እላይ እላይ እያሰብኩ ከመሬት ላይ ስገኝ
በሀሳብ ወጥቼ መገኛዬን ትቼ
እታቹን ፈርቼ የላዩን አይቼ
እላይ እላይ አስቤ ለታቹ ቀርቤ
በሀሳብ ጠግቤ በእውነት ተርቤ
ሀሳብ ሆነ ብቻ የሌለው መክፈቻ
ሁሌ ሽኩቻ ከእውነት ጋር ጥላቻ
መነሻ ሳይኖረኝ መዳረሻ እያልኩኝ
ሀሳብ ብቻ ሆነብኝ ሀዘን አመጣብኝ
ከፍታውን ብተው መነሻዬን ባየው
ችግሬን ባገኘው ስቃዬን ባስበው
ይሄኔ እላይ ነኝ
ሀሳብ የነበረው እውነታ ሆኖልኝ
✍ABD
እያሰኘኝ ሳይኖረኝ ምንም ላላገኝ ያለአቅሜ ስመኝ
እላይ እላይ እያሰብኩ ከመሬት ላይ ስገኝ
በሀሳብ ወጥቼ መገኛዬን ትቼ
እታቹን ፈርቼ የላዩን አይቼ
እላይ እላይ አስቤ ለታቹ ቀርቤ
በሀሳብ ጠግቤ በእውነት ተርቤ
ሀሳብ ሆነ ብቻ የሌለው መክፈቻ
ሁሌ ሽኩቻ ከእውነት ጋር ጥላቻ
መነሻ ሳይኖረኝ መዳረሻ እያልኩኝ
ሀሳብ ብቻ ሆነብኝ ሀዘን አመጣብኝ
ከፍታውን ብተው መነሻዬን ባየው
ችግሬን ባገኘው ስቃዬን ባስበው
ይሄኔ እላይ ነኝ
ሀሳብ የነበረው እውነታ ሆኖልኝ
✍ABD