#የሟቹ_ኑዛዜ
፡
የምንዱቡን ትንፋሽ
ሞት በግፍ ቢነጥቅም
ሟች ቀኑን ያጣ ቀን
ገዳዩ አይታወቅም ፤
አፋኙ ጣረ ሞት
አንደበቱን ይዞ ነፍሱን የነጠቀው
በምን ይናገራል ገዳዩንስ ቢያውቀው
ብቻ ጀምበር እድሜው
በመአልቱ ጽልመት ማልዶ የታገተ
እስከሽበት ዘልቆም አፍ ሳይፈታ ሞተ
ምናልባት ምናልባት እንደመልካም እጣ
ድንገት በለስ ቀንቶኝ የኔም ቀን ከመጣ
ሚጠይቁም ካሉ
ያሟሟቱ ነገር እንዲህ ነበር በሉ
'ሲለው መሶብ መስሎ ጎድሎ እንዳጎደለው
ሲሻውም ቀን ሁኖ ከፍቶ እንደበደለው
እድሜዉን በልቶ ነው ዘመን የገደለው!
✍ ኢዛና መስፍን
፡
የምንዱቡን ትንፋሽ
ሞት በግፍ ቢነጥቅም
ሟች ቀኑን ያጣ ቀን
ገዳዩ አይታወቅም ፤
አፋኙ ጣረ ሞት
አንደበቱን ይዞ ነፍሱን የነጠቀው
በምን ይናገራል ገዳዩንስ ቢያውቀው
ብቻ ጀምበር እድሜው
በመአልቱ ጽልመት ማልዶ የታገተ
እስከሽበት ዘልቆም አፍ ሳይፈታ ሞተ
ምናልባት ምናልባት እንደመልካም እጣ
ድንገት በለስ ቀንቶኝ የኔም ቀን ከመጣ
ሚጠይቁም ካሉ
ያሟሟቱ ነገር እንዲህ ነበር በሉ
'ሲለው መሶብ መስሎ ጎድሎ እንዳጎደለው
ሲሻውም ቀን ሁኖ ከፍቶ እንደበደለው
እድሜዉን በልቶ ነው ዘመን የገደለው!
✍ ኢዛና መስፍን