የኢትዮጵያ ህዝብ ብዛት ስንት ሚሊዮን እንደደረሰ ተገለጸ
ወርልድ ፖፑሌሽን ዛሬ ባወጣው አመታዊ ሪፖርት ኢትዮጵያ በአለማችን ላይ ከፍተኛ የህዝብ ቁጥር ካላቸው አስር አገራት መካከል አንዷ መሆኗን አስታውቋል፡፡ እንደሪፖርቱ ከአለማችን ላይ ከፍተኛ ህዝብ በመያዝ ግንባር ቀደም የሆነችው ህንድ ስትሆን አንድ ቢሊዮን አራት መቶ ሀምሳ ሚሊዮን ህዝብን ይዛለች፡፡
በሁለተኝነት ቻይና የምትከተል ሲሆን ሶስተኛ አሜሪካ ሆናለች፡፡ በመቀጠል ኢንዶኔዥያ፣ ፓኪስታን፣ ናይጄሪያ፣ ብራዚል፣ ባንግላዲሽና ሩሲያ በዝርዝሩ ላይ በቅደም ተከተል የተቀመጡ ሲሆን በአስረኛ ላይ ኢትዮጵያ ሰፍራለች፡፡
ይህ ሪፖርት እንዳለው የኢትዮጵያ ህዝብ ብዛት አንድ መቶ ሰላሳ ሁለት ሚሊዮን ነው፡፡ በአጠቃላይ የአለም ህዝብ አሁን ላይ ከስምንት ቢሊዮን አልፏል ብሏል ሪፖርቱ፡፡