(ዘ-ሐበሻ ዜና) የቀድሞዋ የዩኤስኤይድ ዋና ዳይሬክተር ሳማንታ ፓወር ሀብትን በተመለከተ ሰሞኑን በስፋት መረጃዎች ሲሰራጩ ቆይተዋል፡፡ እንደመረጃዎቹ ከሆነ ሳማንታ ፓወር ስድስት ነጥብ ሰባት ሚሊዮን ዶላር ሀብት የነበራቸው ሲሆን የዩኤስኤይስ ዋና ዳይሬክተር ሆነው በሰሩባቸው ከ2021 እስከ 2025 ባሉት አመታት የሀብታቸው መጠን ከሰላሳ ሚሊዮን ዶላር የበለጠ ሆኗል፡፡
በርካቶች ይህን መረጃ ችላ ብለውት የነበረ ቢሆንም ታዋቂው ባለሀብት ኤለን መስክ ዛሬ ይህ ሀብት ከየት የመጣ ነው በሚል መልሶ ካጋራው በኋላ ግን ትኩረትን ሊስብ ችሏል፡፡ በዩኤስኤይድ ትልቁ ደመወዝ በአመት ከ180 ሺ እስከ 212 ሺህ የሚደርስ ሲሆን ይህም በአራት አመት ከ720 ሺህ እስከ 848 ሺህ እንደሚሆን መረጃዎቹ አስረድተዋል፡፡
ሳማንታ ፓወር የዩኤስ ኤይድ ዳይሬክተር ሆነው በሰሩበት አመታት በሀርቫርድ ዩኒቨርስቲ ያስተምሩ የነበረ ሲሆን በዚህም 471 ሺህ ዶላር አግኝተዋል፡፡ ጎግልን በመሳሰሉ ትልልቅ ድርጅቶች በሚያዘጋጁት ስብሰባ ላይ ንግግር በማድረጋቸው ደግሞ 351ሚሊዮን ዶላር ያገኙ ሲሆን ከመፅሀፋቸው ደግሞ አንድ ሚሊዮን ዶላር ማግኘታቸውን የሚጠቅሱት መረጃዎቹ እንዴት ከሰላሳ ሚሊዮን ዶላር በላይ ሀብት ሊኖራቸው እንደቻለ ጥያቄ እያነሱ ይገኛሉ፡፡
መረጃዎቹ የቀድሞዋ የዩኤስኤይድ ዋና ዳይሬክተር ሀብታቸው በየትኛው አክስዮን ውስጥ እንደተቀመጠም ዝርዝር ማስረጃዎችን አቅርበዋል፡፡ የዩኤስኤይድን ጉዳይ እየተከታተለ ያለው ኤለን መስክ ይህንን በተመለከተ በኤክስ ገፁ ላይ ‹‹ሳማንታ ፓወር ከደመወዛቸው በመቶ እጥፍ የሚበልጥ ሀብት እንዴት ሊያገኙ ቻሉ?›› ሲል ጥያቄ አቅርቧል፡፡
ሳማንታ በጉዳዩ ላይ እስካሁን ምላሽ አልሰጡም።