ይህ መረጃ አሳዛኝም አስተማሪም ስለሆነ በፋስት መረጃ አቅርበነዋል።
ወጣቱ አረብ ሀገር የምትኖረዋን ልጅ በፌስቡክ ይተዋወቃል፣ ፍቅር ጀመሩ የእሱ ፍቅር አላስቀምጥ አላሰራ ብሏት ከስድስት ወር ትውውቅ በኋላ ወደ ሀገር ቤት መጣች።
ወደ ሀገር ቤት መጣች ተቀበላት ቦሌ ወረዳ 12 ቤት ተከራይቶ ገቡ፣ ይህ ሁሉ ሲሆን ቤተሰብ አያውቅም። በሚያሳዝን ሁኔታ በዛው ቀን ለእሱ ብላ የመጣችውን ፍቅረኛውን ገደላት።
ከገደላት በኋላ ሬሳዋን ጠቅልሎ ቤት ውስጥ ካስቀመጠ በኋላ ይዛ የመጣችውን ንብረት ይዞ ጠፋ።
የእሱ አድራሻ እንዳይታወቅ አከራዮቹን «ፋይዳ መታወቂያ ላወጣ ስለሆነ እናንተ ጋር ያለውን መታወቂያ ኮፒ ስጡኝ» ብሎ ተቀብሎ እንደሄደ አከራዮቹ ይናገራሉ።
ከአንድ ሳምንት በኋላ አከራዮቹ ጥሩ ያልሆነ ሽታ በመኖሩ ለፖሊስ አመልክተው በሩ ሲከፈት ሬሳ ቤቱ ውስጥ ተገኘ።
እሱ ብቻ እንደተከራየ የሚያውቁት አከራዮች የሴት ሬሳ ቤት ውስጥ መገኘቱ ዱብ እዳ ነው የሆነባቸው። የተገኘው ሬሳ ለምርመራ ሆስፒታል ከገባ በኋላ ቤቱን የተከራየው ልጅ ሲፈለግ አንድ መንገድ ተገኘ።
የቤት ኪራይ በባንክ አስገብቶ ስለነበር ስልክ ቁጥሩ ተገኝቶ በጂፒኤስ ልጁ እዛው ሰፈር መጠጥ ቤት እየተዝናና ሊያዝ እንደቻለ ለፋስት መረጃ ጉዳዩን ያስረዱ ግለሰቦች ገልጿል።
ከተያዘ በኋላ ያደረገውን ሁሉ በዝርዝር እና በድርጊት በቦታው በመገኘት አሳይቷል።
ጉዳዩን አሳዛኝ የሚያደርገው የልጅቷ ቤተሰቦች ልጃቸው አረብ ሀገር እንዳለች ነው የሚያውቁት። (ይህ መረጃ የደረሰን jan 26 ሲሆን በወቅቱ የልጅቷ ቤተሰብ እየተፈለገ እንደነበር ነው)