«በ 1995 የመጀመርያ ድግሪ ልማር ጅማ ስመጣ የ10 ወር ልጅ ነበረኝ። የዛኔ የዛሬዋ ጅማ 50% ቷ ራሱ አልነበረም።ጅማ ቤተሰቤን ይዠ እንደገባሁ ከተማ ራሀ ሆቴል ከነቤተሰቤ አደርኩ። ጧት ተነስቼ ሚስቴንና ልጄን ሆቴል ትቼ ቆጪ JU አጠገብ ቤት ተከራየሁ። ወደ ሆቴሉ ተመልሼ የፈረስ ጋሪ ይዠ በአጂፕ በኩል ወደ ቆጪ ሻንጣየን እና ቤተሰቤን ጭኘ ወደ ተከራየሁት መሄድ ጀመርኩ።
እና ልጄ ሁለት ቀን ስለተጓዘ ደክሞት ነው መሰል ጸጥታ አብዝቶ ነበር። ጋሪው ላይ ወጣንና ነጂው ፈረሱን "ቼ.. ሂእ ሂኢ" ሲለው ልጄ ከት ብሎ ሳቀ። ባለቤቴ ጋር ተያይተን ሳቅ አልን። ጋሪው ነጅ ደግሞ "ቼ ሲል ፈላው እናቱ እቅፍ ሆኖ ደግሞ ሳቁን ለቀቀው። ከዛ ልቤ ላይ አላህ የጣለውን ጣለና.. ለባለቤቴን "አብሽሪ ይሄ አገር ግጥማችን ነው (ይመቸናል)" አልኳት..ተፋኡሉ አምሮ። እና ዘንድሮ እኔም ፕሮፌሰር ነኝ። ያልጅም 4ኛ አመት ሜድስን ተማሪ ነው።
እና የነገር አለሙ ተፋኡልን እየተባሸርንበት መኖር እንጂ የምን ጨለማ ጨለማ ማየት። ይልቅ በጨለማው ውስጥ ብርሀኑን እየፈለግን በጭላንጭሉ ተስፋ መንቦግቦግ ነው። ብርሀን ባታይ ራሱ አይኔ ታሞ እንጂ ብርሀኑ አለ ብለህ በየቂን መጓዝ ነው። በመሀል ለሚከሰተው አታስብ። ያንተ ድርሻ አይደለም። ዩኒቨርሱ ባለቤት አለው። እንደከጀለ ይገለባብጠዋል።»
©: ፕሮፌሰር ቃልኪዳን ሐሰን