ይህቺን እህታችንን አስታወሳችኋት⁉️
ለ3 አመታት ገደማ ከነ ቤተሰቧ ደጇን ዘግታ ስታነባ የነበረችው እህታችን ሙሪዳ ጀማል፤ ካልሲና አንዳንድ ነገሮች ጉሊት ላይ እየሸጠች ሳለች ከ3 አመታት በፊት የመኪና አደጋ ደርሶባት አደጋው ካደረሰባት ጉዳቶች መካከል፦
①) የግራ ሁለት አጥንት ስብራት፣
②) የቀኝ ደረቷ ሁለት አጥንት ስብራት፣
③) የቀኝ እግር ስር መቆረጥ፣
④) የግራ እግር የቅልጥም ስብራት፣
⑤) የኋላ 3 ጥርስ መንጋጋ መውለቅ፣
⑥) የፊት 2 ጥርስ መውለቅ… አጋጥሟት ነበር።
ባለፈ በእናንተ በደጋጎች ሶደቃ ታክማ ሁሉም ብረቶች ከሰውነቷ ወጥተው በሰላም ወደ ቤቷ መግባቷን ነግረውኛል። አል-ሐምዱ ሊላህ! ችግሯን እንዳካፈልኳችሁ ሁሉ ደስታዋንም ላካፍላችሁ ብዬ ነው። አስቡት! አነሰች በዛች ሳትሉ የምትሰድቋት ሶደቃ የስንቶችን የአመታት ጭንቀትና ትካዜ ወደ ደስታ በአላህ እገዛ እንደምትቀይር! ሁላችሁንም አላህ ይቀበላችሁ።
ግን በገንዘብ እጥረት ይህን ያክል አመት ብረት ሰውነት ውስጥ ተሸክሞ መኖር ከባድ ነው። ሐኪሞች ግን እንደት አቅም ያጣን ሰው በብድርም ሆነ በሆነ መልኩ አሳዝኗቸው ሳይታከም ሲመለስ ሳይከብዳቸው! ሳስበው ግን ሐኪም ብሆን የሚያስችለኝ አይመስለኝም፤ ሲኮን ጨካኝና ቋጣሪ ያደርጋል እንደ¿
ለማንኛውም ሁላችሁም ተመስግናችኋል። በካንሰር የታመመው የ6 አመት ታዳጊ ሙሐመድ ይመርም መታከሚያ ገንዘቡ 3,267,003.58 ብር ደርሶለት የኢምባሲና የባንክ ሂደት እንደጨረሱ በቅርቡ ወደ ህንድ ለሕክምና ይሄዳል። በዱዓችሁ አትርሱት። ሁላችሁንም አላህ ይቀበላችሁ።
||
t.me/MuradTadesse