የሪያዱ ፀያፍ ድግስ እና የቢድዐ ኃይሎች ጥምር ዘመቻ‼
==================================
✍ «ሰሞኑን በሰፊው እየተራገቡ ካሉ ጉዳዮች ውስጥ ምናልባትም ቀዳሚው እጅግ ሰቅጣጭና አሳፋሪ የሆነው የሪያዱ የጭፈራ ድግስ ነው። ድግሱ ካልተሳሳትኩ በያመቱ እየተፈፀመ ያለ የሸር ድግስ ነው። ሃገሪቱ ቀድሞም ቢሆን ተጨባጭ የሆኑ ችግሮች እንዳሉባት ይታወቃል። እንደ አልባኒ፣ ኢብኑ ባዝ፣ ኢብኑ ዑሠይሚን ያሉ ሃገሪቱን የሚወዱም የሚያደንቁም ዑለማኦች ራሳቸው ችግሮች እንዳሉ በግልፅ ተናግረዋል። ከቅርብ ዓመታት በኋላ ደግሞ እነዚህ ክፍተቶች በአይነትም፣ በብዛትም እየጨመሩ መጥተዋል። "ሀይአቱ ተርፊህ" የተሰኘው መስሪያ ቤት ትውልድ እያወደመ፣ ሃገር እየጎተተ፣ ወዳጅ እያሳፈረ፣ ጠላት እያስቦረቀ ያለ መስሪያ ቤት ነው።
በቅድሚያ ክስተቱን በተመለከተ መጥራት ያለባቸው ነገሮች አሉ።
1- የከዕባን ምስል የሚያራክስ ክስተት ተፈፅሟል? መደምደም አይቻልም። ይሁን እንጂ ከአራት ስክሪኖች በህብር የተላለፈው የብርሃን ቅንብር በቪዲዮው መሀል ላይ ከዕባን የሚመስል ነገር ያሳያል። ከዕባ ታስቦበት ከሆነ በዲን ሸዒራ ላይ መሳለቅ ነው። በርግጥ ክስተቱ የዘንድሮ አይደለም። ባለፈው አመት በተካሄደ የቦክስ ውድድር ላይ የተፈፀመ ነው። ለምን አመት ቆይቶ የአሁን አስመስሎ ማሰራጨት እንደተፈለገ አላውቅም።
2- በከዕባ ቅርፅ በተሰራው ምስል ላይ ዘፋኝ ወጥታ ስትጨፍር ብለው ያሰራጩም አሉ። ይሄ ውሸት ነው። በ2023 አርጀንቲና ላይ የተከሰተን ክስተት ነው አቀናብረው ያመጡት።
3- የከዕባን ምስል ዙሪያውን ጣዖቶች አድርጎ የተሰራጨውስ? ይሄ የተቀናበረ ሃሰተኛ ምስል ነው። ለምን አስፈለገ? ሳያጣራ የሚያራግበውን መንጋ ለመጋለብ።
4- በሪያዱ ድግስ ላይ የዐሊይን ዙልፊቃር ሰይፍ ታጥቃ የወጣች ዘፋኝ መታየቷስ? ይህም ሃሰት ነው። አንደኛ ዘፋኟ ፍልስጤማዊት ናት። ሁለተኛ ሪያድ ሳይሆን አሜሪካ ኒዮርክ ውስጥ የተከሰተ ነው። ሶስተኛ ዙልፊቃር በሌለበት የዙልፊቃር ምስል ነው ማለትም አይቻልም።
ከዚህ ውጭ ፀያፍነቱ የማያከራክር እርቃን ቀረሽ ጭፈራ ነበር የተካሄደው። ይሄ ግልፅና ሰቅጣጭ ጥፋት ነው። ይሄ አልበቃ ብሎ:-
1ኛ፦ ምስል ማቀናበር፣ የሌላን ሃገር ክስተት አጭበርብሮ ማቅረብ ራሱን የቻለ ወንጀል ነው። ከኢስላም ለመከላከል ወይም ጥፋትን ለማውገዝ መዋሸት አያስፈልግም። ለሳዑዲ ያለህ ጥላቻ በከዕባ ዙሪያ ጣኦት እስከ መስራት ካደረሰህ ራስህ በከዕባ ላይ እየተሳለቅክ ነው። ኢስላም በግልፅ ከሃ .ዲዎች ላይ እንኳ በደል እንዳይፈፀም ይከለክላል። አላህ እንዲህ ይላል:-
{ یَـٰۤأَیُّهَا ٱلَّذِینَ ءَامَنُوا۟ كُونُوا۟ قَوَّ ٰمِینَ لِلَّهِ شُهَدَاۤءَ بِٱلۡقِسۡطِۖ وَلَا یَجۡرِمَنَّكُمۡ شَنَـَٔانُ قَوۡمٍ عَلَىٰۤ أَلَّا تَعۡدِلُوا۟ۚ ٱعۡدِلُوا۟ هُوَ أَقۡرَبُ لِلتَّقۡوَىٰۖ وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَۚ إِنَّ ٱللَّهَ خَبِیرُۢ بِمَا تَعۡمَلُونَ }
"እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ለአላህ ቀጥተኞች በትክክል መስካሪዎች ሁኑ፡፡ ሕዝቦችንም መጥላት ባለማስተካከል ላይ አይገፋፋችሁ። አስተካክሉ። እርሱ (ማስተካከል) ለአላህ ፍራቻ በጣም የቀረበ ነው። አላህንም ፍሩ። አላህ በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው።" [አልማኢዳህ፡ 8]
2ኛ፦ የተከሰተውን እርቃን ቀረሽ ምስል ማሰራጨቱም ራሱን የቻለ ጥፋት ነው። ብልግናን ለማውገዝ ብልግናውን ማሰራጨት ተቀባይነት የሌለው ምክንያት ነው።
ይህንን ጥፋት ተከትሎ እንደተለመደው በሱና ዑለማኦች እና በሰለፊያ ደዕዋ ላይ ከፍተኛ የሆነ የማጠልሸት ዘመቻ ተከፍቷል። በሳዑዲ ሙንከራት በተከሰተ ቁጥር ሁሌ ጥፍራቸውን ስለው፣ ጥርሳቸውን አግጥጠው በሱና ዑለማኦች ላይ የሚዘምቱ አሉ። እነማን ናቸው? ሺርክን 0ቂዳው ያደረገው አሕባሽ፣ የዲሞክራሲን የኩ. ፍር ስርአት ቅዱስ የኢስላም አካል ያደረገው ኢኽዋን፣ እጁ በሙስሊሞች ደም፣ ልቡ በሶሐቦችና ጥላቻና በሺርኪያት የጨቀየው ሺ0 እና አድናቂዎቻቸው፣ በሱና ዑለማኦች ቂም ያረገዙ ኸዋ -ሪጆች ናቸው። ሌላው በቀደዱለት የሚፈስ የነፈሰው ሁሉ የሚወዘውዘው መንጋ ነው። እንዲህ አይነቱን ክፍል ሸይኽ ሙሐመድ ወሌ "ሰፊው ህዝብ ማለት አንዳንዴ ሰፊሁ ህዝብ ማለት ነው" ይላሉ። በፎቶሾፕ እያቀናበሩ የሚያቀርቡለትን ሳይቀር ሳያላምጥ እሳት ለብሶ እሳት ጎርሶ በዑለማእ ላይ ፈራጅ ቀዳጅ ይሆናል።
አሁን የሱና ዑለማኦችን ለማብጠልጠል ሰበብ ከሆናቸው የከፋ፣ የባሰ እና የበዛ ጥፋት ሺ0 ላይ፣ ሱፊያ ላይ፣ ኢኽዋን ላይ አለ። እንደ ሃገርም እነዚህ ዘማቾች የሚያወድሷቸው ኢራን እና ቱርክ ውስጥ ከዚህ የከፋ ብዙ ጥፋት አለ። እንደ ታዋቂ ሰዎች እነ ቀርዷዊ፣ ሰይድ ቁጥብ፣ በሃገር ውስጥም እነ "ሙፍቲ" ዑመር ላይ አለ። ከመሆኑም ጋር እንዲህ አይነት የተቀናጀ ዘመቻ አድርገውባቸው አያውቁም። የኢኽዋን ቡድን እንዲያውም ከሺ0 ጋር ያለው ልዩነት እንደ አራቱ መዝሀቦች የፊቅህ ልዩነት ነው የሚልበት አለው። ከኢስላም የሚያስወጡ ግን ደግሞ በኢስላም ስም የሚፈፀሙ ጥፋቶች ላይ አይናቸውን ጨፍነው እያለፉ የሱና ዑለማኦችን ፈፅሞ በማይደግፉትና እጃቸው በሌለበት ነገር ተጠያቂ ያደርጓቸዋል። ለምን? የመንሀጅ ልዩነት ስላለ ለማጠልሸት እስከ ጠቀመ ድረስ በሌሉበትም ከመክሰስ አይመለሱም። የተከሰተ ብቻ ሳይሆን የሌለውን አቀናብሮ ከማቅረብም አይታጠፉም፡፡
ዑለማኦቹ ላይ ለሚያነሱት ክስ ሁለት ማመሀኛዎችን ሲያነሱ ማየት የተለመደ ነው። አንዱ ዑለማኦቹ የሳዑዲን መንግስት ያደንቃሉ የሚል ሲሆን ሌላኛው እነዚህን ጥፋቶች ለምን አልተቹም የሚል ነው። ሁለቱም ምክንያቶች የቀደመ ጥላቻን ለማራገፍ የሚነሱ ሰበቦች እንጂ ዑለማኦቹ ላይ ለመዝመት የሚያበቁ አይደሉም። በየተራ እንመልከት፦
ምክንያት አንድ፦ "ዑለማኦቹ የሳዑዲን መንግስት ያደንቃሉ"
ሀ- ዑለማኦቹ ያደነቁት በሚያዩዋቸው መልካም ስራዎች እንጂ በጥፋቶቹ አይደለም። ነው ጥፋት ያለበት አካል መልካም ቢሰራም አይደነቅም፣ እንዲያውም ይወገዛል ነው መርሃችሁ?
ለ- እንደዚያ ከሆነ ለምንድነው ኢራንን የምታደንቁት? ኢራን በሺርክ የተወረረች፣ ዑለማኦቿ ሶሐባ የሚሳደቡ፣ ብልግና የተንሰራፋባት፣ ሱኒዮችን የምትጨፈጭፍ ሃገር ናት።
ለምንድነው ኤርዶጋንን የምታወድሱት? ኤርዶጋን ከማል አታቱርክን የሚያወድስ፣ ቀብሩ ላይ የአበባ ጉንጉን የሚያስቀምጥ፣ የአታቱርክ ልጆች ነን ብሎ የሚኮራ፣ የኢስላምን ህግጋት ማደስ ይገባል የሚል፣ የአንግሎ ሳክሰን ሴኩላሪዝም ነው የምንከተለው የሚል፣ የሸይኽ ሙሐመድ ብኑ ዐብዲልወሃብን ደዕዋ እንደሚጠላ በግልፅ የሚናገር፣ "አላሁ መውጁዱን ቢላ መካን" የሚል፣ የራሱ ባለ ስልጣን በነብያችን ክብር ላይ የተሳለቀ፣ ዝሙት በመንግስት ደረጃ ተፈቅዶ ግብር የሚሰበሰብበት፣ የእርቃንኖች ሆቴል ፈቃድ ያገኘበት፣ ይህ ሁሉ ከመሆኑ ጋር ኢኽዋን ሰፈር ኤርዶጋን በተለየ ይወደሳል። ቀርዷዊ "አላህና መላእክቱ ከኤርዶጋን ጋር ናቸው" ይላል። እስኪ ከናንተ ውስጥ በሱና ዑለማእ ላይ እንደምታደርጉት ቀርዷዊንና መሰሎቹን አጥፊዎችን አወደሱ ብሎ የሚተች አለ? የለም። ለምን? አስቡት የሐሰን ነስረላህ፣ የዐብዱልመሊክ አልሑሢ፣ የቀርዷዊ፣ የዑመር ገነቴ አድናቂ በፈውዛን ላይ አፉን ሲከፍት። አስቡት እሱ ከነዚህ አፈንጋጮች እየተከላከለ እኛ ከነፈውዛን ለመከላከል ስንሸማቀቅ።